KALID ISLAM

KALID ISLAM የጣት ምልክቱን በመንካት ገፄን በፍጥነት ተቀላቀሉ አመሰግናለዉ:: ��� ገፄን ስለተቀላቀሉ ከልብ አመሰግናለው።���

15/10/2023

አልሃምዱሊላህ

27/06/2023

ስታርድ እዝነት ይኑርህ❗️🥺

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ﴾

“አላህ ኢኽሳንን (ማሳመርን) በሁሉም ነገሮች ላይ ፅፏል። የገደላችሁ እንደሆነ አገዳደልን አሳምሩ። አንዳችሁ ባረደ ግዜ አስተራረዱን ያሳምር ማረጃውን ይሳል። የሚታረደውንም እንስሳም ያሳርፍ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1955

በሌላ ሀዲስ፦

﴿جاءَ رجلٌ إلى رسول الله ﷺ فقـال: يـا
رسـول الله إني لأذبحُ الشّـاةَ وأنـا أرحمها،
فقال ﷺ : والشاةُ إن رحِمتَها رحِمَك الله﴾

“አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ﷺ) በመምጣት እንዲህ አላቸው፦ ‘እኔ በጌን አርጄ ለሷም እዝነትን አድርጌ ነበር’ ረሱል (ﷺ) አሉት፦ ‘ለሷ ለበግህ እዝነትን እንዳደረክ አላህ ለአንተም ይዘንልህ።’”

📚 ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1081

✍️

❗️❗️
⊱⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━⊱⊰

ቆሎ ሻጩ ሁጃጅ😊 በሀብቱ የሚታወቀዉ ቱጃር ሰዉዬ በሀጅ ወቅት አረፋ ተራራ ላይ በአከባቢያቸዉ ዝቅተኛ የኖሮ ደረጃ ኖሮት ቆሎ እየሸጠ የሚተዳደርን ሰዉ ያገኘዋል።በጣም ተደነቀ። በሺዎች የሚቆጠ...
22/06/2023

ቆሎ ሻጩ ሁጃጅ😊

በሀብቱ የሚታወቀዉ ቱጃር ሰዉዬ በሀጅ ወቅት አረፋ ተራራ ላይ በአከባቢያቸዉ ዝቅተኛ የኖሮ ደረጃ ኖሮት ቆሎ እየሸጠ የሚተዳደርን ሰዉ ያገኘዋል።

በጣም ተደነቀ። በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ከስክሶ ለሀጅ የሄደዉ ባለሀብት የደሀዉን ሰዉዬ በቦታዉ መገኘት አስገርሞታል። ወደ'ሱ ጠጋ በማለት ሰላምታ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩም ሰላምታዉን መለሰለት።

"እንዴት እዚህ ልትገኝ ቻልክ?" በማለት ጥያቄ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩ ትንሽ ግራ ተጋባ። አረፋ ተራራ ላይ ለሌላ ጉዳይ እንዳልመጣሁ እያወቀ ሳለ እንዴት ጠየቀኝ ሲል አሰበ።

"ያዉ ... ለሐጅ ስነ ስርአት ነዋ አመጣጤ"

"ገባኝ ግን ያዉ... በየትኛዉ አቅምህ እዚህ ልትመጣ ቻልክ?.. ማለቴ ቆሎ ቸርቻሪ ሆነህ ሳለ ገንዘቡን ከየት አመጣሃዉ?" በማለት ጠየቀዉ።

ቆሎ ሻጩም በተረጋጋ መንፈስ መለሰለት።

"እኔ ቆሎ ሻጭ ብሆንም ጌታዬ ግን ቆሎ ሻጭ አይደለም! እዚህ ቦታ ላይ ሆኜ እሱን እንድለምነዉና እንድገዛዉ ስለፈለገ ጌታዬ እንድመጣ ፈቀደ። ይኼዉ ነዉ...."

ኢላሂ! ለኛም ሀጅን ወፍቀን! ሁሌም ካንተ ከጃይ ነንና! አንተ ምንም አይሳንህምና 🤲🤲

✍️ KALID ISLAM

⊱⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━

«… የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ…ይችን ልጅ [ካሚላን] እዚሁ መድረክ ላይ… አይቻት ነበር። … ከባድ ነው… ትልቅ አስተማሪ ሆና እንደምታልፍ ይሰማኛል። [አላህ ይቀበላትና] ለብዙዎቻችን… ራስን ለመለ...
25/04/2023

«… የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ…ይችን ልጅ [ካሚላን] እዚሁ መድረክ ላይ… አይቻት ነበር። … ከባድ ነው…
ትልቅ አስተማሪ ሆና እንደምታልፍ ይሰማኛል። [አላህ ይቀበላትና] ለብዙዎቻችን… ራስን ለመለወጥ፣ ራስን ለመቀየር፣ ራስን ሒሳብ ለማድረግና አላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል፣ ምሳሌ ሆና ታልፋለች ብዬ አምናለሁ።…» Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.

