Mery's page

Mery's page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mery's page, Men's clothes shop, Addis Ababa.

18/12/2022

«ከትዳር በፊት ማወቅ የሚገባን ነጥቦች በጥቂቱ»!

1.አትቆጣ፣-ቁጣ ትዳርን ይገላል።
2.እምነት ይኑርህ፣-እምነት ማጣት ትዳርን ያፈርሳል።
3.ድክመት አይኑርህ፣- ድክመት ትዳርን ያቀዘቅዛል።

5.የሰው ወሬ አትስማ፣-የሰው ወሬ ትዳርን ያፈርሳል።

6.ቸልተኝነት አይኑርህ፣-ቸልተኝነት ትዳርን ይገላል።
7.እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን አትበል፣-እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን ማለት ትዳርን ያቀዘቅዛል።

8.ለሚስትህ እንክብካቤ ይኑርህ፣-ለሚስትህ እንክብካቤ አለማድረግ ትዳርን ያቀዘግዛል።

9.ገንዘብን አታባክን፣- ገንዘብ ማከን ትዳር ውስት እንከን ይፈጥራል።

10.የጓደኛ ብዛት አይኑርህ ፣-የጓደኛ ብዛት ትዳር ውስጥ ችግር ይፈጥራል።

11.አትቅና፣-መቅናት ትዳርን ይገላል።
12.ራስ ወዳድነት አትሁን፣-ራስ ወዳድነት ትዳርን ያፈርሳል

13.የሚስትህን ፍላጎት አዳምጥ፣-የሚስትን ፍላጎት አለማዳመጥ ትዳርን ያፈርሳል።

14.ሱስ አይኑርህ፣-ሱስነት ትዳርን ይገድላል።
15.የራስህን ፍላጎት አትከተል፣-የራስን ፍላጎት መከተል ትዳርን ያፈርሳል።

16.ከሚስትህ ጋር የምክክር ሰዓት ይኑርህ፣-ከሚስትህ ጋር የምክክር(የንግግር)ሰዓት አለመኖር ትዳርን ይገላል።

17.ከልክ በላይ የዋህ አትሁን፣-ከልክ በላይ የዋህነት ትዳርን ያቀዘቅዛል።
ከወረት የጸዳ ፍቅር እግዚአብሔር ለሁላችንም ይስጠን!

30/07/2022
12/07/2022

"ተስፋ የመኖር ምክንያት ነው። ሰውን እንዲኖር የሚያደርገው ወይም የሚገፋው መለወጥ ያለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተሰፋው ነው።...."

08/07/2022



ብዙዋቻቹ ምስሉ በማህበራዊ ሚዲያዋች ሲዘዋወር አይታቹ ይሆናል። ማንዚማን ኤሊ ይባላል።

ማንዚማን ኤሊ በደቡብ ሩዋንዳ በምትገኝ አንዲት መንደር ለየት ባለ አፈጣጠሩ በሰፈሩ የተጠላ፣የተገፋና እንደዝንጆሮና ጉሬላ የሚቆጠር የ23 አመት ልጅ ነው፡፡

ማንዚማን ኤሊ ከቤቱ የወጣ እንደሆን መንደርተኛው ሁሉ ዝንጆሮ ዝንጆሮ ጉሬላ ጉሬላ …እያለ ይጮህበታል።
ማንዚማን ኤሊ ድምፅ የሚረብሽው አይነት ልጅ ስለነበር ጩህቱን ሽሽት መንደሯን ለቅቆ ወደ ጫካ ይሮጣል። መከረኛ እናቱ ልታስቆመው እያለቀሰች ትከተለዋለች፡ ማንዚማን ሲሮጥ ፈጣን በመሆኑ ለእናቱ እሱን ማስቆም በጣም ከባድ ነው።

እናቱ ልጇን ለማስቆም በሳምንት ብዙ ርቀቶች የሮጠችበት ግዜያት ነበሩ …በዚህ ሁኔታ መቀጠል ቢከብዳት ከገመድ በተሰራ መጥለፍያ ተጠቅማ መሮጥ ሲጀምር ጠልፋ ትይዘዋለች፡፡
እናቱ አምስት ልጆችን ወልዳ የሞቱባት ሲሆን ማንዚማን ለፈጣሪ ተስላ የተሰጣት ልጅ ነው። ምንም እንኳ ማንዚማን በመንደሩ እንደ ዝንጆሮና ጉሬላ የሚታይ ልጅ ቢሆንም ለእናቱ የፀሎቷ ምላሽ፡ በረከቷ፡ብቸኛ የስለት ልጅ ነው።

