Zamzam Kadir

Zamzam Kadir Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zamzam Kadir, Women's clothes shop, Addis Ababa.

16/11/2022

Kuweet dubartii Itoophiyaa dabalatee namoota torba du'aan adabde

13/11/2022

Hoji Raawwachiisaa Olaanaa Kutaa Magaalaa Bokkuu Makura Shuumii Booranaa.Ammas Jabaadhu Jabaa keenya.

13/11/2022
12/11/2022

Nageenya Bichaa woyya.

12/11/2022
12/11/2022

Nageenya qofa!!

11/11/2022

OBN TV Qamadii...

A/Dhugaa
B/Soba

Deebii komentii keessa kaayii

09/11/2022


ሀሩንም እጅጉን በመደሰት በሀሳቡ ተስማሙ። በነጋታው ሙሳ እና ሀሩን ያለ ምንም ፍራቻ ወደ ፊርዐውን ቤተ መንግስት ዘልቀው ገቡ።

ከዚያም ፊርዐውንን እንደተገናኙም ወደ አላህ እንዲመለስ'ና በኒ ኢስራኢሎችንም እንዳይበድል፤ ሙሳ እና ወንድሙ ሀሩንም የአላህ መልዕክተኞች መሆናቸውንም አክለው ነገሩት።

ፊርዐውንም ከ10 አመት በፊት እቤቱ ይኖር የነበረውን ሙሳን በትኩረት ሲመለከት አወቀው'ና፦ "አንተ ህፃን ሆነህ እቤቴ አላሳደግኩህም እንዴ!! ያችንም የሠራሃትን ሥራህን አልሠራህምን? አንተም ከውለታ ቢሶቹ ነህ" አለው።

ሙሳም፦"ያን ግዜ ተሳስቼ ነው። ከዚያም እናንተ ትገድሉኛላችሁ ብዬ ሩቅ ሀገር ሸሸሁ። እዚያው ጌታዬም ጥበብን ሰጠኝ።ይህችም የእስራኤልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻደቅባት ጸጋ ናት" አለው።

ፊርዐውንም፦" (ላከኝ የምትለው) የዓለማትም ጌታ ምንድነው" አለው።
ሙሳም፦" የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምታረጋግጡ ብትኾኑ (ነገሩ ይህ ነው)" አለው።

ፊርዐውን ትንሽ ሳቀ'ና ወደ ዙሪያው ያሉትን ሰዎች እየተመለከተ፦"ሚለውን አትሰሙትም እንዴ!" አላቸው።
ሙሳም፦ "የምሥራቅና የምዕራብ በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ ታውቁ እንደኾናችሁ (እመኑበት)" አላቸው።

ፊርዐውንም፦ "ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ" አለው። ሙሳም፦ "እኔ ከአላህ ዘንድ የተላክሁ ስለመሆኔ ማስረጃ ባመጣልህስ?" አለው።
ፊርዐውንም፦ "እስቲ ማስረጃህን አምጣ እውነተኛ ከሆንክ" ሲል ጠየቀ።

ሙሳም ይህን ሲሰማ ብትሯን ጣላት፤ወዲያው ወደ እባብነት ተቀየረች። ጣቱንም በብብቱ አስገብቶ የምታንፀባርቅ ሆና አወጣት። ፊርዐውን እችን ሲያይ፦" አሀ! ይህም ግልፅ ድግምት ነው። እንደውም እንዳንተ ያሉ ድግምተኞች በግዛቴ ብዙ ስላሉ ቀጠሮ እንያዝ'ና እንገናኝ ማን እንደሚያሸንፍ እናያለን" አለው።

