Hoodan Cabdi

Hoodan Cabdi Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hoodan Cabdi, Baby & children's clothing store, Jigjiga, Addis Ababa.

18/06/2026
18/06/2026
18/06/2026
18/06/2026

ለነጋችን ዛሬ ተስፋን እንትከል!

የብልፅግና ፓርቲ ልዩ ኢኒሼቲቭ ከሆኑት ዉስጥ አንዱ በየአመቱ ክረምት ከመግባቱ ቀደም ብሎ የሚጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ነዉ። ይህ ሁሉም ዜጎች ያለ ልዩነት በሚሳተፉበት በዚህ አገራዊ ንቅናቄ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገብናቸው ስኬቶች መላውን ዓለም ያስደመመ ታሪካዊ ምዕራፍ ነዉ።

ባለፉት ዓመታት በሰፊዉ ህዝባችን በተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ንቅናቄ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠሩ የተሸረሸሩ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ፣ የደረቁ ምንጮችና አዳዲሶችም እንዲፈልቁና የከርሰ-ምድር ውሃ እንዲጨምር ተደርጓል። ይህም ተከተሞች ዉበትና ለዜጎች ማረፊያ ጥላ ሲሆኑ፣ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ የአየር ንብረትን ተቋቁመው ምንትና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ መሠረት ጥሏል።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። በየዓመቱ የሚተከሉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፍራፍሬ፣ የቡና እና የቅመማ ቅመም ችግኞች የዜጎችን አመጋገብ ከመቀየር ባለፈ ለሀገር ውስጥ ገበያና ለውጭ ኤክስፖርት የሚሆኑ ምርቶችን በማምራት የኢኮኖሚ አቅማችንን እያሳደጉ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ዜጎቻን በማስተባበር አዳዲስ ታሪክ መስራት እንደምንችል በተግባር ያሳየችው ይህ ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአለም አደባባይ የአረንጓዴ ልማት ተምሳሌት አድርጓታል። የመሬት የመሬት መሸርሸር፣ የአፈር እጥበት፣ ድርቅ፣ የሙቀት መጨመርንና የዝናብ መዛባትን በመከላከል ረገድ ለአለም አቀፉ የአየር ንብረት ሚዛን መጠበቅ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያበረከተችው ጉልህ አስተዋፅኦ በታላላቅ የዓለም መድረኮች ላይ ከፍተኛ አድናቆትንና እውቅናን አትርፎልናል።

ህዝባችንን ከጎናችን አሰልፈን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ያስመዘገብነው ታላቅ ስኬት በፓርቲያችን መሪነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከመቅረጽ ባለፈ፣ አመራሩ ራሱ በግንባር ቀደምትነት በመሰማራትና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በማስተባበር ያሳየው የአመራር ጥበብ የንቅናቄው ስኬት ዋና ምስጢር ነው። ይህ ንቅናቄ የሕዝባችንን የአንድነትና የ"ይቻላል" መንፈስ በተግባር ለአለም ያሳየንበት ታላቅ አገራዊ ታሪክ ነው።

የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በፓርቲያችን ፕሬዚዳንት ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ የተበሰረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት "ተስፋን መትከል" በሚል መሪ ቃል 8 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል እስካሁን የተተከሉትን 48 ቢሊዮን ችግኞችን ወደ የ65 ቢሊዮን ችግኞች ከፍ ለማድረግ ታላቅ ሀገራዊ ግብ አንግበን በጽናት ለሌላ በስኬት ወደ ፊት እየገሰገስን እንገኛለን።

መላው የሀገራችን ዜጎች፣ ወጣቶች፣ አባቶች፣ እናቶች እንዲሁም የመንግሥትና የግል ተቋማት ይህንን ታላቅ አገራዊ ንቅናቄ በንቃት በመቀላቀል፣ ለራሳችንና ለመጭው ትውልድ የምናወርሳትን አረንጓዴ፣ የተዋበችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት አረንጓዴ ዐሻራችንን በጋራ እናኑር!

ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገው የምግብ ዋስትናችን፣ የአየር ንብረት መከላከያችን እና የብልፅግናችን ማረጋገጫ ነው!


#አረንጓዴዐሻራ

17/06/2026

በሀረሪ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ

በሀረሪ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን በአግባቡ ለመስጠት ውጤታማ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተከናውነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መካከል በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ሞዴል ፈተና መሰጠቱን እንዲሁም ፈተናው ታትሞ ዝግጁ መደረጉን ጠቅሰዋል።

የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ክልል አቀፍ ፈተና ከነገ ሰኔ 11 ጀምሮ እስከ ሰኔ 12 2018 እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

በተለይም ተማሪዎችን ካለፈው ተሞክሮ በመነሳት በስነልቦና ከማዘጋጀት ጀምሮ የሚመለከታቸው አካላትን በማሳተፍ ለፈተናው የሚረዱ ቅድመ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሚሰጠው ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተናም 4614 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡

የፈተና አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድም ቢሮው ከመምህራን ማህበር፣ ከጤና ቢሮ እና ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ከተፈቀዱ የፈተና ቁሳቁሶች ውጭ ሌላ መገልገያ ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑንም ነው ቢሮ ኃላፊው የገለጹት፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት ማንኛውም አይነት የጤና ችግር ቢያጋጥማቸው የህክምና እርዳታ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች መመደባቸውን ጠቁመው ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናውን እንዲሰሩ አሳስበዋል።

17/06/2026

Address

Jigjiga
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hoodan Cabdi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share