ስለዚህ ተከትላው ብትሮጥ፡ስለሱ ብትዘለፍ፡ስለሱ ብትሰደብ ታክቷትና ሰልችቷት አያውቅም።
ከለታት አንድ ቀን የማንዚማንን ህይወት የቀየረ የእናቱን እንባ ያበሰ ነገር ተፈጠረ…afrimax english የተባለ ማሀበራው ድረገፅ በልጁ ታሪክ በመሳብ ታሪኩ ላይ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፍልም ለአለም እንካቹ አለ።

የማዚማን እናት አምስት ልጆችን ወልዳ የሞቱባት ቢሆንም ከባለቤቷ ጋር በርከክ ብሎ ነብስ ያለው ልጅ እንዲሰጣቸው ፈጣሪን ለምኖ ከፈጣሪ የተሰጣቸው ውድ ልጇ መሆኑን፡ አባቱ ልጁ በተወለደ በሁለተኛ አመቱ በመምቱ ማንዚማንን የማሳደጉ ሀላፋነት በእናቱ ጫንቃ ላይ የተጣለ መሆኑን በዘጋቢ ፋልሙ ተናግራለች።

ይህ ዘጋቢ ፋልም ከተለቀቀ በኋላ ማንዚማን በብዙዋች ዘንድ መናጋገርያ ሆነ። አለም አቀፍ የዜና አውታሮች ሁሉ የፋት ለፋት ገፅ እርዕስ አደረጉት።

በታዳጊው ታሪክና በእናቱ ፅናት የብዙዋቹ ልብ ተነካ። እንዴት እንርዳቸው በምን እናግዛቸው የሚሉ የእርዳታ እጃቸውን የሚዘረጉ በዙ…የዘጋቢ ፋልሙ መለቀቅ ተከትሎ በተከፈተ gofundme (ጎ ፈንድ ሚ) አካውንት በስማቸው ተከፈተ።

የማንዚማን እናት የዚህ አይነት ፍቅር ከአለም ላይ አለ? ብላ እስክትጠይቅ ብዙ የእርዳታ እጆች ተዘረጉላት። በህልም አለም ያለች እስኪመስል በአካወንታቸ ሚሊዮን ዶላሮች ተለገሰ።

የፅናትዋ ዋጋ፡ የምስጋናዋን ክፍያ ተቀበለች። ታሪክ ተቀይሮ ልጇን ዝንጆሮ ዝንጆሮ… እያሉ ያሳድዱት የነበሩ ሳይቀሩ አብረውት ፎቶ ሊነሱ ይማፀኑት ጀመረ።
…አምላክ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ሆነው በልጆቻቸው ተስፋ የማይቆርጡ እናቶችን እንባ ያብስ…
©Book for all

ይህን ታሪክ ሼር ካረጋችሁት የታሪኩ መልክት እንደገባችሁ እንረዳለን

13/06/2022

በአንድ ወቅት ጫካ ውስጥ መውለጃዋ የቀረበ አንዲት ሚዳቆ ነበረች ።🦌 መውለጃ ሰዐቷ ደርሶ ትግል ላይ ሳለች ድንገት አከባቢዋን ስትቃኝ ከፊት ለፊቷ ወንዝ ፣ ከኋላዋ ቀስት ያነጣጠረባትን አዳኝ፣ ወደ ጎን ስትዞር የተራበ አንበሳ አሰፍስፎባት ትመለከታለች።
ይህም ሳይበቃት ጭማሪ ከፍተኛ ነጎድጓድና መብረቅ ያጀበው ደመና መጥቶ ሰማዩን ያጨልመዋል።💭💭
መብረቁም ከፍተኛ ነበርና ደኑን ይመታና ከፍተኛ ቃጠሎን ያስነሳባታል።⚡😱አስቡት ያለችበትን ጭንቅ 😟😱...

