Hailu Buge Atumo

Hailu Buge Atumo All are on this

22/06/2025

📶 #አትመኝ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡
📶 #አትቅና፦ እንደ ቃየን ወንድምህን ትገላለህ፡፡
📶 #አትስከር፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡
📶 #ዓለምን አትመልከት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ

📶 #በአባቶች አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡
📶 #እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡
📶 #በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድትገባለህ
📶 #ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡
📶 #ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ፡፡
📶 #አትዘሙት፦ እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል፡፡

📶 #ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይትነሣለህ
📶 #ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡፡

19/06/2025
19/06/2025

🙏🙏🙏🙏

14/11/2024
22/09/2023

የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ ሀገራዊ ክብርን ማጎናፀፍ፤ ሀገራዊ ክብርን በማጎናፀፍ ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር !

የብልፅግና ፓርቲ የውጭ ግኑኝነት ዋና ዓላማ ሀገራዊ ክብርን ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት ነው ።

ፓርቲያችን የውጭ ጉዳይን ከሀገር ውስጥ ጉዳይ የተነጠለ አድርጎ አይመለከትም። ይልቁንም የሀገር ውስጥ ጉዳያችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ነፀብራቅ ሆኖ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ያልዘነጋ ነው።
የውጭ ግንኙነታችንም የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ግንባታን የሚያረጋግጥ፤ የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ ሀገራዊ ክብርን የሚያጎናጽፍ፤ ሀገራዊ ክብርን በማጎናጸፍ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ይሆናል።

ሀገራዊ ክብር የሌለው ሀገር ሀገራዊ ጥቅሙን ሊያስጠብቅ እንደማይችል ፓርቲያችን በጥብቅ ይገነዘባል።

በመሆኑም የኢትዮጵያን ታሪክ እና አንድነት ፣ እንዲሁም የዜጎቿን ክብርና ተስፋዋን የሚያንፀባርቅ የጋራ ስምምነት ያለው ሀገራዊ ክብርን እና ሀገራዊ ጥቅማችንን የሚያስጠብቅ የተቀናጀና የተማከለ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና ትግበራን እውን ያደርጋል።
ሀገራዊ ክብራችንን ለማረጋገጥ እና ጥቅሞቻችንን ለማስከበር፣ አስቀድሞ ግንኙነትን በማደስና በማጠናከር ላይ ያተኮሩ ስራዎችን መስራት ላይ ትኩረት በማድረግ በግንኙነት ብልሽት ምክንያት የምናጣቸውን ሀገራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስከበር አመች ሁኔታ ይፈጥራል።

በውጭ ግንኙነት መስክ ሀገራችን መልካም የሚባል ውጤት ያስመዘገበች ሀገር ብትሆንም የውጭ ግንኙነታችን ከጉድለት እና ከግድፈት የፀዳ አይደለም። ስለዚህ ግድፈቶቹን እና ጉድለቶችን መለየት፣ ማስተካከል እና መሙላት ፤ እንዲሁም የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል የፓርቲያችን የውጭ ግንኙነት መሰረቶች ናቸው።

የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም (2014) ገፅ 41

እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ‼️በፈጣሪ ቸርነት 2015ን አልፈን ወደ አዲሱ ዘመን ደርሰናል። ኢትዮጵያ በውጣ ውረድ ውስጥ እያሸነፈች ተጉዛለች። ጽኑ መርሕ፣ ብርቱ ሕዝብና የማይሸነ...
11/09/2023

እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ‼️

በፈጣሪ ቸርነት 2015ን አልፈን ወደ አዲሱ ዘመን ደርሰናል። ኢትዮጵያ በውጣ ውረድ ውስጥ እያሸነፈች ተጉዛለች።

ጽኑ መርሕ፣ ብርቱ ሕዝብና የማይሸነፍ አምላክ ስላለን እዚህ ደርሰናል።

ብዙ ነገሮችን አሳክተናል፤ አያሌ ፈተናዎችን በድል ተወጥተናል፤ እልፍ መሰናክሎች ቢደረደሩም ጠንካራ መሰረት ሆነውን አልፈዋል።

የተሳኩልን ሁሉ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ውጤቶች ናቸው።

የተፈተንባቸው ደግሞ በመለያየት የተነሣ የመጡ ናቸው። በቀጣዩ ዓመት ፈተናዎቻችን እጅግ ቀንሰው፤ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ከአልማዝ ጠንክሮ፤ የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት በጽኑ መሠረት ላይ እናጸናዋለን።

ልማትና ብልጽግናዋን ወደሚመጥናት ደረጃ እናሻግረዋለን።

አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ብልጽግና ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም

https://t.me/wektawi1mereja

ቀናነት ቀና ያለ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ ቅንነት በተንኮል ያልታጠፈ፣ በምቀኝነት ያልተቆለመመ፣ በራስወዳድነት ያልተንጋደደ ሃሳብና ምግባር ነው፡፡ የተንጋደደ ማንነት ቀጥ ያለ ሰውነትን አያስ...
15/08/2023

ቀናነት ቀና ያለ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ ቅንነት በተንኮል ያልታጠፈ፣ በምቀኝነት ያልተቆለመመ፣ በራስወዳድነት ያልተንጋደደ ሃሳብና ምግባር ነው፡፡ የተንጋደደ ማንነት ቀጥ ያለ ሰውነትን አያስገኝም፡፡ ገዳዳ አስተሳሰብ ሕይወትን ያንጋድዳል፡፡ አንዴ ከአስተሳሰብህ ከተጣመምክ በስራህ መቼም ቢሆን ቀጥም ቀናም አትልም፡፡ የጎበጠ ማንነት፣ አንገት የደፋ ሕሊና ቀጥ ብሎ መቆም አይችልም፡፡ በሌሎች የሚዘወር ጭንቅላት የራሱ መሪ የለውም፡፡ በትንሹ ተፈትኖ የወደቅ በትልቁ ሊታመን አይችልም፡፡ ሲያስብ የተሳሳተ ምግባሩም ሆነ ተግባሩ የተሳሳተ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው የዘራውን ያንኑ ነውና የሚያጭደው!

