Ethiopian in Saudi

Ethiopian in Saudi stay positive ✨️ 🙏 🙂
(1)

የኢትዮ ሳዑዲ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስጠበቅ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ መጠናከር አለበት - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲ...
18/05/2026

የኢትዮ ሳዑዲ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስጠበቅ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ መጠናከር አለበት - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያን የጋራ ተጠቃሚነት ለማስጠበቅ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ይበልጥ መጠናከር አለበት አሉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሳኡዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ ኤልኬሬጅ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ የጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ መክረዋል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያና ሳዑዲ የረጅም ጊዜ ግንኙነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር አላቸው።

የሀገራቱን የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ደህንነት መጠበቅ እና በህጋዊ መንገድ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን አዳዲስ የስራ እድሎችን ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ዋሊድ ኤልኬሬጅ በበኩላቸው÷ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ እና ከህዝቦቿ ጋር ያላትን የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጠው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሕጋዊ መንገድ ወደ ሳዑዲ የሚገቡበትን ሁኔታ በመፍጠር ደህንነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን የተለዋወጡ ሲሆን፤ በተለይም በቀጣናው የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመፍታት ውይይት ብቸኛው አማራጭ ሊሆን እንደሚገባ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የ"ጅንኑ" ባለቤት ምስጢር የጋሽ ታምራት አዲስ ፈገግታ!  - ዶ/ር ሰላማዊት ሞገስ በሰይፉ ሾው! 💍🎭   | ​ተወዳጇ የጥርስ ሐኪም ዶ/ር ሰላማዊት ሞገስ በቅርቡ ትዳር መመስረቷንና አስደናቂ...
06/04/2026

የ"ጅንኑ" ባለቤት ምስጢር
የጋሽ ታምራት አዲስ ፈገግታ! - ዶ/ር ሰላማዊት ሞገስ በሰይፉ ሾው! 💍🎭

| ​ተወዳጇ የጥርስ ሐኪም ዶ/ር ሰላማዊት ሞገስ በቅርቡ ትዳር መመስረቷንና አስደናቂ የሙያ ጉዞዋን በሰይፉ በኢቢኤስ ፕሮግራም ላይ በዝርዝር አጋርታለች።

​💍 የ"ጅንኑ" ባለቤት ምስጢር፦
ሰላማዊት ከባለቤቷ ከአንዷለም ታረፈ ጋር ያላትን ትዳር "ጅንኑ" (ኩሩ) በሚል ቅጽል ስም እያቆላመጠች፣ የግል ሕይወታቸውን ሰላም ለመጠበቅ ሲሉ ፎቶ ደብቀው መቆየታቸውን ገልጻለች። የባለቤቷ ወንድነትና ኩራት እንደማረካትም በፈገግታ ተናግራለች።

​🎭 አንጋፋው ተዋናይ ጋሽ ታምራት ኃይሌ በደረሰባቸው የጥርስ ችግር ሳቢያ ፈገግታቸው ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም፣ ዶ/ር ሰላማዊትና ቡድኗ በነጻ ባደረጉላቸው ዘመናዊ የጥርስ ተከላ (Implant) አሁን ወጣት መስለውና በልበ ሙሉነት እየሳቁ ቀርበዋል።

​ "ኋይት ሃውስ" (White House)፦
በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነና በማይክሮስኮፕ የታገዘ ዘመናዊ የጥርስ ውበት ማዕከል መክፈቷን ገልጻለች። አሁን ላይ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ሳይቀር ሰዎች ታካሚ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ጀምረዋል።

​🙏 በየዓመቱ መቅዶንያ በመሄድ ለአረጋውያንና ለአእምሮ ሕሙማን የምታደርገው ነጻ የሕክምና አገልግሎት በሰይፉ ፋንታሁን ከፍተኛ አድናቆት ተችቶታል።

​"ፈገግታን መመለስ ታላቅ ደስታ ነው!" ለዶ/ር ሰላማዊትና ለባለቤቷ መልካም የትዳር ዘመን እንመኛለን! 🇪🇹❤

​ #ዶርሰላማዊት #ጋሽታምራት #ፈገግታ #ኋይትሃውስ

07/03/2026

ሳውዲአረቢያ የት ከተማ ነዉ አሁን ያላችሁት ??

Address

Addis Ababa

Telephone

+251939195532

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian in Saudi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share