Yalew Abate Worku

Yalew Abate Worku Work is life disiener

21/07/2023

👉⛪️💒በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
✝ውድ የጎላ ቅዱስ መርቆሪዎስ የልማትና በጎ አድራጎት አባላት ✝
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንዲህ አሉ፦ ማንም ቢሰድብህ ስለ መሰደብህ ሳይሆን ስለ ሰደበህ ሰው አስብ። ያ ሰው ወንድምህ ነው። በፍቅር የተሞላህ መንፈሳዊ ሰው እንደመሆንህ መጠን አንተን በመስደብ ኃጢአት ላደረገው ወንድምህ ምን ልታደርግለት እንደምትችል ታስብ ዘንድ ይገባሃል። በእርግጥ አንተን የተሳደበበት ስድብ በድኅነቱ መግቢያ ላይ ቆሞ ይከለክለውና በዚሁ ሳቢያ ውድ ነፍሱ ወደ ሲዖል ትወርድ ዘንድ አትሻም። በመሆኑም ያንን ኃጢአት ቆጥሮ እንዳይቀጣው ይልቁንም ይቅር እንዲለው እግዚአብሔርን ትጠይቅለታለህ ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ካለው ኃጢአት እንዲያወጣውና ዳግመኛ አንተን ሆነ ሌሎችን በመስደብ እንዳይበድል ልትጸልይለት ይገባል።
ወስብሐት ለእግዚአበሔር ።

11/11/2022

ኬኒያ ናይሮቢ

ጉዳዩ "አሳሳቢ" ነው‼

የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች ናይሮቢ ላይ እያካሄዱት ባሉት ውይይት የሕወሃትን ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ዙሪያ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል። ሌሎች ታጣቂዎች ከትግራይ መቼ ይወጣሉ? የሚለው ጉዳይ ግን "አሳሳቢ" እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። ከትጥቅ ማስፈታት በተጨማሪ ለትግራይ የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንደገና ማስቀጠልና ሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ክልሉ ማስገባት የውይይት አጀንዳዎች መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል። ውይይቱ ትናንት ይጠናቀቃል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ሲሆንም፣ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አፍሪካ ኅብረት በጉዳዩ ዙሪያ ያወጣው መረጃ የለም። (ዋዜማ)

10/07/2022

💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠
/(ማቴ ፫:፫/)

✝እንኳን አደረሰን!!

🛑 ዝክረ ቅዱሳን ላልደረሳቸው እናድርስ እናስፋ ስለ ሃገራችን እንጸልይ ንስሃ እንግባ!!🛑

💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/

🔷ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

🛑ስለ ንስሃ🛑

✝ከቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንማራቸው 7 ነገሮች።

፩, 🛑ቅዱስ አብረሃምን መምሰል( ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘ)::

፪, 🛑ዓለምንና የዓለምን ነገሮች መታው።

፫, 🛑የንስሃ ሕይወት( ንስሃን በትጋት መፈጸም)።

፬, 🛑መታዘዝ (የሚታዘዘውን ሳያጓድል መስራትን)።

፭, 🛑ለሌሎች መኖርን።

፮, 🛑በሰው አለመፍረድን።

፯, 🛑ትሕትናን።
እነዚህን እናስተውላቸው!!!

✝ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!✝

🛑እናስተውል!!🛑
1፡ ❇️👉ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡
2፡ ❇️👉ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡
3፡ ❇️👉በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡
4፡ ❇️👉የበጎ ለውጥ እናት *ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ* ናቸው

✝ 5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።
1, 🛑አላማ

2 ,🛑እምነት

3,🛑ጥረት

4 🛑ጥንቃቄ

5🛑ጽናት
=>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️

" ❇️ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::❇️
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

29/05/2022





ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ።

እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል። አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ።

ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል ።

ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ።

ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር።

እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል።

እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።

( )

06/03/2022

#ቅድሰት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ)

ቅድሰት የዐቢይ ጾም ሑለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡ የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ቅዱስ›› የሚለው ቃል ለሰዎች፡ ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ፡ ለዕለታት ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም ይህንን ሲያስተምረን ነው፡፡ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡

ብርሃን ከጨለማ ጽድቅ ከኃጢአት ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና›› ያለንም ለዚህ ነው፡፡ /1ተሰ 4÷7/ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን አላማ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች እንዲህ ገልጾላቸዋል ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሰማያዊ ሥፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ብሎ ካመሰገነ በኋላ ‹‹ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳን ንጹሐንና ያለነውር በፍቅር ያደርገን ዘንድ ለእርሱ መረጠን›› ኤፌ 1፡3-4 አስቀድሞ ስለወደደንና ስላከበረንም ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጅቶ በእጆቹ ካበጀን በኋላ የሥነ ፍጥረት ዘውድ አድርጎ በገነት አኖረን ፡፡( ዘፍ 1፡26፤መዝ 8፡1)

የቀደመው አዳም አታድርግ የተባለውን በማድረጉ በንዝህላልነትና በስንፍና በከይሲ ዲያብሎስም ምክር ተዋረደ፡፡ በሞተ ሥጋ ላይም ሞተ ነፍስ ፤በርዕደተ መቃብር ላይ ርዕደተ ሲኦል ተፈረደበት፡ በባሕርዩ ሞት ገባበት፡ ተዳደፈ፡፡ ክፉ ፍትወታት የሚያጠቁትና የሚያሸንፉት የዲያብሎስና የኃጢአት ባርያ ሆነ፡፡ በማይለወጥ ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ግን ጠፍተን እንድንቀር አልተወንም፡፡ በሰጠን ተስፋ፡በተቆጠረው ሱባኤና በተነገረው ትንቢት መሰረት ዘመኑ ሲደርስ በተዋህዶ ሰው ሆነ፤ የተዋረደ ሥጋችንን አከበረ፡፡ በከበረ ደሙ ዋጀን፤ ከኃጢአታችን አጠበን፡፡ በእርሱ ምክንያት የእግዚአብሔር ልጆች ተባልን ፡፡ጌታችንና መድኃኒታችን ሰው የሆነውና ለመዳናችን የሆነውን ዋጋ ሁሉ የከፈለው ለእኛ ያለውን ፍቅርና ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ ለእኛ ለማሳየት ነው፡

17/07/2021

ወይ
ጊዜ

ወይ
ዘመን

ወይ
ትንቢት

ደረሰ
መሰለኝ

።

21/06/2020

merkoriwos

17/05/2020
አ           ......             አ                                       ቤ                                            ቱ   ...
29/04/2020

አ ...... አ
ቤ
ቱ

ይ
ቅ
ር

በ
ለ
ን

Address

Wollo
Addis Ababa
YALEW1234

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yalew Abate Worku posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yalew Abate Worku:

Share