Debr werk

Debr werk Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Debr werk, Baby & children's clothing store, Addis Ababa.

16/09/2025
03/09/2024

በጎንደር ከተማ ሰው የሚያግቱ እና በግፍ የሚገድሉ ወንጀለኞችን በመቆጣጠር የሕግ የበላይነትን ለማስፈን እየተሠራ መኾኑ ተገለጸ።

👉በእገታ፣ በግድያ እና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 49 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

ጎንደር ከተማ እና አካባቢው ከሰሞኑ ሕጻናት እና ሴቶችን ሳይቀር ማገት እና ገንዘብ መጠየቅ ብሎም የጭካኔ ግድያ የመፈጸም ወንጀሎች ይፋ እየወጡ ነው። ይህንን በተመለከተም የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት መግለጫ አውጥቷል። የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል።

ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ!

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በከተማችንና አካባቢው የተለያዩ ወንጀሎች መከሰታቸውና የብዙ ወገኖቻችን ሰላምና ደህንነት የሚያውክ ድርጊት እየተፈፀመ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወገኖቻችንን ያሳዘነና ልብ የሰበረ መሆኑ ይታዎቃል። በተለየም ደግሞ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ በሴቶች፣ በህፃናት እና በአረጋውያን ላይ ያነጣጠረ አፈና፣ እገታ እና ግድያ ሲፈጸም ቆይቷል።

የከተማችን ሕዝብ በተለያዩ ጊዚያት የችግሩን መንስኤ በውል በመለየት በጥፋተኞች ላይ የሕግ የበላይነትን እንድናስከብር የገለጸልንን ሐሳብ መነሻ በማድረግና ተጨማሪ ሥራዎችን በመሥራት በእገታ፣ በግድያና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 49 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውለናል ።

ነሐሴ 27/16 ዓ.ም በከተማችን በተፈጠረው ችግር ምክንያት ስለተጎዱ ወገኖቻችን ጉዳዩን አጣርተን የምንወስደውን ሕጋዊ እርምጃ ውጤቱን ለሕዝባችን የምናሳውቅ ይሆናል ።

ሌሎች ቀሪ ተጠርጣሪዎችን ለመቆጣጠር ሥራ እየሠራን ባለንበት ወቅት የከተችንን ሰላም እና ደህንነት የማይሹ ኃይሎች የግል ጥቅማቸውን ለማጋበስ ሲሉ ከጎንደር እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም የእናትና ልጅ ግድያ ተፈፅሟል። ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም ከእናቷ ጡት ነጥቀው የሁለት ዓመት ህፃን በማገት 300 ሺህ ብር ከተቀበሉ በኋላ ገድለው ከወላጆቿ ግቢ ጥለዋታል። የእናቷን ጡት ሳትጠግብ በጠዋቱ ሕይወቷን በተነጠቀችው ህፃን ልጃችን፣ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም በዚሁ አረመኔና ጨካኝ ቡድን ሕይወታቸውን ባጡ የእናትና ልጅ ሕልፈተ ሕይወትና ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም በተፈጠረው ችግር ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የፀጥታ ምክር ቤቱ የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለተጎዱ ቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የከተማችን ሕዝብ መፅናናትን እንመኛለን።

የጋራ ፀጥታ ምክር ቤቱ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት በወንጀሉ የተሳተፉ አካላትን ለሕግ የማቅረብ እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።
ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና የከተማችንን ሰላም ለመጠበቅ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ ድምፅ አልባ መሣሪያ እና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ፣ በተደራጀም ይሁን በተናጠል በከተማችን ወንጀል መፈፀም ፍፁም ሕገ ወጥና የተወገዘ ተግባር ነው ።

የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የሰው ሃብት እና ንብረት ዘርፈው ለመክበር የቋመጡ ኃይሎች ከተማውን ለመዝረፍ የተሰለፋ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከመንግሥት ጎን በመቆም የምትወዷትን ከተማችሁን ከአጋችና ከዘራፊ ቡድን እንድትጠብቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debr werk posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share