Nave advertising

Nave advertising Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nave advertising, Durame.

ከምባታ
23/02/2025

ከምባታ

23/02/2025
please follow meሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን 2ለ0 አሸነፈ   | የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ዛሬ ከሜዳው ውጪ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 አሸንፏል ።መሐመድ ሳላህ...
23/02/2025

please follow me
ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን 2ለ0 አሸነፈ

| የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ዛሬ ከሜዳው ውጪ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 አሸንፏል ።

መሐመድ ሳላህ በ14ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ግብ ሲያስቆጥር፤ ስቦዝላይ በ37ኛው ደቂቃ 2ኛውን ግብ አስቆጥሯል።

ሲቲዎች በተደጋጋሚ የሊቨርፑል የግብ ክልል መድረስ ቢችሉም ፤ ግብ ማስቆጠር አልቻሉም።

መሐመድ ሳላህ በ25 ግቦች የፕሪሚየር ሊጉን የኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ ይገኛል።

ተጫዋቹ በውድድር ዓመቱ 16 ግብ የሆኑ ኳሷችን በማቀበልም ቀዳሚ ነው።

ፕሪሚየር ሊጉን ሊቨርፑል 64 ነጥብ በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ 1ኛ ደረጃ ላይ ነው።

አርሰናል በ26 ጨዋታዎች ከመሪው በ11 ነጥብ ዝቅ ብሎ በ53 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ በ2ኛነት ተቀምጧል።

አንድ ጨዋታ እየቀረው ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል በ20 ነጥብ ዝቅ ብሎ 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሲቲ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ በሚቀጥሉት ጨዋታዎች ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል።

በላሉ ኢታላ

የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ባለቤታቸው አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ አንድ ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለመቄዶንያ  ድጋፍ አድርገዋል፡፡ያስጀመረን ያስፈፅመናል!!!
23/02/2025

የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ባለቤታቸው አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ አንድ ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለመቄዶንያ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ያስጀመረን ያስፈፅመናል!!!

ባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ ነኝ ፀሎት አደርግልሻለው ብርሽንም አበዛልሻለው በማለት ከአንዲት ግለሰብ  #ከ736ሺ ብር በላይ ያታለለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ  | ግለሰቡ በተላከለት ገንዘብ ባ...
23/02/2025

ባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ ነኝ ፀሎት አደርግልሻለው ብርሽንም አበዛልሻለው በማለት ከአንዲት ግለሰብ #ከ736ሺ ብር በላይ ያታለለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

| ግለሰቡ በተላከለት ገንዘብ ባጃጅ መግዛቱንም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማረጋገጡን አስታውቋል

የካቲት 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል አደባባይ አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪው የባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ እና ፈዋሽ ነኝ በሚል "አባ መንግስቱ" የሚል ማህበራዊ ሚዲያ በመክፈት አንዲት ታዋቂ የኢትዮጵያ አርቲስት የሰጠችውን ኃይማኖታዊ የፈውስ ምስክርነት ከሌላ ሰው ላይ አውርዶ በራሱ አካውንት የፈወስኳት እኔ ነኝ በማለት ይለቃል። ይህን ቪዲዮ የተመለከተች የግል ተበዳይ ባህላዊ መድኃኒት እፈልጋለሁ በማለት ወደ ግለሰቡ በመደወል ስትጠይቅ እንደሚሰራላት ይነገራታል።

ከጊዜ በኋላ ግለሰቡ አካውንትሽ ላይ ስንት ብር አለ ብሎ ግለሰቧን በመጠየቅ ብርሽን አበዛልሻለው ብሎ በማሳመን በተለያ ስም በከፈተው የባንክ አካውንት በተለያዩ ጊዜያት እና ቀናት በድምሩ 652ሺ ብር ወደ ራሱ አካውንት እንድታስገባለት ያደርጋል። ይህም አልበቃው ብሎ ከሌሎች ተበድራ 84ሺህ 800 ብር ተጨማሪ እንድታስገባለት ማድረጉን በጎፋ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተጣራው የወንጀል ምርመራ መዝገብ ያስረዳል።

ተከሳሽ በአጠቃላይ 736,800ብር እንዲላክለት ያደረገ ሲሆን ብርሽ በዝቶልሽ ይመለስልሻል እያለ ቀጠሮ እየሰጠ ሲጠፋ እና መታለሏ የገባት የግል ተበዳይ ወደ ፖሊስ በመምጣት የተፈፀመባትን ወንጀል ትናገራለች።

ፖሊስም የግለሰቧን አቤቱታ መነሻ በማድረግ እና የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለግለሰቡ የተላከበትን አካውንት ሲያጣራ ግለሰቧ በተለያዩ ቀናት በተለያየ አካውንት ገንዘቡን መላኳን አረጋግጧል።

ግለሰቡ በተለያዩ ስሞችና በተለያዩ ባንኮች አካውንት መኖሩን ያጣራው ፖሊስ ግለሰቡን የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ደቡብ ምዕራብ ክልል በምትገኘው ቴፒ ከተማ ድረስ በመሄድ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል ያለው ፖሊስ ግለሰቡ በቁጥጥር ከዋለ በኋላ በተላከለት ገንዘብ ኮድ (1) 05224 ደቡብ ምዕራብ ጊዜያዊ ሠሌዳ ያለው አንድ ባጃጅም የገዛ ሲሆን ተጠርጣሪው ከነ ኤግዚቢቱም በቁጥጥር ስር ውሏል።

አሁን አሁን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እፈውሳለሁ ባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ ነኝ የሚሉ ምንም አይነት እውቅናና ፍቃድ የሌላቸው ግለሰቦችን እያስተዋልን እንገኛለን ያለው ፖሊስ፤ ስለዚህም ህብረተሰቡ ውሳኔዎችን ከመወሰኑ በፊት ማንነታቸውን እና ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥ ለመሰል የወንጀል ድርጊቶች እንዳይጋለጥ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።


ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

"""""""""""***""""""""""
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.

