Faris kadir

Faris kadir Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Faris kadir, Men's clothes shop, Haraar, Harar.

02/04/2026
02/04/2026

የመጋቢት 24 አንፀባራቂ ድል ለኢትዮጵያ ብልፅግና መሰረት ነው!!

#መጋቢት24

02/04/2026

ኢትዮጵያ ዐዲሲቷ የተስፋ ዓድማስ ናት!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የታሪክ አውድ ውስጥ አዲስ ትርጉምና ጽኑ ቃል-ኪዳን ተላብሶ ብቅ ያለ፣ ለሀገራችንና ለሕዝቦቿም አዲስ የተስፋ አድማስን የፈነጠቀ ክስተት ነበር።

ይህ ዕለት ኢትዮጵያን ተብትቦ ይዞ ከነበረው ውስብስብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቅርቃር አውጥቶ ወደ ብሩህ መጻኢ ዕድል ለማሸጋገር የተገባ ታላቅ የትውልድ ውል ሆኖ ተመዝግቧል።

ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2018 ዓ.ም. ባሉት ስምንት የለውጥ ዓመታት የጊዜ ጉዞ ውስጥ፣ ሀገራችን ያስመዘገበቻቸው ድሎች፣ የተሻገረቻቸው ክፉ ፈተናዎችና የገነባቻቸው ተጨባጭ እውነታዎች ኢትዮጵያን ከነበረችበት የውድቀት ስጋት ታድገው ወደ ላቀ የልዕልና ምዕራፍ ያሸጋገሩ ናቸው። ይህ የትንሣኤ ጉዞ በፈተና እቶን ውስጥ አልፎ የነጠረ፣ በጽናት የታነጸና የኢትዮጵያን የማይበገር ማንነት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዳግም ያስመሰከረ የታሪክ አሻራ ነው።

የዛሬው የፖለቲካ ምኅዳራችን አስኳል የተቀዳው ከዚሁ ከመጋቢት 24ቱ የታሪክ ብርሃን ነው። የሐሳብ ልዩነትን በጸጋ የሚቀበል፣ የመሐልና የዳር ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን በማክሰም ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ያጸና፣ እንዲሁም ከፋፋይና ነጠላ ትርክቶችን በማርገብ የወል ሀገራዊ እሴቶችን የሚያሰርጽ ሥርዓት ዕውን ሆኗል።

ብሔራዊ ጥቅምንና ደኅንነትን የሚያስቀድም፣ ዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲን የሚከተልና ለጎረቤት ሀገራት ቀዳሚ ትኩረት የሚሰጥ የፖለቲካ ሥነ-ምኅዳር መሠረቱ የተጣለውም በዚህ ወቅት ነበር። ከለውጡ ማግሥት ጀምሮ የፖለቲካ ዓውዱ በዘላቂነት እንዲጸና አካታች ሀገራዊ ምክክር በስፋት እየተካሄደ ከመሆኑም በላይ፣ የሽግግር ፍትሕ ለማስፈንም እየተሰራ ይገኛል፡፡

የፌዴሬሽኑ አባል ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸውን በተግባር እየተለማመዱ ሲሆን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በነፃነትና በሕግ አግባብ ራሳቸውን ለውድድር እያቀረቡ ይገኛሉ።

መንግስት አካታች የፖለቲካ ስርዓት እንዲሰፍንበወሰደው ብስለት የተሞላበት እርምጃ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ከካቢኔ ጀምሮ በየደረጃው ሥልጣን እያጋራና ሀገር በጋራ የመምራት ዕድል እየሰጠ ይገኛል። ይህም ኢትዮጵያውያን በለውጡ ብሥራት አማካኝነት ከመጠፋፋት ፖለቲካ ወደ መተባበር የዲሞክራሲ ልምምድ መሸጋገራቸውን በግልጽ ያሳያል።

መጋቢት 24 የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ስብራት የታከመበትና አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የተጀመረበትም ጭምር ነው። ሀገራችን በተለያዩ የንግድ ብድሮች ጀርባዋ ጎብጦ፣ በነጠላ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክንያት የመልማት ጸጋዎቿ ተዳፍነው፣ በመንግሥት የአፈጻጸም ዐቅም ውስንነትም በብሔራዊ ውርደት ዋዜማ ላይ ቆማ ነበረ።

