Habib M.d Hakena

Habib M.d Hakena ተደምረንና ተጋግዘን እዉነትን ተናግረንና በጎ በጎዉን ሰርተ?

ጦርነት ምርጫችን አይደለም። ነገር ግን ከጀመሩት ለኛ ብርቃችን አይደለም።
10/03/2022

ጦርነት ምርጫችን አይደለም። ነገር ግን ከጀመሩት ለኛ ብርቃችን አይደለም።

29/03/2019

"አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት" Prime Minister Dr Abiy Ahmed Ali ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ

ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በውጭ ለሚኖሩኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን ከዕለት ፍጆታቸው ላይበመቀነስ ቢያንስ በቀን አንድ ዶላር ድጋፍ እንዲያደርጉ ለአቀረቡት...
17/03/2019

ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በውጭ ለሚኖሩ
ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን ከዕለት ፍጆታቸው ላይ
በመቀነስ ቢያንስ በቀን አንድ ዶላር ድጋፍ እንዲያደርጉ ለአቀረቡት
ወገናዊ ጥሪ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት
ፈንድ Ethiopian Diaspora Trust fund (EDTF) በሚል ስያሜ
ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መመስረቱ ይታወቃል። ይህንን
ወገናዊ ጥሪ ለማገዝ የኢትዮጵያ ማህበር በሆላንድ ከበጎ አድራጎት
ድርጅቱ ተወካዮች ጋር በመመካከር እና ጊዚያዊ አስተባባሪ አካል
በመሰየም በኔዘርላንድ የትረስት ፈንዱን ቻርተር ለማቋቋም የሚያስችሉ
ቅድመ ዝግጅቶችን ሲያመቻች ቆይቷል።
በዚህም መሰረት የዲያስፖራውን የበጎ አድራጎት ድርጅት የኔዘርላንድ
ቅርንጫፍ (EDTF- Chapter in NL) ለማቋቋም እ.ኤ.አ ማርች 16
ቀን 2019 ከ14፡00 እስከ 19፡00 ሰዓት በደንሀግ ከተማ ለማድረግ
መዘጋጀቱን የገለጸ ሲሆን፣ ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን
በምስረታው ስነ-ስርዓት ላይ እንድትገኙ በታላቅ ትህትና ጥሪያችንን
እናስተላልፋለን።
አድራሻ፡ Trompstraat 342, 2518 BT Den Haag
(Zeeheldentheater)
የሆላንድ EDTF-Chapter ምስረታ ጊዚያዊ አስተባባሪ አካል
በሔግ፡ ኔዘርላንድ የኢ.ፌዲ.ሪ ኤምባሲ

07/11/2018

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ
መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።
በዛሬው መደበኛ ስብሰባውም የቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀትን ለመወሰን
የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ አፀድቋል።
ለምክር ቤቱ ቀርቦ በፀደቀው በውሳኔ ሃሳቡ መሰረት 20 የነበሩት
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ወደ 10 ዝቅ የተደረጉ መሆኑም
ተገልጿል።
እንደ አዲስ በተደራጁት በእያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ በስራቸው ከ2 እስከ 4
ንዑስ ኮሚቴዎች እንደሚደራጁ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ተገልጿል።
የቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት ማሻሻያ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት
መንግስት ለሚሰራው ስራ የላቀ ውጤታማነት ለመረጋገጥ መሆኑ
ተገልጿል።
እንዲሁም የምክር ቤቱ ሕገ መንግስታዊ ተልዕኮ በተሟላ እዲወጣ
ለማስቻል ወሳኝ በመሆኑ እና የመንግስትን አደረጃጀት ክለሳ ተከትሎ
የሚደራጅ ማሻሻያ መሆኑም መክንያትነት ተጠቅሷል።
ምክር ቤቱ አደረጃጀት ማሻሻያን መሰረት በማድረግ የቋሚ ኮሚቴ
አመራርና አባላት ምደባን በተመለከተ ሰፊ ውይይት በማድረግ የቀረበ
የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በ2 ተቃውሞ በ6 ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ
ድምፅ ማጽደቁን ፋና ዘግቧል።
በዛሬው እለት በፀደቀው የውሳኔ ሀሳብ መሰረትም 10ሩ ቋሚ
ኮሚቴዎች፦
1. የህግ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
2. የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
3. የሰው ሃብት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
4. የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራ ዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
5. የተፈጥሮ ሃብት፣መስኖ እና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
6. የከተማ ልማት፣ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
7. የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
8. የገቢዎች፣በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
9. የግብርና፣ አርብቶ አደር እና አከባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
10. የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
እያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሚኖሩት ሲሆን አጠቃላይ የአባላት
ብዛትም ከ20 እስከ 45 የሚደረስ ነው።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአለም አቀፍ
የልማት ማህበር መካከል ለተወዳዳሪነት እና ስራ ፈጠራ ፕሮጀክት
ማስፈፀሚያ የተደረገውን ተጨማሪ የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ
ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ
አዋጁን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

