Azest Gifts

Azest Gifts 4th Floor, Building 2, No. 5, Campus Road, Songzhou Street, Baiyun District, Guangzhou

BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS FOR MEN AND WOMEN HR19
22/02/2023

BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS FOR MEN AND WOMEN HR19

tanktop - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27
22/02/2023

tanktop - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27

T - shirt - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27
22/02/2023

T - shirt - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27

Sweater - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27
22/02/2023

Sweater - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27

Hoodie - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27
22/02/2023

Hoodie - LOVE BEAUTIFUL HORSE 3D ALL OVER PRINTED SHIRTS HR27

21/09/2018

፨፨፨ገጣሚ አትበሉኝ፨፨፨
ባዛውንቶች ለቅሶ በህፃናት ጩኸት
በእናቶች ዋይታ ባባቶች መቆጨት
ወይኔ ክንዴን ማለት
በድሀ አንገት መድፋት
በሀብታም ድንፋታ
በጠንካራው ትዕቢት
በሌላው ቅሬታ
ተወጥሮ ሳለ
ገጣሚ ሞኝ ነው ይህንን አይይም
ባሳቡ ያለችውን ሴትን እየሳለ
ኡኡታ በርክቶ ሰቆቃ አይሎ
ወዮታ ከፍ ብሎ እግዚኦ አጥር ነቅሎ
እሾህ ሰው ላይ በቅሎ
ከአይኑ ስር ሳለ
ገጣሚ ሞኝ ነው ይህንን አያይም
ተፈጥሮን እያለ
እኔ ግን
ሰቆቃዬን ትቼ ወደሴት ካየሁኝ
ደሜን እዤን ትቼ ባስብ ከማገጥኩኝ
ወንድሜ እየሞተ ካልጋው ላይ ከዋልኩኝ
ገጣሚ አትበሉኝ
ድህነቴን ትቼ ይቺ ውብ ጨረቃ
በጠፈሩ ደምቃ
እያልኩ ከዘመርኩኝ
ችግሬን ረስቼ ይቺ ድንቅ ፀሀይ
በውበቷ አማላይ
ማለት ከጀመርኩኝ
ገጣሚ አትበሉኝ
የአይኖቿ ነፀብራቅ የቅንድቧ ማማር
የፊቷ ክብነት የፀጉሯ ማጠር
የጥርሷ መሽኮርመም የከንፈሯ ማፈር
እያልኩ ከገጠምኩኝ
የእውነት ገጣሚ አትበሉኝ
ጆሮዬ በጩኸት ነግሎ
አይኔ በእምባ ታውሮ
እጄ በእሾህ ተቆርጦ
እግሬ ደም በለወሰው ረግረግ ተውጦ
ባባቴ አጥንት ላይ ቆሜ
በእህቴ ለቅሶ ደክሜ
በእናቴ ጩኸት አዝምሜ
በወንድሜ ደም ተምሜ
እኔ ስለዳሌ ከፃፍኩኝ
የእውነት ገጣሚ አትበሉኝ።

ገጣሚ አይደለሁም።

ለሰሞኑ!!!!
፼0(እኔ)


27/06/2018

ፐ-ግዕዝ:
የ______ዘመን
ያኔ በዛ ዘመን አንተን ለመዋጋት
ትልቅ ግንብ ገነቡ ባቢሎናውያን
አንተም ይህን ስታይ እጅግ ተቆጥተህ
ቋንቋውን ደባለቅህ አዛባህ
እ-ን-ዳ-ይ-ግ-ባ-ቡ አደረግህ
አሁን
አሁን በ_____ዘመን
በአንድ ቃል አውርተን
አንድ ዜማ አውጥተን
አንድ ሐሳብ አውግተን
እንደባቢሎናውያን ካላዛባህብን
ታዲያ ለምንድን ነው መግባባት ያቃተን
ሌላ ዓይነት ቋንቋ እንደሚያወራ ሰው
ለፀብ ተጋበዘን ለአመፅ ተነሣን
አንተ እንደዛኔው ካለዋወጥክብን ካላዛባህብን
ታዲያ ለምንድን ነው?
የሰላሙ ወሬ አመፅ የሚጭርብን?
አንተ እንደዛኔው ካላዛባህብን
እኛ ሳንረዳው ካልቀያየርክብን
ታድያ ለምንድ ነው?
የፍቅሩ ጥያቄ ለሞት የሚያበቃን
ታላቅ ሐሴት ሳይሆን ኃዘን የሚጭርብን
ታድያ ለምንድን ነው?
ታድያ ለምንድን ነው?
የኛ ኃጥያት በዝቶ ነው?
እ! እሱማ ግልጽ ነው
ትዕግስትህ አልቆ ይሆን?
እባክህ አምላኬ
እባክህ ጌታዬ
እባክህ አንድዬ እኔን ግራ ገባኝ
ይህን መልስልኝ
እንድ ነው ቋንቋችን?
ተጻፈ፦በኔጌር 27/01/2010