ሙሳም በዚህ ተስማምቶ ትልቅ ህዝባዊ በአል በሚከበርበት ቀን ቀጠሮ ተያይዘው ያን ቀን በሰላም ተለያዩ።

ቀን ቀንን ወራት ወራትን እየተካ ሙሳ እና ፊርዐውን የያዙት ቀጠሮ ወቅቱን ጠብቆ መጣ። ህዝቡ የዛሬዋን የቁርጥ ቀን ፍፃሜ ሊመለከት ለቁጥር አዳጋች ሆኖ በሰልፍ ተሰብስቧል።

ድግምተኞችም እድሜ ልካቸውን ሲጠበቡበት የከረሙትን አስደናቂ ድግምት ይዘው ከሙሳ ሊፋለሙ ሰልፍ ይዘው ቁጭ ብለዋል። የድግምተኞች ብዛት 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ነበር። የድግምተኞቹ ቁጥር 30,000 ከሆነ የተመልካቹን ቁጥር መገመት አያዳግትም።

ተመልካቹም፣ ድግምተኛውም፣ ንጉሱም ሙሳም ሁሉም ቦታውን ከያዘ በኋላ ድግምተኞቹ ቀስ ብለው ፊርዐውንን፦ " ግን እኛ ካሸነፍን ምንድነው ሽልማታችን?" አሉት።
ፊርዐውንም፦ "እኔ ዘንድ የቅርብ ባለሟል ትሆናላችሁ" አላቸው።

አሁን ትንቅንቁ ሊጀመር ነው፤ ፊርዐውን ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፣ ሙሳ እና ወንድሙ ከአንድ ጎኑ ሲሆኑ ድግምተኞቹም ከአንድ ጎን ቁመዋል። ህዝቡ የትንቅንቁን ፍፃሜ ለማየት እጅጉን ጓግቷል።

ሙሳም ትንቅንቁ ከመጀመሩ በፊት አንድ አፍታ ወደ ድግምተኞቹ በመዞር፦ "ወዮላችሁ በአላህ ላይ ውሸትን አትቅጠፉ፡፡ በቅጣት ያጠፋችኋልና፡፡ የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ" አላቸው።

ድግምተኞቹም በጣም ተደናግጠው እርስ በርስ፦ "ይህማ የድግምተኛ ንግግር አይደለም " መባባል ጀመሩ። ከዚያም ፊርዐውን ውድድሩ እንዲጀመር ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ድግምተኞቹም ወደ ሙሳ በመዞር፦ "አንተ ትጀምራለህ ወይስ እኛ እንጀምር?" አሉት። ሙሳም፦"እናንተው ጀምሩ" አላቸው።

ሰላሳ ሺህ ድግምተኞ በእጆቻቸው የያዙትን ገመዶች ወደ ፊት መወርወር ጀመሩ። የወረወሩት ገመድ ተከማምሮ፣ ተከማምሮ ትልቅ ዳገት ካከለ በኋላ ድግምተኞቹ የተመልካቹን አይን የሚያየውን ገመድ እባብ እንዲያስመስልላቸው አድርገው ደገሙባቸው።

ሰዉ ሲያይ ተራራ የሚያክል የእባቦች ክምር ላይ እርስ በርስ እባቦች ይታራመሳሉ። ህዝቡ በፍርሀት ተውጧል፣ ትዕይንቱ በጣም ያስደነግጣል፣ አለማችን አስተናግዳ የማታውቀው የድግምት አይነት ተከስቷል።

ሙሳ ይህን ሲያይ እንዳይሸነፍ እና ህዝቡ ከእምነት እንዳይርቅ ፈራ። አላህም የሙሳን ሁኔታ እንዳይፈራ ካረጋጋው በኋላ፦"አንተም በእጅህ የያዝካትን በትርህን ጣላት" አለው።

ሙሳም በትሯን ሲጥላት በትሯ ወዲያው ወደ ትልቅ ዘንዶነት በመቀየር ድግምተኞቹ እባብ አድርገው የጣሉትን ሁሉ አንድ በአንድ በቅፅበት በልቶ ጨረሳቸው።

