Shop in ethio

Shop in ethio We are a professional shoe supplier, we will provide you with the best and most affordable shoes. Welcome to our website!

Company Name: Beijing Meishunya Shoes Co., Ltd. Company Address: No. 1303, Cultural Building, No. 139, Shaoshan North Road, Chaoyang Street, Furong District, Changsha City, Hunan Province.

01/12/2021

የተለያዩ ያገለገሉ ስልኮችን እዚህ ፔጅ ላይ ያገኛሉ

samsung J4+ 4800birr
01/12/2021

samsung J4+ 4800birr

Iphon6 5000birr only
01/12/2021

Iphon6 5000birr only

17/05/2018

ኃያላን ቀስት ተሰባብሮ
አለቅነትን ስልጣናትን ሽሮ
በግርማው ያለ ሁሉን እየረታ
ዛሬም ይገዛል የጌቶች ጌታ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ

ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው
መንግሥቱም ጽኑ ነው ማንም አይረታው
የተነሱበትን ሁሉንም ገልብጦ
ብቻውን ይገዛል እርሱ ብቻ ጸንቶ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ

ጐርደድ እያለ ከጠላት ሰፈር
ሺ ጦር ቢሰለፍ የማይበገር
ድምጹ ነጐድጓድ የሚያስፈራራ
ሁሉን የረታ ተራ በተራ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ

ነጉሰ ነገሥት ግርማዊ ተብለው
በምድር ሲኖሩ ክብርን ተጋፍተው
ዛሬ ተረስተው አፈር ሆነዋል
ሞትን ፈንቅሎ ኢየሱስ ግን ተነስቷል

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ
ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ

ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው
መንግሥቱም ጽኑ ነው ማንም አይረታው
የተነሱበትን ሁሉንም ገልብጦ
ብቻውን ይገዛል እርሱ ብቻ በልጦ

አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ (፪x

30/04/2018

እያለፈ ነው ኢየሱስ እያለፈ ነው አ እያለፈ ነው እባቴ እያለፈ ነው

30/04/2018

(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች �?ዕራ�?? 1)
----------
2፤ በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፤

3፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

4፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤

5-6፤ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።

7፤ እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤

8፤ እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።

9፤ ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

10፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።

11፤ ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና።

12፤ ይህንም እላለሁ። እያንዳንዳችሁ። እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ።

13፤ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?

14-15፤ በስሜ እንደ ተጠመቃችሁ ማንም እንዳይል ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ከእናንተ አንድን እንኳ ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

16፤ የእስጢፋኖስንም ቤተ ሰዎች ደግሞ አጥምቄአለሁ፤ ጨምሬ ሌላ አጥምቄ እንደ ሆነ አላውቅም።

17፤ ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝምና፥ ወንጌልን ልሰብክ እንጂ፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም።

18፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።

19፤ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተጽፎአልና።

20፤ ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚች ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?

21፤ በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።

22፤ መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥

23፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥

24፤ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።

25፤ ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።

26፤ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።

27፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤

28፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገ

16/04/2018

GOD IS LOVE ALL THE TIME

18/01/2018

(ወደ ሮሜ ሰዎች �?ዕራ�?? 12)
----------
1፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።

2፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

3፤ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።

4፤ በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥

5፤ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።

6፤ እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤

7፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤

8፤ የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።

9፤ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤

10፤ በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤

11፤ ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤

12፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤

13፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።

14፤ የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ።

15፤ ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።

16፤ እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።

17፤ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።

18፤ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።

19፤ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።

20፤ ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።

21፤ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።

16/01/2018

ተነግሮ የቱ ይተዋል
የጌታ ሥራ እጅጉን በዝቷል
ከየት አንስቼ ስንቱን ላስታውስ
በየማለዳ ሁልጊዜ አዲስ

ነግሮ ሊጨርስ ማነው የቻለ
ተዓምራቶቹን እያስተዋለ
የጌታን ክብር ታላቅነቱን
የፍቅሩን ብዛት ደግሞ ጥልቀቱን

ከመጣው (ም) ሁሉ ያለፈ
ከህሊናችን ሞልቶ የተረፈ
ነውና ታላቅ ሥራው ብዙ
ለዚህ ለጌታ ምሥጋናውን አብዙ

ይሄ ሁሉ ፍጥረት የሚያመሰግንህ
ይሄ ሁሉ ክብር ለአንተ የተገባ
ስለሆንክ ገዢ ብርቱና ገናና
አሁንም አሁንም ይብዛልህ ምሥጋና

ፍጥረታት በሙሉ በግዛትህ ናቸው
ስለዚህም በአንተ ብዙ ደስታ አላቸው
በራሳቸው ቋንቋ ይመሰክራሉ
የእግዚአብሔር ሥራ ፍጥረት ነን እያሉ ሃሌሉያ

የለህም መሳይ (፫x) በምድር በሰማይ
የለህም እኩያ (፫x) ኦ ሃሌሉያ

በደማቅ ብርሃን እራስክን ሰውረህ
ከፍ ካሉት በላይ እጅግ ከፍ ብለህ
ድካምና ዝለት ሳያውቅህ እርጅና
ትናንትና ዛሬም ሁልጊዜ ገናና

ንጉሥ በንግሥናው አዋቂው በዕውቀቱ
ሊመስልህ ሲሞክር ሲጥር አይ ሰው ከንቱ
ነገር ግን ከአንተ ጋር ሁሉን ሲያስተያይ
ሁሉን ብሎ ያልፋል የለህም መሳይ ሃሌሉያ

የለህም መሳይ (፫x) በምድር በሰማይ
የለህም እኩያ (፫x) ኦ ሃሌሉያ

እግዚአብሔር እንዲህ ይህን ይመስላል
ተብሎ በቃላት መች ይገለጻል
አንዲያ ልጁ በቀኙ ያለው
ተረከው እንጂ ሌላ ማን አየው

ሰማይ ተቀምጦ እግሮቹ ምድር
ታላቅነቱ እንዴት ይነገር
መግለጫ ቋንቋ ቢጠፋም ቃሉ
እንዲሁ ብቻ ተመሥገን በሉ

የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል
የጌታ ዝና እጅጉን በዝቷል
ከየት አንስቼ ስንቱን ላስታውስ
በየማለዳ ሁልጊዜ አዲስ

የለህም መሳይ (፫x) በምድር በሰማይ
የለህም እኩያ (፫x) ኦ ሃሌሉያ (፪x)

02/01/2018

ስለ ጻድቅ ሰው የሚሞት መቼም ቅርብ ይገኝ
እንዴት ተገኘ ብዬ አያስደንቀኝ
ስለ ቸር ሰው ቢሆን እንደዚሁ ነኝ እኔ
ጊዜዬን በዚህ አልፈጅም ለምኔ ለምኔ
አንድ ነገር አለ እኔን ያስደነቀኝ
ደካማ እያለሁ ሳላውቀዉ ያወቀኝ
ሃጥያት ያራቀኝ ከመንገድ አውጥቶ
ኢየሱስ መለሰኝ ሞቴን ሁሉ ሞቶ አሃ

አዝ፦ እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (፪x)

በአንዷ አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጥያተኛ ሆኑ [1]
ከዲያብሎስ ጋራ ገሃነም ሊጣሉ
በኢየሱስ መታዘዝ ከፍርድ አምልጠናል [2]
የመንግሥተ ሠማይ ወራሽ አድርጐናል

አዝ፦ እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (፪x)

ዝቅ ዝቅ ያለው ኢየሱስ ከሁሉ ይበልጣል
ለእኔ ባረገው ነገር ልቤ ተሸንፏል
የፍቅርንም ሚስጥር ያወኩት በእርሱ ነው
አቀብት ዳገቱን የወጣዉ ለእኔ ነው
በደሙ ተድቄ ከቁጣ ድኛለሁ
ጠላትነት ቀርቶ ወገን ተብያለሁ
ሰላሙን ሰብኮኛል የሰላም አለቃ
የጭንቀቱ ዘመን ከእኔ ላይ አበቃ አሃ

አዝ፦ (እንዴት ያለ ፍቅር ነው)
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shop in ethio posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share