23/02/2025
ባለቤቱን 3 ሺ ፓውንድ ያስቀጣው ዶሮበእንግሊዟ ደርቢ ከተማ በአውራ ዶሮው የማያቋርጥ ጩኸት የተሰላቹ ጎረቤቶች  ቅሬታ ካሰሙ በኋላ የአውራ ዶሮው ባለቤት ከ3,000 ፓውንድ በላይ እንዲከፍል ...
23/02/2025

ባለቤቱን 3 ሺ ፓውንድ ያስቀጣው ዶሮ

በእንግሊዟ ደርቢ ከተማ በአውራ ዶሮው የማያቋርጥ ጩኸት የተሰላቹ ጎረቤቶች ቅሬታ ካሰሙ በኋላ የአውራ ዶሮው ባለቤት ከ3,000 ፓውንድ በላይ እንዲከፍል ተወስኗል።

የሰሜን ምስራቅ ደርቢሻየር ካውንስል ኃላፊዎች ልዩ የክትትል ባለሙያዎችን አስማርተው በጥባጩ አውራ ዶሮ ከአንድ ሰአት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 80 ጊዜ ያህል ሲጮህ እንዳገኙት ተገልጿል።

ዴሪክ ቦወር የተሰኘው የአውራ ዶሮው ባለቤት ችሎት ፊት እንዲቆም ጥሪ ቢደርሰውም ሳይገኝ መቅረቱ የተገለፀ ሲሆን ቅጣቱም እስካሁን ሳይከፈል መቅረቱን የሰሜን ምስራቅ ደርቢሻየር ካውንስል አስታውቋል።

ቃልኪዳን ይጥና

via Artstvworld

ተዘርፌያለሁ!   | በትላንትናው ዕለት መገናኛ አከባቢ 24 - 40/60 ከቀኑ 6:30 እስከ 11:00 ባለው ሰዓት ኮንዶሚኒየም ላይ ሌቦች በሬን ሰብረው 1. ሁለት HP ላፕቶፕ እና 2. ሀር...
23/02/2025

ተዘርፌያለሁ!

| በትላንትናው ዕለት መገናኛ አከባቢ 24 - 40/60 ከቀኑ 6:30 እስከ 11:00 ባለው ሰዓት ኮንዶሚኒየም ላይ ሌቦች በሬን ሰብረው

1. ሁለት HP ላፕቶፕ እና
2. ሀርድ ዲስክ(ባለቤቴ ለ 4 ዓመታት የለፋችበትን ፒ.ኤች.ዲ ሪሰርችዋን እና ብዙ ፕሮፖዛሎችን የያዘ )፤
3. አንድ IPad
4. 12 ግራም የአንገት ወርቅ
5. የጆሮ ጌጥ እና የጣት ቀለበት
6. ተንቀሳቃሽ ዋይፋይ
7. ሁለት ብራንድ የእጅ ሰዓቶች አልባሳት
8. ፓውር ባንክ እና ሀርድ ዲስክ

ለአካል ጉዳተኛ ሕፃናት ጠቃሚ የተባለ እና ከውጪ የመጣ መታሻ፤ የሕፃናት ማዘያዎች እና ሌሎችም እቃዎች ተዘርፌያለሁ።

ፖሊስም ጉዳዩን የያዘው ሲሆን ፤ ከሕዝብ የሚደበቅ ነገር የለምና የትኛውም አይነት ፍንጭ ካላችሁ እንድትጠቁሙን በአክብሮት እጠይቃለሁ።

እግዚአብሔር ሆይ በሁሉ ስለ ሁሉ ተመስገን።

(ሼር በማድረግ ለብዙዎች አድርሱልኝ!)
Aklilu Tesfaye

ባል እና ሚስት ናቸዉ።በጣም ነዉ የሚዋደዱት ።ብዙ ጊዜ ባልን እንዴት ታገባታለሕ በሚል ብዙዎች ትችት ያደርሱበታል።ባል ግን ከባለቤቴ የምለየዉ ስሞት ብቻ ነዉ በማለት ይመልስላቸዋል።በማንኛዉም...
23/02/2025

ባል እና ሚስት ናቸዉ።በጣም ነዉ የሚዋደዱት ።ብዙ ጊዜ ባልን እንዴት ታገባታለሕ በሚል ብዙዎች ትችት ያደርሱበታል።
ባል ግን ከባለቤቴ የምለየዉ ስሞት ብቻ ነዉ በማለት ይመልስላቸዋል።
በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ብትሆንም የአንተ የሆነዉን አታጣም።

23/02/2025

መልካም ሰንበት

ዶ/ር ዛኪራ ተባረክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።  ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በሜዲስን 3.87 አምጥታ በዛሬው እለት የተመረቀችው እህታችን በሶስት ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች።* ከሁ...
23/02/2025

ዶ/ር ዛኪራ ተባረክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።

ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በሜዲስን 3.87 አምጥታ በዛሬው እለት የተመረቀችው እህታችን በሶስት ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች።
* ከሁሉም የህክምና ተማሪዎች አንደኛ ወጥታ ተሸልማለች።
* ከሁሉም ሴቶች አንደኛ ወጥታ ተሸልማለች።
* ከሁሉም ተማሪዎች አንደኛ ወጥታ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልማለች።

«ከጠንካራ ሴት ጎን ጥሩ ባል አለ።» ይኸው ከጎኗ

Address

Durame

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nave advertising posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share