29/04/2023
አንድ ሰው በሞተ ጊዜ (ነፍሱ ከስጋው በተለየች ጊዜ) ጎረቤት ፣ወዳጅ ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ ለሟች ይለቀሳል ፣😭😭😭😭 ለቅሶው፣ ኡኡታ፣ ሙሾው፣ ትርምሱን ይህን ሁሉ የሟች (አስክሬን) ያዳምጠዋል። ገናዦች አይኑን ባይከድኑት ኖሮ በዙርያው የሚሆነውን ሁሉ በግልፅ ይከታተል ነበር።
ይሁን እንጂ አንድ የሞተ ሰው መጀመሪያ ላይ መሞቱን አያውቅም።ልክ በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ሞትን በህልም ውስጥ እያለመ እንደሆነ ይሰማዋል፣ መሞቱን ተከትሎ እየተለቀሰለት፣
ጀናዛው ታጥቦ ፣ በጨርቅ ተገንዞ ካበቃ በኋላ በሰዎች ትከሻ ላይ ሆኖ ወደ ሙታን መንደር ወደ መቃብር ስፍራ እየተሸኘ እንደሆነ እና ወደ መቃብር ሲወርድ ያያል።
ወደ መቃብር ውስጥ ከገባ በኋላ እንኳ ይህ ሁሉ በህልም ያውስጥ እንዳለ አይነት ስሜት ይኖረዋል።ለቀብር የመጡ ሰዎች ቀብረውት አፈር ተመልሶ ሲያበቃ እና ሁሉም ሰው ከስፍራው ሲሄድ
መጮኽ ነገር ግን ጩኸቱን የሚሰማው ማንም የለም ሁሉም ሰው ተበታትኖ ብቻውን ምድር ውስጥ ሲቀር ። አላህ ነፍሱን ይመልሳል።
አይኑንም ገልጦ ከ"መጥፎ ህልሙ" ይነቃል።ይህ ሰው ከመጥፎ ህልሙ ሲነቃ መጀመሪያ ላይ ደስተኛ ይሆናል ፈጣሪውን ያመሰግናል ።
ያጋጠመው ነገር ሁሉ በህልም ዓለም የተከሰተ ቅዠት እንደሆነ አድርጎ ያስባል ።
እና አሁን ከሞት እንቅልፉ ነቅቷል፣ በመቃብሩ ውስጥ ያለውን ጨለማ አይቶ ሶስት ጊዜ ለመነሳት ይሞክራል ለመነሳት ሲሞክርም የመቃብሩ የላይኛው ክፍል ግንባሩን ይገጨዋል
ከዚያም በጨርቅ የተጠቀለለውን ገላውን መንካት ይጀምራል
⇛ይቀጥልና ለብሼ የነበረው ሸሚዜ የታለ?
⇛ቲሸርቴ የታአለ?
⇛ማነው እሱ እርቃኔን አስቀርቶኝ በጨርቅ የጠቀለለኝ ?
⇛የት ነኝ ያለሁት፣ ይህ ቦታ የት ነው?
⇛ይህ ቦታ ለምን ጨለመ ?
⇛ማን ነው ወደዚህ ድቅድቅ ጨለማ ቦታ ያመጣኝ ?
⇛እዚህ ምን እያደረግኩ ነው ይላል ?
መልስ የሚሰጠው አካል የለም
እንደ እሱ አስተሳሰብ ከዚህ አስፈሪ ቦታ ሊያወጡኝ ይረዱኛል የሚላቸውን ቤተሰቦቹን፣ ዘመዶቹን አልያም የጓደኞቹን ስም እየተጣራ የቻለውን ያህል ይጮኻል!!
ነገር ግን ማንም ሰው ምንም አይመልስለትም።
ከዚያም የሆነውን ነገር ሁሉ ይገነዘባል እርሱ ያለው በሙታን መንደር፣ ከመሬት በታች በመቃብር ውስጥ ነው
ይህን ጊዜ ያጋጠመው ነገር ሁሉ ህልም እንዳልሆነ ይረዳል በእርግጥ መሞቱን ይገነዘባል
ከዚያም በዚህ ክፉ ጊዜ የሚደርስለት ብቸኛው ተስፋ አላህ መሆኑን ያስታውሳል።
ለአላህም እያለቀሰ ምህረትን ይጠይቃል፣እንዲህም ይላል
ያ አላህ (አላህ ሆይ) ይቅር በለኝ ይላል ...!!! 😭😭😭😭በህይወት ሳለ ከዚህ በፊት ተሰምቶት በማያውቀው እና በማይታመን ፍርሃት ተውጦ እጅጉን ይጮኻል። የሚደርስለት ግን አያገኝም
ይህ ሰው በህይወት እያለ አላህን የሚፈራ (አላህን የሚገዛ) እና ጥሩ ሰው ከነበረ፣ ለእርሱ ሁለት መላእክቶች ይመጡና ከጎኑ ተቀምጠው መልካምነቱን እያወሱ ያፅናኑታል በመልካምም ያገለግሉታል
በአንፃሩ ይህ ሰው በህይወት እያለ መልካም ስራ ካልነበረው ፣አላህን የሚያምፅ እና በሽርክ ውስጥ ሆኖ (አላህን ያጋራ) ከነበረ
ሁለት አስቀያሚ እና አስፈሪ የፊት ገፅታ ያላቸው መልአክቶች እርሱን በማሰቃየት ህመሙንና ፍርሃቱን ለመጨመር ይመጣሉ።
በዚያ ጭንቅ ጊዜ ሟች እያለቀሰ የአላህን ምህረት እና እዝነት ይለምናል !! ነገር ግን ምንም አይጠቅመውም ምናልባት ከአላህ ምህረት የሚጠይቅበት ትክክለኛው ጊዜ በምድር ላይ በህይወት እያለ ፣ወጣት እና ጤናማ በሆነ ጊዜ ነበር ።ነገር ግን ሁሉም ነገር አክትሟል
አሏህ ሆይ እኔም፣ እናቶቻችን፣ አባቶቻችን፣ ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን እና ውድ ዘመዶቻችን፣በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በትንሹ እና በትልቁ የሰራነውን ወንጀላችንን በእዝነትህ ማርልን !!
አላህ ሆይ ይቅር በለን 🙏🏻
አላህ ሆይ እምነታችን በአንድ አላህ
አሟሟታችንን በላኢላሀ ኢለላህ አርግልን
🤲🤲🤲 #አሚን #አሚን
Hijra Tube ኢስላማዊ ድህረ ገፅ