Abdi Tube

Abdi Tube for sale

አረብ ሀገር ለምትኖሩ በሙሉ
02/03/2026

አረብ ሀገር ለምትኖሩ በሙሉ

ቪዲዮ ቀርጾ ፖስት ማድረግ ያስቀጣል?

የ6ቱ መሻዒኾች የሞባይል መተግበርያ ተመረቀ ። በዛሬው እለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ፣ የምክር ቤቱ የፕሬዝዳንት...
28/02/2026

የ6ቱ መሻዒኾች የሞባይል መተግበርያ ተመረቀ ።

በዛሬው እለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ፣ የምክር ቤቱ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ጨምሮ ታላላቅ መሻዒኾች ፣ ዱዓቶችና የማህበረሰብ መሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ስቴይ ኢዚ ሆቴል የ6 መሻዒኾችን ሸሪዓዊ አስተምህሮ የያዙ የሞባይል መተግበርያዎች ተመርቀዋል ።

መተግበሪያቸው ይፋ የሆኑት 6ቱ መሻዒኾች ማለትም ( የመተግበርያው ሊንክ ከስር ተያይዟል ) :-

1. ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጦፋ
https://play.google.com/store/apps/details?id=tv.africa.seid&pcampaignid=web_share

2.ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.africa.mohammedzain

3. ሸይኽ ኢብራሂም ሲራጅ ( ረህመቱላህ አለይሂ )
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sheikhibrahimsiraj.app

4. ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bewidetechnologies.muhammedhamidin

5. ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bewidetechnologies.hamidmusa

6. ሸይኽ ሙሐመድ ፈረጅ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sheikhmuhammedferej

እስካሁን በተለያዩ መንገዶች ሲያቀርቧቸው የነበሩ ሸሪዓዊ ትምህርቶችን በእያንዳንዳቸው ስም በበለጸጉ የሞባይል መተገበርያዎች ማግኘት የሚቻልበት ነው ። የሞይባል መተገበርያው በአፍሪካ ቲቪ እና ቢዋይድ ቴክኖሎጂስ በትብብር የበለጸገ ሲሆን በመድረኩ ላይ አፍሪካ ቲቪ ለዳዕዋ ስራ እያደረገ ያለው የላቀ አበርክቶ ተወስቶ ተመስግኗል ። መተግበርያው አዳዲስ የዑለሞቹን ትምህርቶች እያካተተና እየተሻሻለ እንደሚሄድ ተገልጿል ።



የ6ቱ መሻዒኾች የሞባይል መተግበርያ ተመረቀ ። በዛሬው እለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ፣ የምክር ቤቱ የፕሬ.....

https://invite-poppo.com/zyncCA Download the app to meet more interesting friends from all over the world!  My ID:485743...
16/02/2026

https://invite-poppo.com/zyncCA Download the app to meet more interesting friends from all over the world! My ID:48574386

በዚህ ቪዲዮ አዲሱን እና በኢትዮጵያ በስፋት እየተሰራበት ያለውን የPoppo Live መተግበሪያ ሙሉ አጠቃቀም አሳያችኋለሁ። እንዴት አካውንት መክፈት እንደሚቻል፣ ሰዎችን በመጋበዝ (Invite) እንዴ....

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጠቅላይ ም/ቤቱ ማቋቋሚ አዋጅ ቁጥር ...
18/11/2025

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጠቅላይ ም/ቤቱ ማቋቋሚ አዋጅ ቁጥር 1207/2012 እና በህገ መጅሊስ 2015 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ማንኛውም የመንግስት አካል የሚወስናቸው ውሳኔዎች እና የሚፈጽማቸው ተግባራት የህዝበ ሙስሊሙን ሀይማኖታዊ መብት የሚጋፉ/የሚጣረሱ መሆናቸው ሲያረጋግጥ እርምት/ማስተካከያ እንዲደረግ የማድረግ ሙሉ ሀላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

በዚሁ መሰረት የብዝሀ ሃይማኖት ባለቤት የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ በልዩነት ውስጥ ያለ መከባበርና መደጋገፍ ተምሳሌት እንደሆነችና ይህም ልዩ ውበቷ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደ መንግስትም ይህንን እሴት በመጠበቅና የህዝበ ሙስሊሙ ለረዥም ግዜ ሲጠይቃቸውና ሲታገልላቸው የነበሩ ጥያቄዎች እየተመለሱ መሆኑ እናምናለን፡፡