የለውጡ መንግሥት እነዚህን አደገኛ ቅርቃሮች በመበጣጠስ ኢትዮጵያን አዲሲቷ የተስፋ አድማስ ማድረግ ችሏል። አዳዲስ የንግድ ብድሮችን ከመውሰድ በመቆጠብና የነበሩትንም በእልህ አስጨራሽ ድርድሮች ወደ ተራዘመ የክፍያ ጊዜ በመቀየር ኢኮኖሚውን ከውድቀት ታድጓል።

በየደረጃው በተተገበሩ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሞች ከግብርና-መር ወደ ብዝኃ-ዘርፍ ኢኮኖሚ ትኩረት በመዞሩ የሀገሪቱን ጸጋዎች በላቀ ደረጃ መጠቀም ተጀምሯል። እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ካጋጠሟቸው መዋቅራዊና የአፈጻጸም ችግሮች ወጥተው ዓለምን ባስደመመ ተአምር ለምርቃት በቅተዋል።

ከሕዳሴው ግድብ ጎን ለጎን በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅም ኢትዮጵያ በአዲስ የኢኮኖሚ ምሕዋር ውስጥ መግባቷን ለዓለም አሳይታለች። ይህም ሀገሪቱ ያላትን ታሪካዊ የነፃነት ቀንዲልነት ከኢኮኖሚ ልዕልና ጋር አጣምሮ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ተሰሚነቷ እንዲጎላ አድርጎታል። ዛሬ ኢትዮጵያ በጥቂት መሪዎች የምትጎበኝ ሀገር ሳትሆን፣ በየሳምንቱ የታላላቅ ሀገራት መሪዎችን የምታስተናግድና ዲፕሎማሲዋ ከተከላካይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት ያደገባት ኃያል ሀገር ሆናለች።

በተመሳሳይ መልኩ መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ከተሞች ዳግም የተወለዱበት መነሻ ሆኖ ያገለግላል። የለውጡ መንግሥት ከተሞችን ወደ ዘመናዊነት በማሸጋገር ንጹሕ፣ ስሉጥ አገልግሎት ሰጪና የተቀናጀ መሠረተ-ልማት መገኛ እንዲሆኑ በትጋት ሠርቷል።

በኮሪደር ልማት አማካኝነት ከተሞች አዲስ ገጽታን የተላበሱ ሲሆን፣ ዘመናዊነትን የሚኖርና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታነጸ ትውልድ የመቅረጽ ሥራ ጥልቅ መሠረት ይዟል። ከዚህም ባለፈ ማኅበራዊ መስተጋብር ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲጠናከር፣ ብዝኃነት የሀገር ጌጥና አንድነት ደግሞ የሀገር ዐቅም እንዲሆን ተደርጓል።

ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን በጋራ የመጋፈጥ ባህል ጎልቶ የታየ ሲሆን፣ በድርቅና በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የተደረገው ሀገራዊ ድጋፍ የዚሁ ጽኑ አንድነት ማሳያ ነው።

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ ከባዕዳን ጋር አብረው ግጭት ለሚፈጥሩ ባንዳዎች፣ መላው ሕዝብ በአንድነት ቆሞ ምላሽ የሰጠበትና ጀግናው መሪም እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ለሀገር ክብር ወደ ጦር ሜዳ የዘመተበት የታሪክ ምዕራፍ ተመዝግቧል።

ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኃይልና በምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አስደማሚ ስኬቶችን አስመዝግባለች። በታዳሽ ኃይል ልማት ለዓለም አብነት መሆን የቻለች ሲሆን፣ ቀድማ ወደ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች መሸጋገሯ አሁን ያለውን የነዳጅ ቀውስ በተወሰነ ደረጃ እንድትቋቋም ረድቷታል።

ምንም እንኳን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች ጉዞዋን ለማዘግየት ቢሞክሩም፣ ኢትዮጵያ ግን አሁንም በአስተማማኝ የፖሊሲ አቅጣጫ ላይ ትገኛለች። እያደገ በመጣው ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖዋ፣ እየፈረጠመ ባለው ኢኮኖሚዋና በጀግኖች ልጆቿ ጽናት፣ ሀገራችን አዲሲቷ የተስፋ አድማስ ሆና ትቀጥላለች።