የሙሳ ዘንዶ የድግምተኞቹን እባቦች ውጦ እንዳጠናቀቀ በኋላ ሙሳ ሄዱ ሲይዘው ተራራ ሚያህል የድግምት እባቦችን የዋጠው ዘንዶ ወዲያው ተመልሶ ወደ በትርነት ተቀየረ።

ህዝቡ ሁሉ የሚያየውን ማመን ተስኖት አይኑን አፍጥጦ ይመለከታል። የድግምተኞቹ አለቃ አይነ ስውር ነበር'ና ድግምቱን ጣለ እንጂ ምን እንደተከሰተ ለማየት አልታደለም ነበር።

ድግምተኞቹም ለአለቃቸው፦ "የጣልናቸውን ድግምቶች በሙሉ የሙሳ በትር ወደ ዘንዶ ተቀይሮ ዋጣቸው" አሉት።
አለቃቸውም፦ "ምንም ትርፍራፊም አላስቀረም?" አላቸው።
ድግምተኞቹም፦ "አዎን ከዚያ በኋላ እንደውም ተመልሶ ወደ በትርነቱ ተቀየረ" አሉት።

ይህን ግዜ ማየት የተሳነው የድግምተኞቹ አለቃ፦ "ይህ ሙሳ የሚያደርገውማ ድግምት አይደለ የፈጣሪ ተዐምር ነው" ብሎ በፊቱ በመደፋት ሱጁድ አደረገ።

አለቃቸው ሱጅድ ሲያደርግ የተቀሩትም ድግምተኞች የአለማት ጌታ ለሆነው አላህ ክብር እጅ ነስተው ግንባሮቻቸውን ከመሬት አላትመው ሱጅድ ወረዱ።

ከዚያም፦ "የአለማት ጌታ በሆነው እና የሙሳም የሀሩንም ጌታ በሆነው አላህ አምነናል" አሉ።

ፊርዐውን ይሄን ሲሰማ በህዝቡ ፊት ከፍተኛ እፍረት ተሰምቶት፦ "ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ (በሙሳ) አመናችሁን! እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ አለቃችሁ ነው፡፡

እናንተን ደግሞ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማናጋት (ግራናቀኝን በማፈራረቅ) እቆራርጣችኋለሁ፡፡ በዘምባባም ግንዶች ለይ እሰቅላችኋለሁ፡፡ ማንኛችንም ቅጣቱ በጣም ብርቱ የሚቆይም መኾኑን ታውቃላችሁ" ብሎ ዛተባቸው።

ፊርዐውን ዛቻውንም እግሮቻቸውን'ና እጆቻቸውን በመቆራረጥ እውን ያደርግ ጀመር። እነሱም እግሮቻቸውን እና እጆቻቸውን ሲቆርጧቸው፦" ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፡፡ ሙስሊሞች ኾነን ግደለንም" እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።

ሰላሳ ሺህ ድግምተኞች ጠዋት ከቤታቸው ሲወጡ ካፊሮችና በአላህ ላይ ያመፁ ነበሩ፤ ማታ ላይ ደሞ ሸሂዶች ሆኑ።

ሙሳ ዐሰ ሰው ገድሎ እንዳይበቀሉት ሰግቶ ከግብፅ እንዲወጣ የመከረው ሰውዬ የፊርዐውን ሽንፈት ግልፅ መውጣቱን ሲመለከት በህዝቡ ፊት ለሙሳ ዐሰ ማመኑን አወጀ።

ከዚያም ከድግምተኞቹ ጋር አንድ ላይ ተሰቀለ። ያን ቀን በሙሳ አሸናፊነት ውድድሩ ተጠናቀቀ። ያን ቀን ሀቀ ወደ ላይ ከፍ ብላ ውሸትም አንገቷን ደፋች።