ቀሪ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉና እነዚህም በአላህ ፈቃድ ወደ ፊት እንደሚመለሱ ተስፋም እናደርጋለን፡፡ በተጨማሪም በመንግስት በኩል ከመቼውም ግዜ በላቀ ሁኔታ ከህዝበ ሙስሊሙ መሪ ተቋም ጋር ተግባብቶና ተናቦ አመርቂ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ለዚህም ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር አብይ አህመድ እና ለመንግስታቸው እንደተለመደው ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ነገር ግን በተለያዩ ግዜያት በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የሚወሰኑ ውሳኔዎች፣ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና እየተወሰዱ ያሉ አቋሞች የህዝበ ሙስሊሙ መብት በእጅጉ የሚጋፉ ሆኖ አግንተናቸዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ከግዜ ግዜ ይሻሻላሉ፣ ከመሪ ተቋሙም ጋር በውይይት ይፈታሉ በሚል በትዕግስት ብንጠባበቅም በተለያዩ ግዜያት በክቡር የትምህርት ሚኒስተሩ በኩል እየተወሰዱ ያሉ የተናጥል እርምጃዎችና የተያዙ አቋሞች የህዝበ ሙስሊሙን መብት በእጅጉ የሚጥሱ እና በተጨባጭ ከኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግስት አቋም የተለየ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ እነዚህም፦

1. የሙስሊም ሴት ተማሪዎች የእምነት አለባበስ (ሂጃብ) ለብሶ የመማር መብት በተመለከተ፦

ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት ጀምሮ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ህጎች ብንመለከት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሀይማኖታቸው ግዴታ ያደረገባቸው ልብስ ለብሰው ትምህርት እንዳይማሩ የሚከለክል ህግ የለም፡፡ ቢኖር እንኳን በህግ መንግስቱ አንቀጽ 27 የተደነገገው የሀይማኖት፣ የእምነትና የአመለካከት ነጻነት መብት ጋር የሚጋጭ በመሆኑ እና የህገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት የማንኛውም የመንግስት አካል/ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም ይላል በመሆኑም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሀይማኖታቸው ግዴታ ያደረገባቸው ልብስ ለብሰው መማር አይችሉም የሚል የባለስልጣን የግል ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር በቀጥታ የሚጣረስ በመሆኑ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም፡፡

ነገር ግን ህገ መንግስቱ በዚህ ልክ ግልጽ ሆኖ እያለ የትምህርት ሚኒስቴር እንደ ተቋም እና ሚኒስተሩ በተለያየ ግዜ በሚያደርጓቸው ንግግሮች እና በሚሰጧቸው ማብራሪያዎች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሀይማኖታቸው ግዴታ ያደረገባቸው ሂጃብ የተሳሳተ ትርጉም ሲሰጡ እና ለብሰው መማር አይችሉም የሚል አንድምታ ያለው ንግግር ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ህዝበ ሙስሊሙ እና የህዝበ ሙስሊሙ መሪ ተቋም እያሳዘነ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስተር ወቅቱ በሚመጥኑ በተለያዩ የትምህርት ጥራት ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር በሚጠበቅበት በዚህ ወሳኝ ወቅት በየግዜው የሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ጉዳይ ለምን አጀንዳ እንዲሆን እንደፈለገ እና የተፈለገው ውጤት ምን እንደሆነ መገመት አይሳነንም፡፡

ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሌላውን መብት ሳይነኩ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የቅድመ ጥንቃቄ የደህንነት ጉዳዮች በሌሎች አማራጮች መከላከል እየተቻለ ሀይማኖታቸው ግዴታ ያደረገባቸው ልብስ ለብሰው እንዳይማሩ መከልከሉ ህጋዊ ያልሆነ እና በምንም አመክንዮ ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ ሚኒስተሩ ጨምሮ አንዳንድ አካላት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 90(2) የሚረዱበት መንገድ ከድንጋጌዎቹ አውድ ውጪ እና ከህገ መንግስቱ አጽዳቂ ጉባኤ አባላት ሃሳብና ፍላጎት ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ በተመለከተ እየወሰደው ያለው እርምጃ እና የያዘው አቋም ከህዝበ ሙስሊሙ መሪ ተቋም ውይይት ያልተደረገበትና መግባባት ላይ ያልተደረሰበት በመሆኑ በኛ በኩል አጥብቀን እንቃወመዋለን፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ በ02/03/2018 በአዳማ ከተማ በተካሄደው አገራዊ የትምህርት ጉባኤ ላይ በሂጃብም ሆነ በሰላት ጉዳይ ከመጅሊስ ሀላፊዎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል በሚል ያስተላለፉት ንግግር ከእውነት የራቀ እና እንደ መጅሊስ ከሚኒስተሩ ጋር የተግባባንበት ምንም አይነት ነገር እንደሌለ እየገለጽን በሚኒስተሩ በኩል ተቋማችን በሚመለከት ለተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ በግልጽ ማስተካከያ እንዲደረግ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

2. በአማራ ክልል ሙስሊም ተማሪዎች ግዕዝ በግዳጅ እንዲማሩ በትምህርት ቢሮው በኩል የተወሰነው ውሳኔ በተመለከተ፦

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከወላጆች እና ከህዝበ ሙስሊሙ መሪ ተቋም መጅሊስ ጋር ውይይት ሳይደረግበት ሙስሊም ተማሪዎች ያለፍላጎታቸው በግዳጅ ግዕዝ እንዲማሩ የወሰነው ውሳኔ መላው የክልሉ ህዝበ ሙስሊም እና በተለያየ እርከን ያሉ የክልሉ መጅሊስ ተቃውመውታል፡፡

ስለሆነም እንደ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም የክልሉ ህዝበ ሙስሊም እና መሪ ተቋሙ ያልተቀበለው፣ ምክክር ያልተደረገበት እና ህጻናትን በግዳጅ ለማስተማር ሊያደርግ የሚችል የህግ መሰረት በሌለበት ግዕዝን በግዳጅ ለማስተማር ያሳለፈው ውሳኔ ክልሉ ያለበትን ውስብስብ ችግር በበለጠ የሚያባብስ እና ውጤቱም እጅግ በጣም አደገኛ ሊሆን የሚችል በመሆኑ እንደ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ውሳኔው የምንቃወመው ሲሆን የክልሉ ት/ቢሮም ውሳኔው በድጋሚ እንዲያጤነው እና የእርምት እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡

የክልሉ ት/ቢሮ ውሳኔ ከአገራዊ የትምህርት ፖሊሲው እና ከአጠቃላይ የትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2016 አንቀጽ 28 እና አንቀጽ 29 ጋር የሚጋጭ በመሆኑ እና ይህንን የማስቆም ሙሉ ሀላፊነትና ጉዳዩም በቀጥታ የሚመለከተው የትምህርት ሚኒስተር በመሆኑና ትምህርት ሚኒስተር በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት ጉዳዩ እንዲያስቆመውና በህግ የተጣለበትን ሀላፊነት እንዲወጣ እናሳስባለን፡፡

3. የትግራይ ክልል ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የእምነት አለባበስ ጉዳይ በተመለከተ፦

በትግራይ ክልል ያሉ ሴት ተማሪዎች በፌደራሉም ሆነ በክልሉ ህገ መንግስት እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ህጎች የተፈቀደላቸውን የእምነት አለባበስ ለብሰው የመማር መብታቸው ተጥሶ ላለፉት 2 ዓመታት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የትምህርት ሚኒስተር ተማሪዎቹ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ምንም አይነት ጥረት አላደረገም፡፡

