Messy Ethiopian

Messy  Ethiopian Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Messy Ethiopian, Baby & children's clothing store, ETHIOPIA, Dubai.

29/03/2024
29/03/2024

ብልፅግና ፓርቲ ዴሞክራሲ በተቋም ግንባታ ይረጋገጣል ብሎ ያምናል፡፡

እስካሁን ባለዉ የዓለም አቀፍ ሁኔታ ሁሉም ምሁራንና ሀገራት እኩል የተስማሙበት የዴሞክራሲ ብያኔ ባይኖርም የተዋንያን እና የህዝብ ተሳትፎ የተረጋገጠበት ስርዓት መገንባት መቻል ነው፡፡ እነዚህ ተሳትፎዎች የሚረጋገጡበት አያሌ ሁኔታዎች ቢኖሩም የሀሳብ ነጻነት፣ የመደራጀት መብትና የሀገሪቱን ህጎች በመከተል በምርጫ የመሳተፍ (መወዳደር) መብቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ብልፅግና ከተመሰረተ ገና አጭር ዕድሜ ያለው ፓርቲ ቢሆንም ለዴሞክራሲ ያለውን ቁርጠኝነት የሀሳብ ነጻነትን ያለገደብ በማረጋገጥ፣ በ2013 የተካሄደውን ሀገራዊና ክልለዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በማድረግ፣ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ሌሎች የዴሞክራሲ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲደራጁ በማስቻል አመርቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩልም ፖለቲካችን ከመጣበት የረጅም ዓመታት የጉልበት ዝወራ ተላቅቆ ወደ ሃሳብ እንዲሸጋገር ፓርቲያችን ብልፅግና ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ከተቻለ በአንድ በኩል የሲቪክ መብቶችና የማህበረሰብ መብቶች ስርዓታዊ በሆነ አግባብ ይከበራሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እኩልነት፣ ነፃነትና ፍትህ ተቋማዊ በሆነ አግባብ እንዲሰፍኑ ስለሚያግዝ የሰው ልጆች ተደማሪ ፍላጎቶች መካከል ያለውን ተቃርኖ በመቀነስ ትብብር እንዲጎለብት ያግዛል፡፡

26/03/2024

የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር የብቸኝነት ጉድለትን በመሻገር የወል ብልጽግናን እንድናረጋግጥ ያግዘናል፡፡

የሰው ልጅ እዚህ ምድር ላይ አብሮ መኖር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የብቸኝነት ጉድለት እንዳለበት በመረዳት በትብብርና በፉክክር መልክ ሊገለጡ የሚችሉ መስተጋብሮችን ፈጥሮ አብሮ እየኖረ እዚህ ደርሶአል፡፡

የብቸኝነት ጉድለት ማለት የሰው ልጅ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደማህበረሰብ በተናጠል የሆነ ብቃት ይኖረው ይሆናል እንጂ ከሌላው ሙሉ በሙሉ ተቆራርጦ እራሱን ችሎ መኖር እንደማይችል የሚሳያሳይ ክፍተት (Vacuum)ነው፡፡ ይህ ፅንሰ ሀሳብ ለሀገራትም ይሰራል፡፡ ሀገራት ለብቻቸው የሚያቆማቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፀጋዎችና ብቃቶች ቢኖሯቸውም ከሌላው የዓለማችን ክፍሎች ጋር ሳይተባበሩ ለብቻቸው ዘላቂ ህልውና እና ጥቅም ማረጋገጥ አይችሉም፡፡

የሰው ልጅ ይህን የብቸኝነት ጉድለት ለመሙላት ወይም በትብብር አሊያም በፉክክር አማራጮች ውስጥ ሊያልፍ ይችላል፡፡ በእነዚህ አማራጮች ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት ደግሞ ሚዛናዊ ሆኖ አብሮ ተባብሮ መኖርን ጨምሮ ኢ ሚዛናዊነት ሲያጋጥም ደግሞ ተገቢ ወዳልሆነ ፉክክር በማድላት ራስን ከሌሎች እስከ ማግለል ሊደርስ ይችላል፡፡ እውነታው ግን የሰው ልጅ ኑሮ የሚዛናዊ ትብብርና ምክታዊ ፉክክር ውጤት መሆኑን በወጉ በመገንዘብ በሰጥቶ መቀበል ህግ አብሮ መኖር (መስራት) ነው፡፡

የመደመር ጸሃፊ የተከበሩ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የመደመር ምንነትና አስፈላጊነት በተነተኑነበት ክፍል መደመር ከብቸኝነት ጉድለት ወደ ክሱትነት የሚደረግ ጉዞ መሆኑን ሁሉም ሰው ሊረዳ በሚችለው መልኩ አብራረተዋል (መደመር፡36-48)፡፡

26/03/2024

Address

ETHIOPIA
Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Messy Ethiopian posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share