Remu Yeberhiwa Tube

Remu Yeberhiwa Tube ኢትዮጵያ

መልካም ሚስት.....!!🍃🕯 ˓٭˛ ،🌸📌 قال مسلمـة بن عبـد الملكـ رحمـہ اللـه :-🌼 المـــرأة الصالحـــة خير للمـــؤمن من : العينيــن ـ ...
04/03/2023

መልካም ሚስት.....!!
🍃🕯 ˓٭˛ ،🌸

📌 قال مسلمـة بن عبـد الملكـ رحمـہ اللـه :-

🌼 المـــرأة الصالحـــة خير للمـــؤمن من : العينيــن ـ واليديــــن ـ والرجليــــن .

መልካም የሆነች ሚስት ከሙዕሚን ..ከሁለት አይን፣ ከሁለት እጅና ከሁለት እግር በላጭ ነች።

📓📔 أحسن المحاسن للثعالبـﮯ 【 ٣٦٨ 】
‌‌‎

15/02/2023
16/09/2022
14/09/2022
13/09/2022

አላህ ጀነቴን በእግሯ ስር ያደረጋት እናቴ እንደነገረቺኝ መስከረም 2 1981 ሰኞ ለሊት ሸኽ ዩሱፍ የሱብሒ አዛን ሲሉ ነው በምወዳት ትውልድ መንደሬ ሜጢ ወደ ዱንያ የመጣሁት። ያው እናት ምንም ዓይነት ክስተት አይረሳትም አይደል? እነሆ 34ኛ ዓመት😳። አይ ዱንያ

ይህን ቀኔን በዶክተር ጣሪቅ ሱወይዳን የህይወት ትዝብት ውስጥ ላሳልፈው

"ክፍተቱ የአካል ክፍሌ ሳይሆን የልቦናዬ ነው"

1. ረዥም ሰዓት ስራ ላይ ሳሳልፍ አካሌ ይችላል። ሰላት ስሰግድ ግን ቶሎ ለመጨረስ ስል አጭር ምዕራፍ አነባለሁ። ስለዚህ አካሌ ረዥም መቆም እየቻለ የማሳነሴ ሚስጥሩና ክፍተት የልቤ እንጂ የአካሌ አይደለም።

2. ለይል ልሰግድ የምችልበት ስንት ጊዜ ለእርባና ቢስ ጉዳይ ለሊት ነቅቼ ቁጭ ብያለሁ። ነገርግን ልቤ ከንቃት ርዝመት ደክሞት አንቀላፍቷል። ይህም የልቤ እንጂ የአካሌ ክፍተት አይደለም።

3. ለ16 ተከታታይ ዓመታት የልጆቼን የትምህርት ጉዞ ለማሳመር ስል በጊዜ ስቀሰቅሳቸውና ስጥር ለሶላተል ፈጅር ለመቀስቀስ ግን ሲያቅተኝ ነበር። ይባስ ራሴንም አሰነፍኩት። ችግሬ ማልዶ መነሳት ላይ ሳይሆን ልቤ ለአላህ መንቃት ስላቃተውና ዱንያዊ ጉዳዬች ላይ ስለተሰቀለ ነበር። ስለዚህ ችግሬ የአካሌ ሳይሆን የልቦናዬ ነው።

4. ረዥም ሰዓት ወስጄ ቁጭ ብዬ የዱንያን ክስተቶች ዜና እና አሉባልታ ሳነብ ያልደከምኩ፣ ግማሽ ሰዓት ወስጄ ቁርአን ማንበብና ዚክር ማድረግ ያቅተኛል። ስለዚህ ክፍተቱ የልቤ እንጂ የአካሌ አይደለም።

5. ትምህርቴን በሚገባ ሳጠና እና ተፈትኜ ውጤታማ ለመሆን ስተጋ፣ ህይወቴን በሙሉ የዘነጋሁት ሌላ ስራ እንዳለኝና ሞቼ ሌላ ፈተና እንደሚጠብቀኝ እረሳዋለሁ። እርሱም የተፈጠርኩለት ዓላማ ሲሆን አላህን መታዘዝና ለርሱ ማደር ነው። ስለዚህ ክፍተቱ የልቤ እንጂ የአካሌ አይደለም።

6. ለመፀዳዳት፣ ለመብላት፣ ለመስራት፣ ለመማር ለመዝናናት፣ ለመሳቅና ለመጫወት ጊዜ አገኛለሁ። እናም ችግሩ የጊዜ ማጣት ሳይሆን ልቤ ለዒባዳዎቼ ጊዜ መስጠትን አለማሰቡ ነው። እናም ችግሬ የልቤ እንጂ የአካሌ አይደለም።

በአጠቃላይ ችግሩ አላህም የማንችለውን ካለማሸከሙና ስለማንችል ሳይሆን፣ የልባችን ተነሳሽነት ችግር ነው። በለት ተለት በሕይወት ብልጭልጮች፣ በአካል ፍላጎቶች መንጠልጠሏ አበላሽቷታል። አላህ ሆይ ! ዝርያችንንና ወዳጆቻችንን ሁሉ ንፁህ ልቦና ለግስልን። ያ ሐዩ ያ ቀዩም!"
በዱዓ

https://t.me/mettiey

Address

Riyadh

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Remu Yeberhiwa Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Remu Yeberhiwa Tube:

Share