ይልቁንም የክልሉ መጅሊስ የተማሪዎቹ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ለማስከበር በፍ/ቤት ክስ አቅርበው ጉዳዩ እስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ደርሶ ፍርድ ቤቶቹ የተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው የመማር መብት እንዳላቸው ውሳኔ ቢሰጡም የክልሉ መንግስት የፍ/ቤት ውሳኔ ለመፈጸም አሻፈረኝ ብሎ ተማሪዎቹ እስካሁን ወደ ትምህርታቸው አልተመለሱም፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግስት በፍ/ቤቶቹ ውሳኔ መሰረት ሙስሊም ተማሪዎች ሀይማኖታቸው ግዴታ ያደረገባቸው ሂጃብ ለብሰው እንዲማሩ እንዲያደርግና የፍርድ ቤቶቹ ውሳኔ እንዲፈጽም እየጠየቅን የትምህርት ሚኒስተርም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት ተማሪዎቹ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንዲያደርግና በህግ የተጣለበትን ሀላፊነት እንዲወጣ እናሳስባለን፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የሙስሊም ተማሪዎች አሳሳቢ ጉዳይ እንደ መንግስት በዋናነት የትምህርት ሚኒስቴር በራሱ ከችግሩ እንዲላቀቅ እና ችግሩን ከስሩ እንዲፈታው እየጠየቅን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው በመሆኑ በህግ የተጣለበትን ሀላፊነት እንዲወጣ እናሳስባለን፡፡ ሌሎች የሚመለከታችሁ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ በመሆኑ በዚሁ አጋጣሚ ጉዳዩ በልዩ ትኩረት እንድታዩት እና የሰላም መደፍረስ እንዳያስከትል እናሳውቃለን፡፡

በመጨረሻም እንደ ኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤቱ ጉዳዮቹን በቅርበት እየተከታተልናቸው የምንገኝ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት ችግሮችን ጨምሮ ሌሎች ህዝበ ሙስሊሙ የሚመለከቱ ችግሮች ከስር መሰረታቸው ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይረዳ ዘንድ በዛሬው ዕለት ከተለያዩ ባለድርሻ ማለትም ከኡለማ፣ ከህግ ሙሁራን፣ ከማህበረስብ፣ ከሴቶችና ከወጣቶች እና ከሚዲያ ባለሙያዎች የተውጣጣ ከሚቴ በማዋቀር ወደ ስራ እንዲገባ ያደረግን መሆኑን እናሳውቃለን ሲል ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

29/10/2025

ከባድ ውሸት 😄
Abdi Tube

27/10/2025

ኮልፌ ተቀብረው በነበር ከተቀበሩ በኋላ ይሄ ሁሉ ንትርክና ክፍፍል በሙስሊሙ መካከል ባልተፈጠረ ነበር።

ለማንኛውም ኮልፌ በሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ጎን ቦታ ተመቻችቶላቸው እዛ ይቀበሩ ዘንድ ጥረት በማድረግ፣ ለብቻቸው አሁን በተቀበሩበት ቦታ መቀበራቸው ከፍተኛ ፊትና እንደሚያስነሳና ወደፊትም ለአላስፈላጊ ኢ-ኢስላማዊ ድርጊት እንደሚውል ገምተው የራሳችን ጥረት ያደረጉ አካላትን ሳላደንቅ አላልፍም። አላህ በጥረታችሁ ልክ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ። የቻላችሁትን ያክል ሰበብ ለማድረስ ሞክራችኋልና። አሁንም ቅርብ ነው። ቦታው ማስፋፊያ ተጨምሮበት ወይም ባለው ልክ የሁሉም ሙስሊም መደበኛ መቃብር እንዲሆንና ምንም አይነት ከሌላው መቃብር የተለየ ድርጊት እንዳይፈፀም በማድረግ ረገድ አሻራችሁን በማሳረፍ ቀጣዩ ትውልድ ሙታን አምላኪ እንዳይሆን የበኩላችሁን ሚና ተወጡ። አላህ ያግዛችሁ!

እነ ሐሰን ታጁም ጉዳዩን እንደ ማታገያ ከመጠቀምና በሬሳ ከመነገድ ተቆጥባችሁ፤ አላህን ፍሩና ወደ ቀልባችሁ በመመለስ ይህን ፋይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዝጉት። ቤተሰብም ሐዘኑን ያውጣ፣ ለግላዊና ቡድናዊ አላማ መወጣጫ አታድርጉት።

26/10/2025

«ውሀብዮች የሚያመልኩትን አምላክ ከማምለክ፤ ሙፍቲን ማምለክ ይሻላል‼
እነርሱ የሚያመልኩት አሻንጉሊት 🙄
ዑመር ኮምቦልቻ የተነገረው

26/10/2025

እጅግ አደገኛ ንግግር‼
==============
(የኮልፌ መቃብር የተሰረቀ ነው?)

