28/08/2026
ታቦር ክ/ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪ የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የ2019 ዓመት ዕቅድ ማስተዋወቂያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ።
22/12/2018ዓ.ም
ታቦር ክ/ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪ የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የ2019 ዓመት ዕቅድ ማስተዋወቂያ የንቅናቄ መድረክ በክፍለ ከተማዉ የሚገኙ በግልና በማህበር የተደራጁ የዘርፉ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ተወካዮች በተገኙበት ተካሄደ ።
የንቅናቄውን መድረክ በንግግር የከፈቱት የሀዋሳ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ግዛዉ ስሆኑ ባስተላለፉት መልዕክት በአራቱም አምራች ዘርፍ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አምራቾች ለሀገሪቱ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አንጻር በተገቢው ልደገፉ አንደሚገባ አንስተው ችግሮቻቸውንም ሆነ ተሞክሮዎቻቸውን ለመለወጥ በተናጠል ከሚደረገው እንቅስቃሴ ይልቅ እንደዚህ ባለው ህጋዊ ማዕቀፍ መደራጀት ተገቢ መሆኑን በማንሳት ሁሉም ለም/ቤቱ መጠናከር የበኩሉን እንድወጣም ጥሪ አስተላልፈዋል።
መድረኩን የመሩት ታቦር ክ/ከተማ ኢንዱስትሪ ል/ጽ/ቤት አቶ ዮናስ ክንታሞ እና የሀዋሳ ከተማ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕረዚዳንት ከአቶ አብርሃም ቶማ በጋራ ስሆን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በም/ቤቱ ም/ፕረዚዳንት በአቶ ዮሐንስ ጌታሁን በዝርዝር ቀርቦ በተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየቶች ቀርበዉ በመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ በሰፊው ዉይይት ከተደረገ በኋላ ጸድቀዋል።