School life

School life Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from School life, Men's clothes shop, Addis Ababa.

25/01/2025
25/01/2025
24/01/2025

ነፃነታችን በአግባቡ በማስተዳደር ዴሞክራሲያችንን እናዳብር !

ለስጋዊ ፣ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ፍላጎቶች መሟላት አጥብቆ እንደሚሻው ሁሉ የሰው ልጅ ለነፃነቱ መስዋዕትነት ጭምር ይከፍላል።

ከጥንት እስከ ዛሬ ሰዎች ግለሰባዊ እንዲሁም ቡድናዊ ነፃነቶቻቸውን አሳልፈው ላለመስጠት የሚቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ።

በዓለም ላይ ከተከሰቱ ታላላቅ አቢዮቶች ይዘዋቸው ከተነሱ ሀሳቦች መካከልም የነፃነት ጥያቄ ይገኝበታል።

በአፍሪካ ፣ በኤሲያ እና በሌሎችም አህጉሮች የተካሄዱ የፀረ ኮሎኒያሊዝም እና የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴዎች መሰረታዊ ሀሳብ ነፃነት ነው፡፡

በዓለም ላይ አንቱታን ያተረፉ ታላላቅ ግለሰቦች የትግላቸው ማዕዘንም ነፃነት መሆኑን መረዳት አይከብድም።

በዚህ ወቅት በተለያዩ ሀገራት የሚደረጉ ትግሎችም ሁለት መልክ አላቸው። በአንድ በኩል ህዝቦች በተለያዩ ምክንያቶች የተነጠቁትን ሰላምና ነፃነት ለማስመለስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የዜጐችን ሰብአዊ እና ዴሞክራያዊ ነፃነቶች በሀይል በመንጠቅ የራስን ፍላጎት ለመጫን የሚደረግ ኋላቀር አካሄድ ነው።

በእኛ ሀገርም በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴዎች ዋና ዓላማቸው የህዝብን ነፃነት መግፈፍ ፣ ማጎሳቆል ፣ ከድህነት አረንቋ እንዳይወጣና ኢኮኖውያዊ ነፃነቱን እንዳያረጋግጥ የመፈለግ የተዛነፈ አመለካከት ውጤቶች ናቸው።

ፅንፈኝነት የራስን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት በህዝብ ኪሳራ የማረጋገጥ የውስን ግለሰቦችና ቡድኖች እኩይ አስተሳሰብና ድርጊት በመሆኑ የብዙሀኑን ህዝብ መብት እና ጥቅም ሊያስጠብቅ አይችልም ፤ አስከብሮም አያውቅም።

ፅንፈኝነት በህዝብ ስም ቢምልና ቢገዘትም የህይወት መስዋዕትነት በማስከፈል ፣ የሀገርና የህዝብ ንብረት በማውደም ፣ የህዝብን አቅም እያዳከመ ፣ የሀገረ መንግስት ግንባታን እያቀጨጨ ለጥቂት የደም ነጋዴዎችን ጊዜያዊ የኑሮ ፌሽታ ሲፈጥር ይገለጠል።

ጥቂቶች ባለማወቅ ፣ የተወሰኑትም ተታለው ፣ አንዳንዶችም ተሸውደው በፅንፈኞች የአዘቅት መንገድ ቢነጉዱም ፤ መሳሳታቸውን ቢረዱትም ፅንፈኝነት በምክንያታዊነት የመወሰንን ነፃነት ስለሚነጥቃቸው የወረዱበትን ቁልቁለት ለመውጣት ዳገት ይሆንባቸዋል።

ፅንፈኝነትን ተጋፍጦ ከማሸነፍ ውጭ ለነፃነት ፈላጊዎች ሌላ አማራጭ ግን የላቸውም።

የፅንፈኝነትን ሀገር አፍራሽ አደጋ ለመከላከል ከተናጠል ትርክት ይልቅ የወል ትርክትን ማስቀደም የግድ ይላል።

የመካከለኛው እና አካታቹ የመደመር መንገድም ፅንፍ እና ፅንፍ የመቆምን ስብራት የሚጠግን የፓርቲያችን ፍኖት ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያን በረጅም ጊዜ ታሪካቸው ነፃነታቸውን ለውጭ ሀይሎች አስደፍረው አያውቁም። በየትኛውም ውስጣዊ ሁኔታ ቢሆኑ ነፃነታቸውንና ብሄራዊ ክብራቸውን በመስዋዕነትነታቸው አስጠብቀዋል ዘልቀዋል። ለዚህም ነው ከሌሎች ሀገራት በተለየ መልኩ የድል በዓላችንን ለማክበር የታደል ነው።

