25/04/2023
"ሀሉም በጊዜው ይሆናል"!
✅ ያለ ሰዓቱ አይነጋም!"
✅ ጨርሶ አይጨልምም።
👉 ፀሐይ ስትጠልቅ፣ ጨረቃና ከዋክብት ይወጣሉ።
👉 ዘጠኝ በሮች ሲዘጉ አንዱ ይከፈታል።
👉 ዘጠኝ ወዳጆች ሲሄዱ አንዱ ይተርፋል።
👉 ፀሐይ ባትጠልቅ ጨረቃ አትታይም። ፈተና ካልመጣምየማናውቃቸው ሰዎች አሉ።
👉 ፈተናው የሚሰጠን የመጨረሻ ውጤት የቅርብ ያልነው ሩቅ፣ የሩቅ ያልነው የቅርብ መሆኑን ነው።
👉 ፀሐይ እንደምትወጣ እርግጠኞች ነን።
👉 ጨረቃና ከዋክብት ለመውጣታቸው ግን እርግጠኛ አይደለንም።
👉 ጨረቃ የማትወለድበት፣ ከዋክብት የሚሰወሩበት ጊዜ አለ።
👉 የምታስተማምነዋ ፀሐይ ስትጠልቅ ያልጠበቅናቸው ጨረቃና ከዋክብት ይወጣሉ።
👉 የማታ ብርሃኖች ዙሪያውን በደንብ ባያሳዩንም ለእግራችን መርገጫ ያሳዩናል።
👉 ሰማዩን በውበት ይገልጡልናል። የብርሃንን ዋጋ እንድናስብና እንድንሰስት ያደርጉናል።
👉 እንደ ፀሐይ እርግጠኛ የሆንባቸው ሊጠልቁ ይችላሉ።
👉 ያልጠበቅናቸው ደግሞ ብቅ ይላሉ። ጨርሶ አይጨልምምና።
👉 “ፀሐይ ስለ መጥለቋ ከተመረርህ ከዋክብትም ይሰወሩብሃል” ይባላል።
👉 ቢወጡም አታያቸውም ማለት ነው።
👉 ምሬት ዓይንን ያጨልማልና።
✅ #አዎ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።
👉 አሁን ለመተኛት ገብተን ወዲያው ቢነጋ መልካም አይደለም።
✅ #ያለ ሰዓቱ ከነጋ፡-
1️⃣ "አእምሮአችን አይታደስም፡-
👉 አእምሮ የሚታደሰው የዋልንበትን አሳብ ፍጹም ትተን ስናርፍ ነው።
👉 በቂ ዕረፍት ስናገኝ ለቀጣዩ ቀን መማርና መሥራት እንችላለን።
👉 በሕይወት ውስጥ የሚገጥመን የፈተና ሰዓትም ራሳችንንና ዙሪያችንን እንድናይ ስለሚረዱን ያበስሉናል።
✅ እኔ ማን ነኝ?
👉 የምኖረው ከእነማን ጋር ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ የምንችለው በመከራ ሰዓት ነው።
👉 የፈተና ቀኖች የጠለለ አሳብን፣ የተጣራ ወዳጅን ያስቀሩልናል።
👉 ለቀጣዩ ዘመንም በቀላሉ የማይበገር አእምሮን ያጎናጽፉናል።
👉 ያለ ሰዓቱ ካልነጋ አንበስልም።
👉 እኛ የሚያስጨንቀን መከራው ነው፣ ጌታ ግን ትምህርቱ እንዳያልፈን ያስባል።
👉 ሕጻን ልጅ ስለ መድኃኒቱ ምሬት ያለቅሳል፣ ወላጆች ግን ስለመዳኑ ይጨክናሉ።
👉 ሩኅሩኁ ጌታ እስክንማር ይጨክናል።
2️⃣ "ከድካም አንላቀቅም፡-
👉 ያለ ሰዓቱ ከነጋ አሁን የተለየነው ግርግር መልሶ ይመጣል።
👉 አሁን የተውነውን ሥራ እንቀጥላለን።
👉 ከድካም ስለማንበረታ በቀጣዩ ቀን እንደክማለን፣ እንወድቃለን፣ በሥራችንም ውጤታማ አንሆንም።
👉 የቀጣዩን ቀን ትግል ለመቋቋም በሰዓቱ መንጋት አለበት።
👉 እግዚአብሔር ከግርግሩ ለይቶ፣ ሱስ ከሆኑብን የጊዜ ገዳዮች አውጥቶ የሚያሳርፈን በጨለማ ቀኖች ነው።
👉 በሰዓቱ ሲነጋ በርትተን ለቀጣዩ ዘመን ኃይል ይዘን እንቆማለን።
👉 በሰዓቱ ይንጋ፣ በትግሎቻችን ሁሉ ጌታ ትዕግሥት ይስጠን።
✅ የማይነጋ ሌሊት የለም።
✅ ማታ ጠዋት ይሆናል።
✅ ማታ የተለየን ጠዋት ይመጣል።
👉 ጠዋት ሲመጣ ግን በሰዓቱ ነግቷልና አእምሮአችን ታድሶ፣ አቅማችን በርትቶ እንቀበለዋለን።
#ፈጣሪ ጸጋውን ያብዛልን!
#ሀገራችንና ህዝቦቿን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን