Ethiopian dj vu

Ethiopian dj vu tv show

23/01/2025
የቲክቶክ ቁርጡ ታወቀ።ሲጠበቅ የነበረው የፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰማ።  የአሜሪካ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ቲክቶክ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ካልተሸጠ በጃንዋሪ 19 2025 እ. ኤ...
17/01/2025

የቲክቶክ ቁርጡ ታወቀ።

ሲጠበቅ የነበረው የፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰማ። የአሜሪካ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ቲክቶክ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ካልተሸጠ በጃንዋሪ 19 2025 እ. ኤ.አ እንዲዘጋ በስር ፍርድ ቤቶች የተወሰነውን ውሳኔ ያለተቃውሞ በሙሉ ድምጽ ደግፎታል።
ፍርድ ቤቱ በውሳኔው "ቲክቶክ ከ170 ሚልየን ተጠቃሚዎቹ የመናገር ነጻነት አንጻር፣ ከቻይና መንግስትጋ ያለው ቁርኝት ለአገር ደህንነት አስጊ እንደሆነና ይህን ተከትሎም የግድ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ተሸጦ በአሜሪካ ህግ እንዲዋቀር" ሲል ሃሳብ ሰጥቷል።

የዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ኑዛዜ2008 ዓ.ም. ከዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ ጋር የተባበሩት ዐረብ ኢመሬትስ ሻርጃ ሰአሊተ ምሕረት አብረን ለማገልገል ተጠርተን ነበር:: ከሃያ ቀናት በላይ በየቀ...
14/01/2025

የዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ኑዛዜ

2008 ዓ.ም. ከዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ ጋር የተባበሩት ዐረብ ኢመሬትስ ሻርጃ ሰአሊተ ምሕረት አብረን ለማገልገል ተጠርተን ነበር:: ከሃያ ቀናት በላይ በየቀኑ በሚካሔደው በዚህ ጉባኤ ላይ ዘማሪት ሕይወት መሣሪያ በማይፈልገው የተለየ ድምፅዋ "ና ና አማኑኤል ና መድኃኒቴ" የሚል ድንቅ መዝሙር ስትዘምር ሰማሁ::

"ስሸጥህ አቀፍከኝ ስወጋህ ዓይኔ በራ" እያለ ራስን ከይሁዳና ከሌንጊኖስ ጋር በትሕትና የሚያነጻጽረው ይህን መዝሙር በጣም ስለወደድሁት አንዲት ቃል ላይ ብቻ እርማት እንድታደርግ አስተያየት ሰጥቼ አብረን በሰነበትንበት ሻርጃ ሕዝቡ በቃሉ እስኪይዘው ድረስ 14ቱንም ቀን አስዘመርኳት::

ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ በሙያዋ ነርስ ስትሆን ቤተ ክርስቲያን ቆንጥጣ ካሳደገቻቸው ወርቅ ዘማርያን አንድዋ ናት:: ሰዓታት የምትቆም ፣ አስቀድሳ የምቆርብ ፣ መምህሩ ያስተማረውን ቁጭ ብላ ሰምታ ለትምህርቱ የሚስማማ መዝሙር የምትዘምር ፣ በጣም በትሕትናና በታዛዥነት የምታገለግል ካላት የዝማሬ ጸጋ ገና የሚገባትን ያህል ያልተሰማች (Underrated) ያወቋትና የሰሟት ደግሞ እንዴት ሳልሰማት ቀረሁ የሚሉባት የቤተ ክርስቲያን ውድ ልጅ ናት:: እግዚአብሔር ይጠብቅልንና ዘማሪት ሕይወት ከ "ረ" ፊደል በስተቀር በመዝሙር ዘርፍ ገና ለመሥራት ምንም የሚቸግራት ነገር የለም::

ሰሞኑን በአእላፋት ዝማሬ ላይ "ና ና አማኑኤል" የሚለው መዝሙር በጃን ያሬድ መዘምራን ሲዘመር የሰሙና የወደዱት ምእመናን "ይኼ መዝሙር ግጥሙ የአንተ ነው" በሚል ሲመርቁኝ ሰነበቱ:: ምርቃቱን ሳላስተባብል አሜን ብዬ ብቀበልም ይህንን በሳል መዝሙር ግጥምና ዜማ የሠራውን ሰው ግን በጸሎት እንድታስቡትና እንድትመርቁት ማሳሰብ የግድ ሆነብኝ::

የመዝሙር ርእስ :- ና ና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ዘማሪዋ :- ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ
ግጥም :- ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ
ዜማ :- ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ

መዝሙሮችዋን ለመስማት ይኼንን ገፅ ሰብስክራይብ አድርጉ https://youtu.be/MZHegl4Wrn4?si=7NmkZ9NJFGvmklfJ

https://youtu.be/mpoTvGB3kcQ?si=bpxzCLCH42yX-Lfw

14/01/2025

አየሱስ ያድናል

ጋዜጠኛ:- ህዝቡ የሚፈልገው እርሶ ስልጣን በገዛ ፍቃዶት እንዲለቁ ነው ሪዛይን አያደርጉም?ዶ/ር አሸብር:- ከኔ ቀድመህ ነው አንተ ነህ ሪዛይን የምታደርገው።
19/08/2021

ጋዜጠኛ:- ህዝቡ የሚፈልገው እርሶ ስልጣን በገዛ ፍቃዶት እንዲለቁ ነው ሪዛይን አያደርጉም?
ዶ/ር አሸብር:- ከኔ ቀድመህ ነው አንተ ነህ ሪዛይን የምታደርገው።

Abiy arrives in Turkey18 Aug 2021 – (EP) Ethiopia’s prime minister Abiy Ahmed and his delegation arrived in Ankara, Turk...
18/08/2021

Abiy arrives in Turkey

18 Aug 2021 – (EP) Ethiopia’s prime minister Abiy Ahmed and his delegation arrived in Ankara, Turkey for a working visit (pictured).

