15/04/2026
⚜️ ታም ፎርድ (Tom Ford) ⚜️
ታም ፎርድ እ.ኤ.አ. በ 1961 በቴክሳስ፣ አሜሪካ ተወለደ። መጀመሪያ ላይ በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጥበብ ታሪክ (Art History) ያጠና የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ግን ትኩረቱን ወደ ትወና እና አርክቴክቸር (Architecture) ቀየረ። በፓርሰንስ ዲዛይን ትምህርት ቤት (Parsons School of Design) በአርክቴክቸር ተመርቋል።
ሆኖም ግን፣ በትምህርቱ የመጨረሻ ዓመት ላይ ለፋሽን ያለው ፍላጎት በማደጉ ወደዚያው ዘርፍ ለመግባት ወሰነ። ይህ የሚያሳየው አንድ ሰው በአንድ ዘርፍ ብቻ መገደብ እንደሌለበት እና አስፈላጊ ሲሆን የንግድ ስልቱን እንደ አዲስ የመቅረጽ ድፍረት ሊኖረው እንደሚገባ ነው።
ታም ፎርድ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ ጣሊያኑ ኩባንያ Gucci ሲቀላቀል፣ ድርጅቱ በከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ እና በክስረት አፋፍ ላይ ነበር። በ1994 የፈጠራ ዳይሬክተር (Creative Director) ሆኖ በተሾመ በአንድ ዓመት ውስጥ የድርጅቱን ገቢ በ90% አሳደገ።
የቆየውን እና አሰልቺ የነበረውን የጉቺ ስታይል ወደ ዘመናዊና ማራኪ ወደሆነ ፋሽን ቀየረው። በኋላም Yves Saint Laurent (YSL) የተባለውን ድርጅት Gucci (ጉቺ) ሲገዛው፣ እሱ የሁለቱንም ድርጅቶች የፈጠራ ስራዎች በበላይነት መርቷል።
ከጉቺ (Gucci) ጋር በ2004 ከተለያየ በኋላ፣ በ2005 TOM FORD የተባለ የራሱን የንግድ ምልክት (Brand) አቋቋመ። መጀመሪያ ላይ መነጽሮችን እና መዋቢያዎችን (Cosmetics) በማምረት ጀመረ፣ ከዚያም ወደ ወንዶች እና ሴቶች አልባሳት በመግባት በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ውድ የቅንጦት ብራንዶች አንዱ እንዲሆን አደረገው።
ታም ፎርድ በፋሽን ብቻ አልተገደበም። ጎበዝ የፊልም ዳይሬክተርም ነው "A Single Man" እና "Nocturnal Animals" የተባሉ እውቅና ያተረፉ ፊልሞችን ሰርቷል።
#ፋሽን