ወደ ፊት ሮጣ እንዳታመልጥ ጥልቅ ወንዝ ተደቀነባት፤ከኋላዋ አዳኙ፤ከጎኗ ደግሞ አንበሳው፤ወደ ጫካ ገብታ እንኳ እንዳትደበቅ ከፍተኛ ቃጠሎ ላይ ነው... በዚያ ላይ የውልደት ህመም ነፍስ ውጪ ግቢ እያስባላት ነው ...

ትኩረቷን መፈፀም ወደ ምትችለው ነገር ላይ ብቻ በማድረግ ቀሪውን ለፈጣሪ በመተው በመወለድ ላይ ስላለው ልጇ ብቻ ማሰብ ጀመረች።🤔🤔

የመብረቁ ብልጭታ💥 አይኑን ብዥ ያደርግበትና ቀስቱ አምልጦት ወደ ተራበው አንበሳ ይሄድና አንበሳውን ይገለዋል።
አጉበድብዶ የነበረው ደመናውም መዝነብ ይጀምርና የደኑን ቃጠሎ በቅፅበት አጠፋው።👏👏
በጭንቅ ታጅባ የነበረችው ሚዳቆም በሰላም ተገላገለችና ወደ ቀደመው ሂይወቷ ተመለሰች ይባላል.🤗🤗🤗🤗

#መልእክቱ

አንዳንዴ በህይወትህ ውስጥ በብዙ ፈተናዎችና ጭንቀቶች ልትከበብ ትችላለህ ያኔ አንተ ልትፈታው በምትችለው ነገር ላይ ብቻ አትኩርና ቀሪውን ለመፍትሄዎች ሁሉ ባለቤት ለ ፈጣሪህ ተወው።💚💚
መውጫ መፍትሄ አንተ ጋ እንጂ ፈጣሪህ ዘንድ አይጠፋም.
ብለህ ለጭንቆች እውቅና ከመስጠትህ ይልቅ የትላልቅ ጭንቀቶች አለቃ የሆነው ጌታ አለኝ እያልክ ጭንቀቶችህን አቅልላቸው።
በፈጣሪህ ፈፅሞ ተስፋ አትቁረጥ በጠረጠርከው ታገኛዋለህ

melat tesfya

10/06/2022
17/05/2022

የተከፈለ ውለታ

አሜሪካን ካንሳስ ሲቲ ነዋሪ የሆነችው ሳራ ዳርሊንግ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያዋ በማቅናት ላይ ሳለች አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ከመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሲለምን ትመለከታለች

ሳራ ወደ አዛውንቱ በመጠጋት ቦርሳዋን ከፍታ የተወሰኑ ዶላሮችን ሰውየው ከጎኑ ባስቀመጠው የፕላስቲክ ኩባያ ውስጥ አኑራ ጉዞዋን ትቀጥላለች

ሳራ ከምንግዜውም በላይ በህይወቷ ደስተኛ ነበረች ከምትወደውና ከምታፈቅረው ጓደኛዋ ጋር በትዳር ለመጣመር የቀናት ዕድሜ ቀርቷቸዋል።

ለእሷ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር ያለው ፍቅረኛዋ እጅግ ውድ የሆነ 💍ዳይመንድ💍የቃል ኪዳን ቀለበት ገዝቶ በጉልበቱ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ካቀረበላት እና በደስታ እሺ ካለችው ጊዜ አንስቶ ህይወቷ በሀሴት ተሞልቷል

ምሽት ላይ እንደተለመደው በስስት የምታየውን የዳይመንድ ቀለበት ስማ ለመተኛት ቦርሳዋን ከፈተችው በድንጋጤ ደርቃ ቀረች ቀለበቱ በቦታው አልነበረም።

ቦርሳዋን የከፈተችው መንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ለሚለምነው አዛውንት ገንዘብ ለመስጠት ብቻ እንደነበር አስታውሳ የሰውየው ገንዘብ መሰብሰቢያ ኩባያ ውስጥ ቀለበቱን አብራ ማኖሯን አስታወሰች።

ለእጮኛዋ ስልክ በመደወል ሁኔታውን አጫወተችው እጮኛዋም ሲከንፈ መጣ
ተያይዘው በልመና ወደ ሚተዳደረው ሽማግሌ ቦታ ሄዱ ሰውየው በቦታው አልነበረም "በእርግጥ ውድ የሆነ ቀለበት አግኝቶ እንዴት ተመልሶ በቦታው ሊቀመጥ ይችላል" የእጮኛዋ ግምት ነበር