ዛሬ ላይ የለውጡን መሠረት ከማስፋትና ከማጽናት ወደ ማላቅ የተሸጋገረችው ኢትዮጵያ፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌትነቷን በተግባር ታውጃለች። ይህን ለውጥ እውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በድል እንደሚያሳርጉት ጥርጥር የለውም።

02/04/2026

የጠራ ሰማይ በሚታይበት፤ የድካም አዝመራ በሚሰበሰብበት የመጋቢት ወር፣ አሻጋሪ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ከፍታዎቻችን አስምረናል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

መጋቢት ለፖለቲካችን የልዩ ታሪክ ወር ነው፡፡ ሕዝብ ከጨለማ ወደ አሻጋሪ ብርሀን የወጣበት የአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ ወርም ነው። በመጋቢት አያሌ የለውጥ ነጋሪቶች ተጎስመው አዲስ የፓለቲካ-ኢኮኖሚ ለውጥ ታውጇል።

ሕዝባዊ ግፊት እና ትግል ያመጣው የመጋቢት ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶችን መጠገን ያስቻሉ ሪፎርሞች የተተገበሩበት ነው፤ የሕዝባችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት የጀመሩበት አዲስ የኢትዮጵያ ንጋትም ሆኗል።

የምርትና ምርታማነት ዕድገት፣ የቱሪዝም መነቃቃት፣ የማዕድን ሐብት ተጠቃሚነት፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ፣ የከተማ ልማት እና የዲፕሎማሲ ስኬት ሁሉ ጅማሯቸው መጋቢት ነው፡፡

በተቋም ግንባታም ባለፉት ስምንት ዓመታት አስደናቂ ለውጦች ተመዝግበዋል። የጸጥታና የደኅንነት ተቋማት ታላቋን ኢትዮጵያ የሚመጥኑ እንዲሆኑ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ፣ በአደረጃጀትና በሥራ ከባቢ የማዘመን ሥራዎች በስኬት ተከናውነዋል።

መጋቢት የሀገራችንን ከተሞች የማዘመን ትልም ዕውን የሆነበት፣ የኮሪደር ልማት ስኬቶችን መጎናፀፍ የቻልንበት፣ የዓየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ያለመ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻን በቢሊየን የሚቆጠሩ ዛፎችን በመትከል አረንጓዴ ምድር የፈጠርንበት፣ እንዲሁም በሀገራችን አዲስ የፖለቲካ፣ የዴሞክራሲ እና የትርክት ዕይታ የተበሰረበት ወር ነዉ፡፡

ለሺህ ዓመታት በዝናብ ጥገኝነት ላይ ተመስርቶ የነበረውን ግብርናችንን በማዘመን በበጋ መስኖ ዓመቱን ሙሉ ማምረት የጀመርነው በዚሁ ወርሃ መጋቢት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ ስንዴ ኢኒሼቲቭ ከውጭ የሚገባ ስንዴን ሙሉ ለሙሉ በማቆም አሁን ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር ሆናለች። የወተት፣ የዶሮና የማር ምርቶች በየቤተሰቡ ሌማት ላይ እንዲገኙ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ጅማሮው መጋቢት ነው፡፡

እነዚህ ባለፉት ስምንት ዓመታት ኢትዮጵያን ከውስብስብ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አዲስ የከፍታ ምዕራፍ ካሸጋገሩ ድሎች ጥቂቶቹ ናቸው።

በመሆኑም ለሕዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገራችን ክብርና ብልፅግና መሳካት አበክረን እንሰራለን።

02/04/2026
02/04/2026

እናስታውስዎ! የምርጫ ካርድ ወሰደዋል?

የካቲት 28 የጀመረው የመራጮች ምዝገባ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

እርስዎም መብትዎን ለመጠቀም ተመዝግበው የምርጫ ካርድ ይውሰዱ!

01/04/2026

የመጋቢት 24 ፍሬዎች

በሐረር ከተማ እና የጀጎል የኮሪደር ልማት ለኑሮና ለሥራ ምቹ ከመሆን በተጨማሪ የከተማዋን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን አስችሏል።

Address

Haraar
Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Faris kadir posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share