በማግስቱም ትናንትና የተሰቀለ የሙሳ የመካሪው ሚስት የሆነችው ሴት የፊርዐውንን ልጅ ተቀጥራ በማበጠር ላይ ሳለች፤ ማበጠሪያው ከእጇ ሲወድቅባት፦ "ቢስሚላህ (በአላህ ስም)" አለች።

የፊርዐውንም ልጅ፦ "አባቴን ለማለት ፈልገሽ ነው" አለች።
አበጣሪዋም፦ "አይ አላህ ማለት የኔም ያንችም የአባትሽም ጌታ ነው" አለቻት።
ልጅቷ ወዲያው ብድግ በማለት ሄዳ ለአባቷ (ፊርዐውን) የሆነውን ሁሉ ነገረችው። ፊርዐውንም አበጣሪዋን ከነ ህፃን ልጇ በማስጠራት፦ "ጌታሽ ማን ነው" አላት። አበጣሪዋም፦"የኔም የንተም ጌታ አላህ ነው" አለችው።

ፊርዐውን ይህን ሲሰማ ነሀስ ቀልጦ በትልቅ የብረት ጋን ውስጥ እንዲሞላ ካደረገ በኋላ የተቀሩ ልጆቿንም ሰብስቦ አንደኛውን በቀለጠው ነሀስ ውስጥ ሲያስገባው ልጇ አይኗ እያየ ስጋው ከአጥንቱ ተለያይቶ ተንሳፈፈ።

ፊርዐውንም ዞር አለ'ና፦ "አሁንስ ጌታሽ ማን ነው" አላት። እሷም ከአቋሟ ምንም ሳትዛነፍ፦"የኔም ያንተም ጌታ አላህ ነው" አለችው።

አሁንም አንድ ልጇን አምጥቶ በነሀስ ቅላጭ ውስጥ አስገብቶ ከገደለ በኋላ ሀሳቧን ሲጠይቃት ከአቋሟ ፍንክች አላለችም።

እንዲህ እንዲህ እያለ ልጆቿን በሙሉ በቀለጠ ነሀስ ውስጥ ዘፍቆ ፈጃቸው'ና በጀርባዋ የተሸከመችው ህፃን ብቻ ቀረ። እሱንም ወታደሮቹ በቀለጠው ነሀስ ውስጥ ሊወረውሩት ሲሉ ሆዷ አልቻለም'ና ልታፈገፍግ ሆነች።

ገና ጡት የሚጠባውም ህፃን፦ "እናቴ እውነት ላይ ነሽ'ና ባለሽበት ፅኚ" አላት። እሷም ከእቅፏ ያለውን ህፃን ለአላህ ስትል ለወታደሮቹ አሳልፋ ሰጠቻቸው'ና ከወንድሞቹ ቀላቀሉት። አሁን የሷ ተራ ነው፤ ፊርዐውንም፦ "ከመሞትሽ በፊት ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት። እሷም፦"ፍቃደኞች ከሆናችሁ የኔን እና የልጆቼን አጥንቶች ሰብስባችሁ በአንድ ጉድጓድ ቅበሩን" አለች። ኑዛዜዋንም ፈፀሙላት።

ይህ ሁሉ ሲሆን በቅርበት ትከታተል የነበረችውም የፊርዐውን ሚስት (ኣሲያ) የአበጣሪዋ ሩህ ሲወጣ መላዕክት ሩኋን አጅበው ወደ ሰማይ ሲወጡ አላህ ግርዶሹን ከፍቶላት ተመለከተች። ( የፊርዐውን ሚስቱ ሙስሊም ናት ነገር ግን ማንም አያውቅባትም)

ወደ ፊርዐውንም ዘወር ብላ፦ "ተጠንቀቅ! አላህን እንዴት እንዲህ ትዳፈራለህ?" አለችው። ፊርዐውንም፦ "ይህችን አበጣሪ የለከፋት ልክፍት ብቻ ለክፎሽ እንዳይሆን" አላት።