በቀጣዩ ቀንም በተመሳሳይ ከእጮኛዋ ጋር ሽማግሌው ተቀምጦ ወደ ሚለምንበት ቦታ ሄዱ አሁንም ሰውየው አልነበረም በቃ ጦስሽን ይውሰድ ከእንግዲህ እርምሽን አውጪ ነበር የእጮኛዋ መልስ በሦስተኛው ቀንም ሳራ ለእጮኛዋ ደውላ ወደ ሽማግሌው ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀችው እጮኛዋ በመገረም "6 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ቀለበት ችግረኛ እና በረንዳ የሚያድር ሰው እጅ ገብቶ አገኘዋለሁ ብለሽ እንዴት ታስቢያለሽ ?" ነበር ያላት ... ሳራም በቃ የዛሬን ብቻ እንየው ሰውየው ከሌለ እርሜን አወጣለሁ አለችው

እጮኛዋም የሳራን ፍላጎት ለመሙላት ተስማምቶ ጉዞዋቸውን አቀኑ ሽማግሌው በቦታው ተቀምጦ ሲለምን አገኙት
ሳራ በደስታ ተዋጠች አላውቅሽም ብሎ እንዳይሸመጥጠኝ የሚል ስጋት እንደዋጣት ወደ ሽማግሌው ተጠጋች

አባት ያስታውሱኛል ? በማለት ጠየቀች ሽማግሌው ቢል ሬይ ሀሪስ ይባላል ቀና ብሎ ተመልክቷት አላወቅኩሽም ልጄ ሲል መለሰላት

ሳራም ከ3 ቀን በፊት ከቦርሳዬ ገንዘብ አውጥቼ ሳስቀምጥ ሌላ ዕቃ አብሬ አኑሬ ነበር ?!
የጣት ቀለበት ነው ?
አዎን አባት
ቢል ቀለበቱን ጠቅልሎ ካስቀመጠበት ኪሱ በማውጣት አንድ ቀን እንደምትመለሺ አውቅ ነበር በማለት ከሰጣት ብኋላ ... ቀለበቱን ያገኘሁት ዕለት ትክክለኛ ወይም አርቴፊሻል ቀለበት መሆኑን ለማወቅ ወደ ጌጣጌጥ ሱቅ ወስጄው ነበር እነሱም ትክክለኛ መሆኑን ነግረው $4,000 ዶላር ሊገዙኝ ጠይቀውኝ ነበር።

በእርግጥ ኑሮውን በበረንዳ ለሚያሳልፍና በልመና ለሚተዳደር 4ሺህ ዶላር ከፍተኛ ገንዘብ ነው ነገርግን እኔን ለመርዳት ብላ በስህተት ቀለበት የጣለችን ሴት ንብረት መንካት አልፈለግኩም። በመሆኑም በጥንቃቄ አኑሬው የአንቺን መምጣት ስጠባበቅ ነበር። ሲል መለሰላት

ሳራ ዳርሊንግ እና እጮኛዋ የመልካሙን ቢል ሬይ ሀሪስ ታሪክ ከታች ቀለበቷን ሲሰጣት ከሚታየው ምስል ጋር በማያያዝ በሶሻል ሚዲያ (Facebook) አበቁት ከታሪኩም ጎን ለጎን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ አካውንት ከፈቱ በቢል ሬይ ቀናነት እጅጉን የተደሰቱ አያሌ ግለሶቦች የዕርዳታ እጃቸውን ይዘረጉ ጀመር በአጭር ጊዜ ውስጥ 260,000$ ዶላር ተሰበሰበለት

በአሁን ሰዓት ቢል ከበረንዳ አዳሪነት ወጥቶ የቤት ባለቤት ሆነ ተጨማሪ የመጦሪ ገንዘብም አገኘ

መልካምነት መልሶ ይከፍላል ይሉሀል ይሄ ነው 😉

ምንጭ :- ከፌስቡክ ግድግዳ በያላችሁበት ሠላማችሁ ይብዛልኝ ወዳጆቼ❤❤❤

መቃብሩ በፈርጣማ ወታደሮች ተጠበቀ። በትላልቅ ደጎራ ተዘጋ።አይሁዶች በደስታ ሰከሩ።ጣሊያውያን ፖለቲከኞች በፍርዳቸውረኩ።እናቱ እንባዋ እንደ ጅረት ፈሰሰ። ሐዋርያት የሀዘን ደመናከበባቸው። ከበ...
24/04/2022