25/06/2018

ሁሉም አንድ ናቸው ዲያ

በአንድ በኩል አባቴ አሳዘነኝ።እስካሁን እየደወለ ነበር ማለት ነው።ስልኬ ላይ ያልተሳካ የሥልክ ጥሪ መኖሩን አየሁ።ሁለተኛ ደግሞ ቦንብ ማፈንዳታቸው አሳዘነኝ።ከኛ ውስጥም ሰላማችንን የማይፈልግ...
25/06/2018

በአንድ በኩል አባቴ አሳዘነኝ።እስካሁን እየደወለ ነበር ማለት ነው።ስልኬ ላይ ያልተሳካ የሥልክ ጥሪ መኖሩን አየሁ።ሁለተኛ ደግሞ ቦንብ ማፈንዳታቸው አሳዘነኝ።ከኛ ውስጥም ሰላማችንን የማይፈልግ አለ ማለት ነው?ለጓደኞቼ ነገርኳቸው።
"አላልኩህም ...ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆንክ ችግር ትፈጥራለህ።"አለኝ ጉደኛ ጓደኛዬ።በእርሱ ተገርሜ ሳላበቃ እርሷም
"እንኳን ፈነዳ!"ብላ አስደነገጠችኝ።
"እንዴ ምን ሆናችሁ ነው።ቦንብ እኮ ነው የፈነዳው፤ጎማ አይደለም።"
"አልገባህም...ይህ ቦንብ ለመለያየት የተጣለ ቢሆንም ይበልጥ ያቀራርበናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ደም ሲያይ አይወድም፤ይልቁን ደም መፈለግ ይወዳል።ደም ይበልጥ ያዋግነዋል፤ይበልጥ ያገናኘዋል።"አለኝ።
"ሠዎች ...ዛሬ ምንም አልተግባባንም።"
"አለመግባባት እና አለመስማማት ይለያያል። እኔ እና አንተ ተግባብተናል፤ግን አልተስማማንም።ሌሎች ተስማምተው ያልተግባቡ ይኖራሉ።ይህ በጣም ከባድ ነው። ያልተግባቡ፤ባለመግባባታቸው ያልተስማሙም አሉ።ይህ ይሻላል።መጨረሻ ላይ ተግባብተው የተስማሙ ካሉ እነርሱን የሚያቆማቸው አይገኝም።"አለኝ።
ፀጥ አልኩኝ።
"ሦስተኛ ጊዜ ተሸነፍክ...ዶሮ ከጮኸ በኋላ ...ሦስተኛ ጊዜ"ጓደኛችን ትስቃለች።
ተሰናብቼያቸው ሄድኩ።
ዝናቡ ማካፋት ጀመረ።ካፊያው ይፈናከታል።መላእክቱም አመፅ ጀመሩ እንዴብዬ አስቤ ሣልጨርስ ዶፉን ለቀቀው።"እግዚአብሔር አዘነ።"አልኩኝ። ወዲያው ከባድ ነጎድጓድ ከብልጭታው ጋር ተሰማ።"እግዜሩ ተቆጣ!"አልኩኝ በሹክሹክታ ።እግዜር የተቆጣው በቦንቡ ይሁን በእኔ እንጃ!ብቻ ተቆጥቷል።
* * *
ወደ ርዕሴ ልመለስ። የትላንቱን የድጋፍ ሠልፍ UNESCO ሊመዘግበው ይገባል ባይ ነኝ። 4 ሚልየን ህዝብ በአንድነት የወጣበት ሠልፍ ነው።በነገራችን ላይ ሠልፍ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብርቁ አይደለም።እንደውም ሠልፍ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ይመስለኛል።ይህ ሠልፍ ግን ይለያል። ሌላ ቦታ ሠው የሚሠለፈው እየተማረረ ነው። እዚህ ግን ሁሉም በደስታ ተሠልፏል።ሠልፊ እየተነሣ ...ከህዝቡ ጋር ሠልፊ ...ከዶ/ር አብይ ጋር ሠልፊ...ቦንቡን ካፈነዳችው ጋር ሠልፊ...ከቦንቡ ጋር ሠልፊ ከፈነዳባቸው ጋር ሠልፊ...ሠልፊ ሠልፊ ሠልፊ...
ታዲያ ይሄ ያልተመዘገበ ሌላ ምን ይመዘገባል!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ስለዚህ ሠልፊ የበዛበት ሠልፍ በሚል UNESCO ይመዝግብልን!

ዲያ

Address

4th Floor, Building 2, No. 5, Campus Road, Songzhou Street, Baiyun District
Guangzhou

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Azest Gifts posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share