07/11/2018

ለቸኮለ! የዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 27/2011 አበይት ዜናዎች
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ከብዙ ክርክር
በኋላ ቋሚ ኮሚቴዎቹን ከ20 ወደ 10 ዝቅ በማድረግ እንደገና
አደራጅቷል፡፡ ከመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል አደረጃጀት ለውጥ ጋር
ለማጣጣም ሲባል እንደገና ከተደራጁት 10 ቋሚ ኮሚቴዎች መካከል
የሕግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ እንዲሁም የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ቋሚ
ኮሚቴዎች ይገኙበታል፡፡ ሪፖርተር በበኩሉ በቅደም ተከትል ሁለቱን ቋሚ
ኮሚቴዎች እንዲመሩ በዕጩነት የቀረቡትን አቶ አማኑዔል አብርሃምን
እና ሞቱማ መቃሳን ግን ምክር ቤቱ ውድቅ በማድረግ ያለ ውሳኔ
እንደተበተነ ዘግቧል፡፡
2. አቃቢ ሕግ ዛሬ በዋለ ችሎት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ
ቤት ባልደረባ በነበሩት የወንጀል ተጠርጣሪ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ
የጀመርኩትን ምርመራ በሥራ መደራረብ ሳቢያ ማጠናቀቅ አልቻልኩም
ብሏል፡፡ በባለፈው ችሎት አቃቢ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የፌደራሉ
መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አሳስቦ የነበረ ቢሆንም ዛሬም እንደገና
አቤቱታውን እንደገና ተቀብሎ የመጨረሻውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ
ፈቅዷል፡፡
3. አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል
ሆነው ተሹመዋል፡፡ እስከ ሹመታቸው ድረስ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
ሃላፊ የነበሩ ሲሆን በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አስተዳደር ለፌደራል
ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራልነት በመሾም ሦስተኛው ሰው ሆነዋል፡፡
የቀድሞው ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል በቅርቡ የሰላም ሚንስቴር
ሚንስትር ደዔታ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡
4. የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በአዲስ መልክ
እንዲዋቀርና በድርጅቱ ውስጥ የተፈፀመው ምዝበራ ተጣርቶ ተጠያቂ
ግለሰቦች ህግ ፊት እንዲቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ ምርመራ
ከተጀመረ ስንብቷል። በከፍተኛ ምስጢር ተይዞ እየተካሄደ ያለው
ምርመራ እጅግ ግር የሚያሰኙና አዳዲስ መረጃዎችን አግኝቷል።
ምርመራው እንደቀጠለ ሲሆን በእስካሁኑ ምርመራ ሜቴክ የንግድ
አውሮፕላን ይፋዊ ባልሆነ መንገድ መግዛቱን የሚያሳይ መረጃ
ተገኝቷል። ሁለት መቶ መኖሪያ ቤቶችን በድርጅቱ ገንዘብ ገዝቶ
ለግለሰቦች ሰጥቷል።
5. የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት እንግሊዝ ያቀረበችውን መነሻ ሃሳብ
መርምሮ በኤርትራ ላይ ጥሎት የኖረውን ማዕቀብ በቀጣዩ ሳምንት
ለማንሳት ዝግጅት ላይ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ኤርትራ ማዕቀቡ
የሚነሳላት ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ስምምነት በመድረሷ እና አሜሪካ
በማዕቀቡ መቀጠል ላይ ይዛው የኖረችውን አቋሟን በማላላቷ ነው፡፡
ፈረንሳይ ግን ኤርትራ ከጅቡቲ ጋር ድንበር ውዝግቧን ስላልፈታች
የተወሰነ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲደረግባት በመወትወት ላይ ናት፡፡