መቃብሩ በፈርጣማ ወታደሮች ተጠበቀ። በትላልቅ ደጎራ ተዘጋ።
አይሁዶች በደስታ ሰከሩ።ጣሊያውያን ፖለቲከኞች በፍርዳቸው
ረኩ።
እናቱ እንባዋ እንደ ጅረት ፈሰሰ። ሐዋርያት የሀዘን ደመና
ከበባቸው። ከበረከቱ፣ ከፈውሱ የተጠቀሙት ሕዝቦች በአምላክነቱ
ተጠራጠሩ። ጥቂቶቹ በሀሰት በመገደሉ አለቀሱ።
እውነት በዝምታ ተቀበረች።
ነገር ግን ሙታንን የሚያስነሳው አምላክ መቃብሩን ፈንቅሎ ወጣ -
እሁድ ሌሊት 6:00።
የአርብ ልቅሶ በእሁድ ደስታ ተሻረ። የወላጅ እናቱ የጠነከረ ሀዘኗ
እንደ ጤዛ ተነነ። ሐዋርያት በደስታ ተሰባበቡ። የተጠራጠሩት ወደ
ማመን ተመለሱ። የተቀበረችው እውነት ተገለጠች።
በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም እምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች የድንግል ማርያም ወዳጆች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ

28/03/2022
23/03/2022

እንደ እርግብ የዋህ ሁን።
እንደ እባብ ዝቅ በል መሬት ሁንላቸው። ዱላ ይሰንዝሩብህ።ጭንቅል ጭንቅላትህን ይቀጥቅጡህ። ምንም አትሆንም ግፋ ቢል ራስህን ቢያምህ ነው። እንዲገድሉህ ግን አትፍቀድላቸው። መሬት ልሰህ ተነሳ።