(ካሚላ ጠይብ (አላህ ይዘንላትና) ወደ አኼራ በሄደች በሳምንቱ ቄራ ሰላም መስጂድ ውስጥ በፒሲ(ፕራይቬት ኮሌጅ) ሙስሊም ጀምዓ በተዘጋጀላት የማስታወሻ ፕሮግራም ላይ ጀነት ላይ ማግኘት ስለናፈቀችው ሶሃቢይ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል (ረ.ዓ) ሙሐደራ ባቀረበ ወቅት የሰጠው የምስክርነት ቃል ነው።)

ሰበር ዜና_____________________ ||♥ እንኳን ለ1444ኛው የኢደል ፊጥር በዓል አደረሳችሁ፣አደረሰን በዛሬው ዕለት ማለትም ዕለተ ሐሙስ ምሽት ሚያዝያ 12 ቀን 2015፣ የሱዑዲት ...
20/04/2023

ሰበር ዜና
_____________________
||♥ እንኳን ለ1444ኛው የኢደል ፊጥር በዓል አደረሳችሁ፣አደረሰን

በዛሬው ዕለት ማለትም ዕለተ ሐሙስ ምሽት ሚያዝያ 12 ቀን 2015፣ የሱዑዲት ዐረቢያ የሥነ- ፈለክ ሳይንቲስቶች የዘመኑ ቴክኖሎጂ ባፈራው ቴሌስኮፕ በመታገዝ ባደረጉት ቅኝ፣ አዲሲቷ የሸዋል ወር ጨረቃ ለመታየት በመቻሏ፣

የሸዋል ወር የመጀመሪያው ዕለት የሚጀምረው፣ ማለትም ዒድ አል-ፊጥር የሚውለው በነገው ዕለት፣ ዕለተ ዐርብ ሚያዝያ 13 ቀን 2015 መሆኑ ተረጋግጧል ሲል "ሐረመይን ሸሪፈይን" የዜና ምንጭ ዘግቧል!!

ኢድ ሰላትን በተመለከተ ስቴድየሙ በእድሳት በቁፋሮ ላይ ስላለ የት ይደረግ የሚለውን መጅሊስ ስብሰባ ላይ ይገኛል። አብዬት አደባባይ የሚለው ድምፅ በአብዛኛው አብላጫ እየሆነ ነው።  በነገራችን...
20/04/2023

ኢድ ሰላትን በተመለከተ ስቴድየሙ በእድሳት በቁፋሮ ላይ ስላለ የት ይደረግ የሚለውን መጅሊስ ስብሰባ ላይ ይገኛል። አብዬት አደባባይ የሚለው ድምፅ በአብዛኛው አብላጫ እየሆነ ነው። በነገራችን ላይ ሁሉም ይህን መልክት ይስማ ምክንያቱም ያሁኑ ኢድ የባለስልጣን መግለጫ ምናምን የለውም ሁጥባ ከዛ ሰላት ስለሆነ በቶሎ ስለሚሰገድ እንደሌላው ቀን መስሏቹ እንዳትዘናጉ ለማሳሰብም ጭምር ነው።

18/04/2023
🛑 ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ውስጥ ላለ ብቻ አይደለም🤔🤔የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች...የዚች ለሊት ትሩፋት አይለፋችሁ።  በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ልትበ...
17/04/2023

🛑 ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ውስጥ ላለ ብቻ አይደለም🤔🤔

የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች...የዚች ለሊት ትሩፋት አይለፋችሁ። በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ልትበራቱ ይገባል።በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛትም አትዘንጉ። ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ላይ ላለ ብቻ አይደለም።

ብዙ ሰው መስጂድ ካልሄደ ይሄን ምንዳ የሚያገኙ አይመስለውም። ይህ ስህተት ነው! ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው በኢባዳ ላይ መሆናችን ነው። ለቻለ እና አቅሙ ላለው ሰው ግን የተወዳጁን ነብይ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና(ፈለግ) ለመከተል መስጂድ ላይ ብንሆን ይመረጣል፣ ይወደዳል። ካልቻልን ባለንበት ቦታ ስራ ላይ የሆነም በስራው ላይ እቤቱ የሆነም በቤቱ በኢባዳ ልንበረታ ይገባል!

አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን!🤲🤲

ሕፃኑ የሕፃን ልጅ አባት ኾኗል!እርስዎ በ14 ዓመት ዕድሜዎ ምን ላይ ነበሩ? መልሱን ለርስዎ ትቼ ወዲህ ግን የ14 ዓመት ታዳጊ ትዳር ውስጥ መኾኑን ልነግርዎ ነው።ዓሊ አል ካይሲ የተባለው የ...
17/04/2023

ሕፃኑ የሕፃን ልጅ አባት ኾኗል!
እርስዎ በ14 ዓመት ዕድሜዎ ምን ላይ ነበሩ? መልሱን ለርስዎ ትቼ ወዲህ ግን የ14 ዓመት ታዳጊ ትዳር ውስጥ መኾኑን ልነግርዎ ነው።
ዓሊ አል ካይሲ የተባለው የሳዑዲ ዜግነት ያለው ታዳጊ በ14 ዓመቱ ትዳር መሥርቶ አንድ ዓመት ከመንፈቅ ትዳሩን ካጣጣመ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት የ15 ዓመት ዕድሜ ካላት ሚስቱ ወንድ ልጅ ከነ ቃጭሉ አግኝቷል። ዓሊ አል ካይሲ ከሳዑዲ ቱዴይ ጋዜጣ ጋር በነበረው አጭር ቆይታ ሚስቱ የወለደችበት ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩ ሐኪሞች የልጅቷ አባት ሳይመጡ አገልግሎት አንሠጥም ብለው እንደነበር ተናግሯል። በጭንቀት ውስጥ የነበረው ትንሹ ባል "እኔ ባለቤቷ ነኝ! ኃላፊነቱን እወስዳለሁ!" ቢልም ሐኪሞቹ እሱ ራሱን ወላጆቹን እንዲያመጣ(እንዲጠራ) አድርገውታል።
ይኽም አልፎ አሁን ዓሊ ባለትዳር፣የወንድ ልጅ አባት እና ቤተሰብ አስተዳዳሪ ነው። በነገራችን ላይ ዓሊ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነው::

የሻም መጨረሻ»ሻም አላህ በቁርኣኑ «ዞርያውን የባረክነው» ያለው አገር ሲሆን የዓለም መጨረሻ ክስተቶች ሁሉ የሚፈፀምበት ቦታ ነው።ሻም ማለት በአሁኑ አከፋፈል ሶርያን፥ ፍልስጤምን፥ ጆርዳንን፥...
15/04/2023

የሻም መጨረሻ»

ሻም አላህ በቁርኣኑ «ዞርያውን የባረክነው» ያለው አገር ሲሆን የዓለም መጨረሻ ክስተቶች ሁሉ የሚፈፀምበት ቦታ ነው።

ሻም ማለት በአሁኑ አከፋፈል ሶርያን፥ ፍልስጤምን፥ ጆርዳንን፥ ሊባኖስንና ከፊል ኢራቅን ያጠቃለለ ግዛት ነው።

ነቢዩ (ዐሰወ) በተለያዩ ሐዲሳቸው በሻም ስለሚከሰቱ ጉዳዮች የተረኩ ሲሆን ከእነሱ መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ናቸው፦

♦ የወደፊት የሙስሊሞች መናገሻ ይሆናል።
(አን-ነሳዒ 3561)

♦ መህዲ ኢስላማዊ ኸሊፌት ይመሰርታል።
(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63)

♦ ደጃል ይነሳበታል። ከየሁዶችም የተወሰኑ ይከተሉታል።
(ቲርሚዚ፥ 2244)

♦ ዒሳ (ዐሰ) ሻም ደማስቆ አቅራቢያ በመውረድ ደጃልን ይገድለዋል።
(ሙስሊም፥ 2937)

♦ ሙስሊሞች የሁዶችን ያጠፉበታል።
(ቡኻሪ፥ 2926)

♦ የመጨረሻዎቹ ሙስሊሞች ይኖሩበታል።
(ቲርሚዚ፡ 2183)

♦ አላህ ከሻም የምትነሳ ነፋስ በመላክ የመጨረሻዎቹ ዘመን ሙስሊሞች በሙሉ እንዲሞቱ ያደርጋል።
(ሙስሊም፥ 2940)

♦ አላህ የቂያማህ ቀንን ፍርድ ይሰጥበታል።
(ተፍሲር አልቁርጡቢ 17/31)

የሰላትን ነገር አደራ ረሱል (ሰ.አ.ወ)
04/04/2023

የሰላትን ነገር አደራ ረሱል (ሰ.አ.ወ)

Address

Meskel Square
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KALID ISLAM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category