(መጅሊስና መንግስት በአስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጡን ይገባል!)
||
✍ ዛሬ በሐጂ ዑመር ቤት ለተሰባሰበው ህዝብ አደገኛ ንግግር ካስተላለፉት ሰዎች መካከል አንዱ ቃሲም ታጁዲን ናቸው። ቃሲም ታጁዲን ሐጂ ዑመር በመኖሪያ ግቢያቸው የተቀበሩበትን ምክንያት ሲጠቅሱ፤ የኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ባለቤቱና ሰጪው ስለማይታወቅ፣ ምናልባትም ከሚስኪኖች ላይ በኃይል ተነጥቆ የተሰጠ ሊሆን ስለሚችል፣ ሙፍቲ በሰው ሐቅ ላይ ላለመቀበር ብለው በራሳቸው ገንዘብ በገዙት መሬት ላይ ቅበሩኝ ብለዋል… የሚል በመላው ሙስሊም ላይ ጥርጣሬን የሚነዛ ሃሳብ ተናግሯል።

የእውነት ከጥንት ጀምሮ ሙስሊሞች የሚቀበሩበት የኮልፌ መካነ መቃብር ከግለሰቦች በጉልበት ተነጥቆ የተሰጠ ሐቅ ከሆነና በዛ መቀበር አይቻልም የሚባል ከሆነ፤ መጅሊስና መንግስት ግለሰቡን ይዘው ማብራሪያ እንዲሰጠን፣ ውሸት ከሆነም ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድበት እንፈልጋለን።

እስካሁን ድረስ በዚያ መካነ መቃብር የተቀበሩትን እንደነ ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ አይነት እንቁ ዑለማዎቻችንን በሰው ሐቅ ላይ የተቀበሩ፣ እንደ ሐጂ ዑመር ለሰው ሐቅ የማይጠነቀቁ… የሚል መልዕክት ስለሚያሲዝ፤ በአስቸኳይ መፍትሄ እንፈልጋለን። ይጣራልን‼
መሰል ብዥታና ጥርጣሬ በኡማው ላይ መንዛት ከባድ ወንጀል ነው።

መልዕክቱን ለሚመለከተው ሁሉ በማድረስ እንረባረብ‼
የቪድዮ ማስረጃ አለን፤ ካጠፉት ብዬ ይዠዋለሁ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እየተመለሱ ነው************************በእስራኤል እና በሀማስ መካከል የተደረሰውን የመጀመሪያ ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ተከት...
11/10/2025

በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እየተመለሱ ነው
************************

በእስራኤል እና በሀማስ መካከል የተደረሰውን የመጀመሪያ ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አርብ ማለዳ ላይ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የእስራኤል ጦር ሰራዊቱን በከፊል ከጋዛ እንዳስወጣም ተነግሯል።

የእስራኤል ጦር በመጀመሪያ ምዕራፍ ሰራዊቱን ከስፍራው ለማስውጣት ያደረገውን እንቅስቃሴ ማጠናቀቁን መግለፁን ተከትሎም ፍልስጤማውያን በሰሜን ጋዛ ሰርጥ ወደ ቤታቸው እየተመለሱ መሆናቸውን የተገለፀው።

የተኩስ አቁሙ ስምምነቱ መተግበር ከፍተኛ መጠን ያለው የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲጓጓዝ ማስቻሉም ተመላክቷል፡፡

የመጀመሪያ ዙር ነው በተባለው በዚህ የተኩስ አቁም ስምምነት ሀማስ በሕይወት የሚገኙት 20 የእስራኤል ዜጎችን በ72 ሰዓታት ውስጥ ይለቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ እስራኤል በበኩሏ በእስር ላይ የሚገኙ 250 ፍልስጤማውያንን እንደምትለቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በእስራኤልና ሀማስ መካከል ያለውን ግጭት እንዲቆም በአሜሪካ የቀረበው የሰላም ስምምነት በብዙ ሀገራት ድጋፍ ማግኘቱ ተጠቅሷል፡፡
Abdi Tube

 #ቴሌግራም
11/10/2025

#ቴሌግራም

SUBSCRIBE. SHER LIKE #

11/08/2025


to create YouTube channel how to make money

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abdi Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share