ከሞትክ ግን እሬሳ ትሆናለህ። ዋጋም አይኖርህም። በቃ ያንተ ነገር ያበቃል።
ነግሬሃለው። እኔ የለሁበትም።

16/03/2022

"ሰይጣን ቤተክርስቲያን ሄድሽ አልሄድሽ አይጨንቀውም፡፡" አሉ የቆሙት እማሆይ፡፡ ቀጥለውም፡ "መጽሐፍ ቅዱስም አነበብሽ አላነበብሽ ሰይጣን አይከፋውም፡፡" አሉ
"ታዲያ ሰይጣን የሚጨንቀው እና የሚከፋው መቼ ነው?" ስትል ጠየቀች ሳያት፡፡
"ቤቴክርስቲያን ሄደሽ የሰማሽውን እና መጽሐፍ ቅዱስ አንብበሽ የተረዳሽውን ነገር መኖር ስትጀምሪ ሰይጣን አብዝቶ ይከፋል፡፡" አሉ፡፡
"ልጄ ዋናው ነገር መኖር ነው፡፡ያወቅሽውን ካልኖርሽ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፡፡የህይወትሽ ቤት አሸዋ ላይ የተገነባ ነው፡፡መኖር ስትጀምሪ ግን በማይናወጥ አለት ላይ የተገነባ ህይወት ይኖርሻል፡፡ለመኖር ደግሞ በጀመርያ ፈጣሪሺን ከልብ ማክበርና ማፍቀር አለብሽ፡፡" አሉ የተቀመጡት እማሆይ ደግሞ፡፡
"ችግሩ የዘመኑ ወጣቶች የአምላክን ፍቅር አታውቁም፡፡ልባችሁን የሞላው አለማዊ ነገር ብቻ ነው፡፡" ሲሏት የቆሙት እማሆይ፡
"ቆይ የፈጣሪ ፍቅር ምን ይመስላል?" ብላ ጠየቀቻቸው፡፡
"ይሄውልሽ ልጄ ሰው የሚሰጥሽ ፍቅር ወቅታዊ ነው፡፡ገንዘብ፣ ዝና፣ ውበት፣ ሀብት፣ እውቀትም ሆነ ሁሉም የአለም ነገሮች ከንቱ ናቸው፡፡አላፊ እና ጠፊ ናቸው፡፡አንድ የማያልፍ ነገር የፈጣሪ ፍቅር ብቻ፡፡ፈጣሪ ራሱ ደሞ ፍቅር ነው፡፡ስትቀምሺው በቃ ነፍስሽ እረፍት ታደርጋለች፡፡ከእሱ ውጪ ምንም አያምርሽም፡፡ልብሽ ቅልጥ ትላለች፡፡" አሉ የተቀመጡት እማሆይ፡፡
"ይገርማል!. ....ታድላችኋል!" አለች ሳያት አቀርቅራ፡፡
"አንቺም እኮ ታድለሻል!" ሲሉ የቆሞት እማሆይ መለሱላት፡፡ካቀረቀረችበት ቀና ብላ፡
"ምንድን ነው የታደልኩት?" ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
"ውበት ነዋ፡፡በጣም ውብ እና ቆንጆ ልጅ ነሽ፡፡"
"ታዲያ ምን ያደርጋለ አላፊ እና ጠፊ ነው አላላችሁም!"
"ቢሆንም እስኪጠፋ ድረስ በተሰጠሽ ጸጋ የማይጠፋ ስራ መከወን አለብሽ፡፡እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው የተለያየ ጸጋ ስጥቷል፡፡ለሙሴ ህግ ለሰለሞን ጥበብ፣ ለዕዮብ ትዕግስት፣ ለጳውሎስ መልዕክ፣ ለማርያም ቅድስና እንደሰጠው ለእኛም የሰጠን ጸጋ አለው፡፡እግዚአብሔር ቁንጅና፣ ስልጣን፣ እውቀት፣ ምንኩስና፣ ድምጽ ወዘተ ነገር ሲሰጠን በአላማ ነው፡፡" አሉ የተቀመጡት እናት፡፡
"አላማው ምንድን ነው?" አሁንም ጠየቀች ሳያት፡፡
"አላማው በተሰጠን ጸጋ ማገልገል ነው፡፡ሰዎችን መርዳት እና በመልካም ስራችን የፈጣሪ ብርሃን በእኛ ውስጥ እንዲያበራ ማድረግ ነው፡፡አለምን የተሻለች ቦታ ማድረግ ነው፡፡በጎ ስራችንን ሰዎች ተመልክተው ፈጣሪን እንዲያመሰግኑ ማድረግ ነው፡፡" አሉ እማሆይ፡፡
"ብዙ ሰው ግን እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ ይጠፋበታል፡፡አብዝቶ በዛ እየተመካ ይሰነካከላል፡፡ይወድቃል፡፡አንቺ እንዴት ነሽ?
በቁንጅናሽ ምን እያደረግሽ ነው? " ተጠየቀች ሳያት፡፡
"እንዳላችሁት ባይሆንም በተቻለኝ መጠን በምሰራው ስራ ሰዎችን ለማነቃቃት እጥራለው፡፡በተለይ የአገሬ ሴቶች የተሻለ ቦታ ደርሰው የማየት ጉጉት አለኝ፡፡" ስትል መለሰች፡፡
"አይዞሽ ልጄ፡፡ጉጉት ካለሽ መንፈስ ቅዱስ ያሳካልሻል፡፡ባንቺ ውስጥ አልፎ የልብሽን መሻት ይፈጽማል፡፡ዋናው ነገር ያለው ልብ ላይ ነው፡፡እሱ ከጸዳ ሌላው ቀላል ነው፡፡" አሉ የቆሙት እማሆይ፡፡
"መጠንቀቅ ያለብሽ ደስታሽን አለማዊ ነገር ላይ እንዳይሆን ነው፡፡ሁላችንም በዚህ ምድር ለኮንትራት ህይወት የመጣን ነን፡፡ቀናችን ሲደርስ እንሄዳለን፡፡እስከዛ ግን ራሳችንን ለዘለዓለማዊው ህይወት ማሰናዳት ይገባናል፡፡እሱም ከምንም ነገር በፊት ፈጣሪን አስቀድሞ መኖር ነው፡፡በሙሉ አእምሮ፣ አንደበት፣ መንፈስና ጉልበታችን ፈጣሪን ካፈቀርን የምድር ህይወት አይከብደንም፡፡እንዲሁም ወደ መንፈሳዊው አለም የምንወጣበት ቆንጆ መሠላል ይሆናል፡፡"

Address

Addis Ababa
123

Telephone

+251921794497

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mery's page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mery's page:

Share