ታላቁ የጥበብ ሰው ሩሚ፡-

‹‹የመበላሸትን ወይም የመበከልን ተፈጥሮ ተረዳ፡፡ አንዴ ቁልፍህ ከተጣመመ ወይም ከታጠፈ መቼም ቢሆን ቁልፍህ አይከፍትም፡፡›› ይላል፡፡

እውነት ነው! ራስህን መረዳት ስትጀምር አካሄድህን ታጤናለህ፣ አስተሳሰብህን ትገመግማለህ፣ የምትከተለውን ትመረምራለህ፤ ከፊትህ ያለውን በደንብ ማየት ትጀምራለህ፡፡ መሪህን ትመነጥራለህ፣ ዓላማህን ቀስ ብለህ ትሾፈዋለህ፤ ግብህን ታልማለህ፡፡ መድረሻህን ገና መንገድ ሳትጀምር ወጪና ኪሳራውን ቀድመህ ታሰላዋለህ፡፡፡፡ እየተራመድክበት ያለው “የሕይወት መንገድ አዳላጭ ነው፤ ወይስ ወስዶ ወስዶ ከገደል አፋፍ የሚያደርስ ነው” የሚለውን ለማወቅ አንተነትህን፣ መንገድህንና ዓላማህን መረዳት ይጠበቅብሃል፡፡

የመንገድህን መበላሸት፣ የዓየርህን መበከል፣ የአካሄድህ ግራገብነትን የምትረዳው ራስህንና ዓለሙን ስትረዳ ነው፡፡ የመበላሸት ተፈጥሮን ማወቅ ራስን ከብልሽት ማዳን ነው፡፡ የመኪና መነፋነፍ የብልሽት ምልክት ነው፡፡ የአስተሳሰብ መዛነፍም ውድቀትን ጠቋሚ ነው፡፡ ከብልሽቱ ዓለም ለመውጣት አስተሳሰብን መጠገን ግድ ይላል፡፡ ሊሰምጥ ጫፍ የደረሰ ሰውነትን መታደግ ከምንም በላይ አኩሪና አርኪ ነው፡፡ በሃሳብ ባህር ቀዝፎ፤ በህይወት ውቅያኖስ ተንሳፎ፣ በቀና አስተሳሰቡ ታንኳ የሕይወት ወጀቡንና የኑሮ ሞገዱን የሚያልፍ እሱ በአስተሳሰቡ የጠነከረ፤ ከኑሮው ልምድ የቀሰመ ነው፡፡

ከራሱ ጋር የመነጋገር ልምድን ያዳበረ ጠማማ አስተሳሰቡን ተረድቶ ወደቀናው አስተሳሰብ ይሸጋገራል፡፡ ከራስህ ጋር ለመወቃቀስ ከራስህ ጋር መግባባት ይኖርብሃል፡፡ ወቀሳን የሚቀበል ጭንቅላት ካልፈጠርክ የራስህ ከሳሽ ራስህ ትሆናል፡፡ ከወቀሳ ይልቅ ክስ ውጤቱ ጥሩ አይደለም፡፡ ክስ በመጨረሻ ፍርድ አለው፡፡ ወቀሳ ግን ለራስህ ይቅርታ እንድታደርግለት ነጭ ነጩን ነግሮ ምክር ይለግስሃል፡፡ ወቃሹም ተወቃሹም ራስ ለራስ ነው፡፡

የሚዛናዊነት፣ የአስተዋይነትና የብልህነት ቁልፍ ከታጠፈ ደግ ነገር ሁሉ ላይከፈት ተቆልፎ ይኖራል፡፡ ልብ ከተከረቸመ ቀናነትም ይጠረቀምበታል፡፡ አዕምሮ ከተዘጋ መልካም አስተሳሰብም የተዘጋ ይሆናል፡፡ ሕሊና በምክንያት መውደድና መጥላት ካልቻለ እንደጋሪ ፈረስ በማንም ደመነፍስ ይሾፈራል፡፡ ቁልፍ የሌለው ቤት ለሌባ እንደሚመች ሁሉ ቁልፍ አስተሳሰብ የጎደለውም የማንም ግብስብስ ሃሳብ መጫወጫ ይሆናል፡፡

የሕይወት ጋኑን የሚከፍት ቁልፍ ቅን አስተሳሰብና ምክንያታዊነት ብቻ ነው፡፡ ጋኑ አዕምሮ ነው፤ ቁልፉም አስተሳሰብን ይወክላል፡፡ ብዙ ተመሳስለው የሚሠሩ ቁልፎች ወይም ሃሳቦች አሉ፡፡ የቁልፉን ጋን የሚከፍተው ግን አንዱ ቁልፍ ብቻ ነው፡፡ ያ ቁልፍ የሕይወትህን መስመር፣ የአንተነትህን ጎዳና በርግዶ የሚከፍት ነው፡፡ አዎ ቁልፉ ስሪቱ ከአመለካከትህ ነው፡፡ ጥሬ ዕቃው የበሰለ ሃሳብህ ነው፡፡ በቀላሉ በማንም የማይከፈት ቁልፍ ለማድረግ ግን ማስተር ቁልፍ ያስፈልግሃል፡፡ ስትፈልግ የምትከረችመው፤ ሲያሻህ የምትበረግደው፡፡

Address

Addis Ababa
512

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hailu Buge Atumo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hailu Buge Atumo:

Share