Fesa Samuel

Fesa Samuel Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fesa Samuel, Men's clothes shop, Adama.

02/09/2025
02/09/2025
02/09/2025
02/09/2025
02/09/2025

የወላይታ ሶዶ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማሪያም ለመላው የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

መላው የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የዋንጫ አቀባበል በማስመልከት ከንቲባዋ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ መጪዉ አርብ ወደ ወላይታ ዞን እንደሚገባ በመገለጽ ዋንጫውን በደማቅ አቀባበል ለመቀበል ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል በንቂስ መውጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ እና በሲዳማ ቡና እግር ኳስ መካከል በተደረገ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ የሲዳማ አቻው 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ቢሆንም ተገቢ ያልሆነ ተጫዋች በማሰለፉ ምክንያት የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ቡድን 3 ንፁህ ጎል እና 3 ነጥብ በማግኘት አሸናፊ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መወሰኑንም አንስተዋል።

የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ በነገዉ ዕለት የኢትዮጵያ ዋንጫን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እንደሚረከብም ገልፀዋል።

በሂደቱም በኢትዮጵያ ባልተለመደ መልኩ ፍትሐዊ ውሳኔ በመስጠት ዋንጫው እንዲመለስ ላደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በወላይታ ሶዶ ከተማ አሰተዳደር ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ከዋንጫው ጋር የተፈጠሩ ጉዳዮች በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል።

የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ዋንጫዉን መጪው አርባ ዕለት ይዞ ስለሚመጣ በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግም ተናግረዋል።

በመጨረሻም መላዉ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎችና ህዝባችን የስፖርት ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ በነቂስ በመዉጣት በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ አቀባበል እንድታደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Address

Adama

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fesa Samuel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share