Abiy will be meeting with President Recap Tayyip Erdogan where they are expected to discuss bilateral and regional issues of mutual interest.

Temesgen Tiruneh, chief of the Ethiopian intelligence agency and Redwan Hussein, the former Ambassador of Ethiopia to Eritrea and head of the Ethiopian government's emergency task force on Tigray are among the delegates that travelled with the prime minister.

Meanwhile, the US Special Envoy for the Horn of Africa, Mr. Jeffrey Feltman has been told he will not be able to contact Prime Minister Abiy Ahmed and met Deputy Prime Minister and Foreign Minster Demeke Hasen.

picture of the day 🇪🇹"እብድ እንኳን ሆኖ ለመኖር ሀገር ያስፈልጋል"መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ
17/08/2021

picture of the day 🇪🇹

"እብድ እንኳን ሆኖ ለመኖር ሀገር ያስፈልጋል"

መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ

13/08/2021

በመቀሌ ለአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎችን ሲመለምል የነበረ ከፍተኛ አመራር ተገደለ
By Natnael Mekonnen

: ከትግራይ እናቶች ህፃናትንና ወጣቶችን እየነጠቀና እያስገደደ በመመልመል ለአሸባሪው ህወሓት በታጣቂነት በማሳለፍ ለአስከፊ ስቃይና ሞት ሲዳርግ በነበረው ገ/ዮሃንስ የተባለ የሽብርተኛው ህዋሃት ከፍተኛ አመራር ላይ ትናንት ምሽት 3 ሰአት በመቀሌ ከተማ ደብሪ ተብሎ በሚጠራው ክፍለ ከተማ እንደተገደለ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች ገለጹ፡፡

ገ/ዩሐንስ የተባለው አሸባሪ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በመቀሌ ከተማ ደብሪ ከተባለው ክፍለ ከተማ እድሜአቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትንና ታዳጊዎችን ሽብርተኛው ህወሃት አሁን ላይ “የህዝብ ማዕበል ማሰለፍ” በሚል እየፈፀመ ላለው የወረራ እስትራቴጂ ማሳኪያ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀሰ የነበረ
መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የእነዚህ ህፃናትና ታዳጊ ቤተሰቦች ልጆቻችን የትደረሱ? በሚል በተደጋጋሚ ሲያነሱለት ለነበረው ጥያቄ ገና እናንተም ትሄዳላችሁ በሚል ትዕቢት ሲያሸማቅቃቸውና ሲዘልፋቸው ስለነበር የአካባቢው ማህበረሰብና ወጣቶች ዓላማ ለሌለው ነገር አንዘምትም በሚል ፊትለፊት ምላሻ ይሰጡት እንደነበርና ይህን ተከትሎም በግለሰቡ ላይ ግድያው መፈፀሙን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

በትግራይ ክልል ወላጆች ልጆቻችን አንሰጥም በሚል እምቢተኝነታቸውን በተግባር ጭምር ማሳየት
እንደጀመሩና አሁንም ልጆቻቸው በህይወት መኖር አለመኖራቸው እንቆቅልሽ እንደሆነባቸውና
የሚመለከተው አካል መልስ እንዲሰጠን እንፈልጋለን በሚል በግልፅ ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸውን
ምንጮቻችን ከስፍራው አሳውቀዋል።

13/08/2021

ሰበር ዜና‼️

: የምስራቅ ዕዝ 33ኛው ጋሻ ክፍለ-ጦር አምባላጌን እና ማይጨውን በቆረጣ በቁጥጥር ስር አድርጓል። የመቀሌን መንገድ በመዝጋት ወደ ኮረም አላማጣ ወልድያ እና ቆቦ በባዶ ሜዳ የሮጠውን የአሸባሪውን የህወሓት ኃይል ርዝራዥምንም ከጀርባ ቆርጦ አስቀርቶታል‼

ከ41 አመት በሗላ በኦሎምፒክ የተሰራ ታሪክ! ኬንያውያን "የባህል ስፖርታችን" የሚሉትን ውድድር ለሜቻ ግርማ እንዲህ ደስ በሚል የእግር አጣጣል ዘሎት ብሩን ገቢ አርጓል። አትሌት እሸቱ ቱራ ...
02/08/2021

ከ41 አመት በሗላ በኦሎምፒክ የተሰራ ታሪክ!

ኬንያውያን "የባህል ስፖርታችን" የሚሉትን ውድድር ለሜቻ ግርማ እንዲህ ደስ በሚል የእግር አጣጣል ዘሎት ብሩን ገቢ አርጓል።

አትሌት እሸቱ ቱራ በ1980 የሞስኮ ኦሎምፒክ ነሀስ አግኝቶ ነበር። ከ41 አመት በሗላ በ3 ሺህ መሰናክል የተገኘ የመጀመርያ ሜዳልያም ሆኖ ታሪክ ተሰርቷል።

አንበሳ!

Address

Adama
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian dj vu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian dj vu:

Share