ኤርትራ ለአልሸባብ ድጋፍ ታደርጋለች ተብለ ዐለም ዐቀፍ የጦር መሳሪያ፣
የጉዞ እና ገንዘብ ዝውውር ማዕቀብ የተጣለባት እኤአ በ2009 ነበር፡፡
6. ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እየተገበረው ባለው አዲስ አወቃቀር መሠረት
አምስት ቋሚ ተጠሪዎችን ሹሟል፡፡ አምባሳደር ወይንሸት ታደሠ፣
አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ፣ አምባሳደር ቦጋለ ቶሎሳ፣ አምባሳደር ደዋኖ
ከድር እና አምባሳደር ነጋ ጸጋየ ናቸው፡፡ ቋሚ ተጠሪዎቹ የመስሪያ ቤቱን
የተለያዩ ክፍሎች በበላይነት ይመራሉ፤ በመስሪያ ቤቱን የዕለት ተለት
ሥራዎችም ላይ ውሳኔ የማሳለፍ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡
7. በወላይታ ዞን 10 ሰዎች በቢጫ ወባ በሽታ መሞታቸውን ተከትሎ
የዐለም ጤና ድርጅት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የክትባት መድሃኒቶችን ወደ
ኢትዮጵያ ማስገባቱን ገልጧል፡፡ በአካባቢው በቅርብ ጊዜ ክትባት በስፋት
ስላልተሰጠ እና ከነሐሴ ወዲህም በ35 ሰዎች ላይ በሽታው በመታየቱ
ባጭር ጊዜ በስፋት ሊሰራጭ ይችላል የሚል ስጋት ስላለ ነው ድርጅቱ
የክትባት መድሃኒቶቹን የላከው፡፡ እኤአ በ2020 የቢጫ ወባ ክትባትን
በመደበኛው የክትባት መርሃ ግብር ለማካተት ዕቅድ ተይዟል፡፡
8. የሕዝብን ሰላም በማደፍረስ የተከሰሱ ቤተ እስራዔላዊያን በሙሉ
ወንጀላቸው እንዲሰረዝላቸው ለመንግሥት አቤቱታ እንዲያቀርቡ
የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሪቨን ሪቭሊን እና ፍትህ ሚንስትሩ አይሌት ሻኪድ
መጠየቃቸውን ሐሬዝ የተባለው የእስራዔል ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ለቤተ
እስራዔላዊያኑ ምህረቱ የሚደረገው ከነባር አይሁድ ማህበረሰቦች ጋር
ያላቸውን ክፍተት ለማጥበብ እና በሕግ አስፈጻሚ አካላት ያላቸውን
ጥርጣሬ ለመቅረፍ እና ለማኅበረሰቡ “ስግድ” በዓል ክብር ሲባል ነው፡፡
የአዲሱ ሕግ ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም በፈጸሙት ወንጀል ተፈርዶባቸው
ነገር ግን ገና ያልተሳሩ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ግለሰቦችን እና
ወጣቶችን ያካትታል፡፡ ሚንስትር ሻኪድ “መንግሥት ወደዚህ ካመጣቸው
በኋላ ማግለሉ ፈጽሞ ለማመን የሚከብድ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያዊያን ፈላሾች ላይ ዘረኝነት እና መድልዖ እንደሚደርስባቸው
ተደጋግሞ ይነገራል፡፡
9. ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን
ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃማት ጋር ኅብረቱ እየወሰዳቸው ስላሉት
መዋቅራዊ ማሻሻያዎች መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ
ሴክሬታሪያት ገልጧል፡፡ ከኅዳር 17-18 ስለሚካሄደው 11ኛው የኅብረቱ
ልዩ የመሪዎች ጉባዔም የመከሩ ሲሆን ኮሚሽነር ሙሳም በትዊተር
ገጻቸው ስለ ኅብረቱ ማሻሻያ ለጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳብራሩላቸው
ገልጸዋል፡፡ መጭው የመሪዎች ጉባዔ በዋናነት የሚወያየው በኅብረቱ
ተቋማዊ ማሻሻያ ላይ ነው፡፡
10. በሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም)
የሱማሊያ ጸጥታ ጥበቃውን ለመደበኛው የሀገሪቱ ሠራዊት ለማስረከብ
የሚያስችለውን መርሃ ግብር የያዘ ሰነድ ሰሞኑን ማጽደቁን አስታውቋል፡፡
አሚሶም Concept of Operations የተሰኘውን ሰነድ ያጸደቀው
በኬንያ ናይሮቢ ለአምስት ቀናት በመከረበት ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ
ነው፡፡ አፍሪካ ኅብረት እና ወታደር ያዋጡ ሀገሮች ካጸደቁት ከእኤአ
2018-2021 ያለው የመጨረሻ ምዕራፍ አሚሶም ጦሩን ከሱማሊያ
ሙሉ በሙሉ የሚያስወጣበት ምዕራፍ ይሆናል፡፡