ባለቤቱም፦ "እኔ ምንም አልተለከፍኩም። ነገር ግን የኔም ያንተም የአለማትም ሁሉ ጌታ በሆነው በሀያሉ አላህ አምኛለሁ " አለችው።

ፊርዐውን ቁጣውን መቆጣጠር እያቃተው የሚስቱን እናት በማስጠራት፦ "ልጅሽ በአበጣሪዋ አይነት ልክፍት ተለክፋለች። ይህ በምትለው የሙሳ ጌታ የማትክድ እንደሆን ሞትን አቀምሳታለሁ" አላት።

እናትም ልጇን በህይወት እንድትቆይላት ፊርዐውን የሚላትን ነገር እንድትታዘዝ ለመነቻት። የፊርዐውን ሚስትም፦ "አላህን ካጂ የምትዪውን እንኳን መቼም አላደርገውም" ብላ መለሰችላት።

ፊርዐውንም በገዛ ሚስቱ ላይ የቅጣት አርጩሜውን ሊያወርድባት 4 ችካሎችን መሬት ላይ አስቸክሎ እሷን በአራት ማዕዘን በመወጠር አሰቃይቶ ገደላት።

ያኔ ነፍሷ ልትወጣ ስትል፦ "ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤትን ገንባልኝ፡፡ ከፈርዖንና ከስራውም አድነኝ፡፡ ከበደለኞቹ ሕዝቦችም አድነኝ" ብላ ዱዐ አደረገች። አላህም በዚያች ቅፅበት ለሷ በጀነት ያዘጋጃላትን እንድትመለከት ሲያደርጋት ፈገግ አለች።

ፊርዐውንም፦ "ይሄን እብደት ተመልከቱ እየተቀጣች ትስቃለች" ብሎ ሳይጨርስም አሲያ ነፍሷ ወጣች። ፊርዐውን የህዝቡን ሁኔታ ሲመለከት ሁሉም የሙሳ ነገር እንዳስደነገጠው እና ህዝቡ ሁሉ ወደ ሙሳ እምነት እንዳይገባ ስጋት አደረበት።

ፊርዐውንም የግንባታ ሚኒስቴር ለሆነው ሀማን፦ "ሀማን ሆይ ትልቅ ግንባታ ወደ ሰማይ ገንባልኝ። እስቲ የሙሳን ጌታ አየዋለሁ" አለ። ሀማንም ግንባታው ሰባት አመታትን ያስቆጠረ በጣም ረጅም ህንፃ መገንባት ጀመረ።

ሙሳ ይህን ሲመለከት በውስጡ ስጋት አደረበት። ይህን ግዜ አላህም፦ "ሙሳ ሆይ! ዝም በለው እሱ በሰባት አመት የገነባውን በቅፅበት እደረምሰዋለሁ" አለው።

ግንባታውም ተገንብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ አላህ ጂብሪልን አዘዘውና ጂብሪል ግንባታውን በቅፅበት ደረመሰው። ፊርዐውንም እጅጉን በመናደድ በኒ ኢስራኢሎችን ግብፃውያን እንዲያሰቃይዋቸው ትዕዛዝ ሰጠ።

ግብፃውያንም ወሰንን ያለፈ ስቃይ እና እንግልትን በበኒ ኢስራኢሎች ላይ ያደርሱባቸው ጀመር። በኒ ኢስራኢሎችም የሚደርስባቸውን ስቃይ እና እንግልት መቋቋም ሲያቅታቸው ሙሳ ዘንድ መላ እንዲላቸው ስሞታ አቀረቡ። ሙሳም ኢስራኢላውያን እንዲታገሱ እና ወደፊትም ድሉ የነሱ መሆኑን አበሰራቸው።