ኢትዮጵያውያን በየጊዜው ያካሄዱት ዴሞክራሲን የማዋለድ እና ነፃነትን የመጎናፀፍ ትግል ፍሬ አፍርቶ ፣ መልካም ነገሮችን የሚያስቀጥለው ፣ ያለፉ ስህተቶችን ደግሞ ፈጥኖ የሚያርመው የለውጡ መንግስት ዕውን ሊሆን ችሏል።

የለውጡ መንግስት ከመጀመሪያው ጀምሮ ከወሰዳቸው አበረታች እርምጃዎች መካከል ህዝባችን ለዘመናት ሲጠማው የቆየውን ነፃነት ፣ ፍትሀዊነት እና እኩልነት ማጎናፀፍ ተጠቃሽ ናቸው።

የሀሳብ ነፃነት ፣ የሀይማኖት ነፃነት ፣ የመደራጀት ነፃነት ፣ የሚዲያ ነፃነት ወዘተ በኢትዮጵያ ታሪክ የተረጋገጡት ተጠናክሮ በቀጠለው ሀገራዊ ለውጥ መሆኑ አያሻማም።

በየጊዜው እየተጀመረ ሲጨነግፍ የቆየውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት እና ለማፅናት ቁርጠኛ አቋም የያዘው የለውጡ መንግስት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍትሀዊ ፣ ነፃ እና ቅቡልነት ያለው ሀገራዊ ምርጫ በማካሄድም ደማቅ አሻራውን ፅፏል።

የፈነጠቀው የነፃነት እና የፍትሀዊነት ጎህ ይበልጥ እንዲጠናከር ህዝባችን የለውጡ መንግስት የገጠሙትን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ተጋፍጧል ፤ እየተጋፈጠም ይገኛል።

ሲንከባለሉ ከመጡ ውስብስብ ችግሮች አኳያ የገነገኑ አሁንም የጋራ ትግል የሚያስፈልጋቸው የፅንፈኝነት አስተሳሰቦች እና ተግባራት ቢኖሩም ህዝባችን ያገኘውን ሁለንተናዊ ነፃነት አሳልፎ እንደማይሰጥ ሀገርን ለማተራመስ ፣ ህዝብን ለማባላት ለተነሱ ፅንፈኞች ሁሉ አረጋግጦላቸዋል።

ሀገራችን አሁን ላይ በምትገኝበት ሁኔታ ትልቁ ችግር ነፃነትን በአግባቡ የማስተዳደር እንጅ የነፃነት እጥረት አይደለም። ህዝባችንም በተደጋጋሚ እንደሚገልፀው መብትን እንጅ ግዴታን የማያገናዝብ ልቅ የሆነ ነፃነት ፅንፈኝነትን ቤንዚን ሆኖ እያቀጣጠለው ይገኛል።

የሚዲያ ነፃነትን ብንመለከት ዴሞክራሲ የቱንም ያህል የዳበረባቸው ሀገራት ጭምር ብሔራዊ ስጋት ከደቀነባቸው የትኛውም የሚዲያ ተቋም ላይ እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ አይሉም።

ለአብነትም "ቲክቶክ " የሚባለውን የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም አሜሪካ የደህንነት ስጋት ደቅኖብኛል በማለት በተደጋጋሚ ስትገልፅ የቆየች ሲሆን እስከ ማገድ የደረሰ እና ገና ያልተቋጨ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኗ እየታየ ነው።

በእኛም ሀገር ሁኔታ ማኅበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ዓላማ ከመጠቀም ይልቅ ፅንፈኝነትንና እና ህዝብ ከፋፋይ ሀሰተኛ መልዕክቶችን ለማሰራጨት የሚጠቀመው ቁጥሩ ቀላል አይደለም።

መንግስት በሆደ ሰፊነት እየተራመደ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት እንዲጎለብት በመትጋት የፅንፈኝነት አስተሳሰብን ተቀባይ ማሳጣት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ፤ ተጨባጭ ውጤቶችም መመዝገብ ጀምረዋል።

የፈነጠቀው የነፃነት ጎህ እንዲጎመራ ፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን እንዲያብብ ፣ ሀገረ መንግስት ግንባታችን ስር እንዲሰድ አሰባሳቢውን የብሔራዊነት ትርክት ማስረፅ ድርሻው የጎላ በመሆኑ ሁላችንም ነፃነትን በአግባቡ ማስተዳደርን ልናዳብር ይገባል።


Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when School life posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share