07/11/2018

በፍራንክፈር ከተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን
በተነሱ ጥያቄዎች ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ የሰጡት ምላሽ:-
* የህግ ማስከበር ጉዳይ በቅርቡ በተግባር ይሰራበታል
* ስለ"መደመር" ፍልስፍና በቅርቡ ታትሞ በሚወጣው መጽሐፌ ላይ
በዝርዝር ለህዝብ ይቀርባል
* ቢሄራዊ እርቅ በተመለከተ በቅርቡ ዝግጅታችን በማጠናቀቅ በመላ
ሀገሪቱ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በሚዘጋጅ ኮሚቴ አማካኝነት ብሄራዊ
ውይይት ይደረጋል
* መፈናቀል ሊቆም የሚችል አፈናቃዮቹ ከመፈንገል ይልቅ ማቀፍን
ሲጀምሩ ነው
* ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ሀገር ስለሆነች ኢትዮጵያን ማንኳሰስ
አይቻልም
* ህገመንግስትን የማሻሻል ጉዳይ በተመለከተ ህዝቡ ተወያይቶ
የሚያደርገው ጉዳይ ነው
* በኢትዮጵያ ጠንካራ የሚባል መንግስት ሳይሆን ጠንካራ ህዝብ ነው
ያለው
* በክልሎች መስተዳድሮች ያሉ ሁኔታዎች በተለይ በሶማሌና ጋምቤላ
የተጀመረ ህግ የማስያዝ አካሄድ በሁሉም ይሰራበታል
* አምባገነንነት ለህዝብም ለመንግስት የማይበጅ በመሆኑ በህግ
አስተማሪ እርምጃ በመውሰድ ዜጎች ጥረው ግረው የሚኖርባት ሀገር
መፍጠር ነው
* አንቀፅ 39ና ባንዴራን በተመለከተ ቀስበቀስ በሂደት የሚታይ ጉዳይ
ይሆናል
* ክልል በማስወገድን በተመለከተና ክፍለሀገርን ስለመባል ጉዳይ አሁን
ያለው የፌደራል ስርዓት ያስገኘው ፋይዳና ክፍተት መታየት ይኖርበታል
ይህም የናንተ የሙሁራን ድጋፍ ያስፈልጋል
* ኢትዮጵያውያን ለጉብኝት ካልሆነ ለስደት ከሀገር የምንወጣበት ጊዜ
ያበቃል
* አፍሪካ በቅርቡ በርካታ ዜጎች የሚሰደዱባትና የበለፀገች ትሆናለች
* ትጥቅ ስለማስፈታት በተመለከተ ሁሉም የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች
መሳሪያ ይዞ የገባ የለም
* በሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ በርካታ የትጥቅ መሳሪያ እየገባ ይገኛል
ነገር ግን ብዙ ገንዘብ አውጥቶ ከመግዛት ይልቅ ተደራጅቶ ትራክተር
ቢገዙበት
* ከኦነግ ጋር በተያያዘ የኦነግ ወታደሮች ትጥቃቸው ፈተው የገቡ ናቸው።
በሀገር ውስጥም ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ
* ከአረብ ሀገራትና ከኤርትራ ጋር ያለው ስምምነት ከኢትዮጵያ ህዝብ
የሚደበቅ አንዳች ነገር የለውም
* የአባይን ግድብ በተመለከተ እኛን የሚጠቅም ግብፅን የማይጎዳ ነው።
በዚህ ጉዳይም ደጋግመን ስንገልፀው የቆየ ነው። አዲስ የተደረገ ምንም
የተለየ ስምምነት የለም።
* የአማራና ትግራይ ይሁን አማራና ኦሮሞ በተመለከተ እንደህዝብ ሲታይ
ምንም የሚያሰጋ የለውም። ነገር ግን ምስኪኑ ህዝብ በማባላት ስልጣን
መያዝ የሚፈልጉ አሉ እነዚህም እንደተለመደው የሚሸነፉ ናቸው
* ፍትህን በተመለከተ ከነገ ጀምሮ የሚሰራ አለ
* የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዳግም እየታየ ነው
ኢ.ፕ.ድ

Address

Hadale'ela Afar
Afar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habib M.d Hakena posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Habib M.d Hakena:

Share