ሙሳ ምንም እንኳ ዘወትር ፊርዐውንን እና ህዝቦቹን ወደ አላህ ቢጣራም ከጥመታቸው ለአፍታ አልተወገዱም ነበር። አለህም ይህን ሲመለከት ተከታታይ ዶፍ ዝናብ በመልቀቅ አዝርዕቶቻቸውን እና ፍራፍሬዎቻቸውን እንዳልነበረ አድርጎ በጎርፍ አጥለቀለቀባቸው።

ግብፃውያንም ሙሳ ጋ በመሄድ፦"እባክህ ጌታህን ለምን'ና ይሄን መቅሰፍት አስወግድልን፤ ይሄን ይቅር ብሎን ካስወገደልን እኛም እናምናለን ኢስራኢላውያንንም እንለቅልሀለን" አሉ።

ሙሳም አላህን በመማፀን ዝናቡ እንዲቆም አደረገላቸው በጎርፍ የተጥለቀለቁትም ፍራፍሬዎች እና አዝርዕቶች ዳግም አቆጠቆጡ። ከዚያም ግብፃውያኑም ዳግም ወደ ክህደታቸው ተመለሱ።

አላህም ያን ግዜ የአንበጣ መንጋ ለቀቀባቸው'ና አዝርዕቶቻቸውን ፈጀባቸው። ግብፃውያንም አሁንም ወደ ሙሳ በመሄድ የተለመደውን ቃል በመግባት ልመናቸውን ቀጠሉ።ሙሳም፦"እሽ ካመናችሁ ጌታዬን እለምንላችኋለሁ" በማለት አላህን ተማፅኖ የመጣውን በላእ አላህ አነሳላቸው።

መቅሰፍቱ ሲወገድላቸው አሁንም ወደ ቀድሞው ክህደታቸው ተመለሱ።አላህም ምንም አይሳነውም'ና የነቀዝ መንጋ ለቀቀባቸው። ያስቀመጡትን እህልም ሚበሉትን እስኪያጡ ድረስ እንዳለ ፈጀባቸው።

አሁንም ሙሳ ዘንድ በመምጣት ከጌታህ አስታርቀን እያሉ ስሞታ ማሰማት ጀመሩ። ሙሳም ዱዓእ አድርጎላቸው ነቀዙ ከግብፅ ምድር ጠፋላቸው። ነቀዙ ሲጠፋ እነሱም ዳግም ወደ ክህደታቸው ተመለሱ።

አላህም የእንቁራሪት መንጋ ለቀቀባቸው። ድስቶቻቸውን፣ ምግቦቻቸውን እና ቤቶቻቸውን እንቁራሪቶች ለጉድ ወረሯቸው። ይህንንም መቋቋም ሲያቅታቸው ወደሙሳ በመሄድ፦"ከአሁን በኋለ አይለምደንም" በማለት የተለመደውን ቃል ገቡለት።

ሙሳም ጌታውን ለምኖ መቅሰፍቱን አስወገደላቸው። ነገር ግን ልክ መቅሰፍቱ እንደተወገደላቸው ነበር ግብፃውያን ወደ አመፃቸው ዳግም የተመለሱት።

ያን ግዜ አላህም የግብፃውያንን ውሀ በደም በከለው።ኢስራኢላውያን እና ግብፃውያን ከአንድ ምንጭ እየተጠቀሙ ኢስራኢላውያን ንፁህ ውሀ ሲጠጡ ግብፃውያን ግን ውሀቸው ወደ ደምነት እየተቀየረ ሚጠጡትን አጡ።

እነዚህ ከሀዲያን አሁንም መሸሻ የላቸውም'ና ዳግም ወደ ሙሳ በመሄድ ልመናቸውን አጠናክረው ቀጠሉ።ሙሳም ዱዓ አድርጎ ውሀቸውን ሲያጠራላቸው ዳግም ወደ ክህደታቸው ተመለሱ፡፡

ክፍል 3 ይቀጥላል...

Sefwan Sheik Ahmedin

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zamzam Kadir posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zamzam Kadir:

Share