New generation

New generation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from New generation, Baby & children's clothing store, Ethiopian, Addis Ababa.

09/01/2026
08/01/2026
ካሳና ምትክ የተወሰደበትን የግለሰብ ይዞታ ቅርስ  ፈረሰ በማለት የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ  ነው ሲል የየካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር አስታወቀ!!በአዲስ አበባ ከተማ የካ ከፍ...
25/11/2025

ካሳና ምትክ የተወሰደበትን የግለሰብ ይዞታ ቅርስ ፈረሰ በማለት የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲል የየካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር አስታወቀ!!

በአዲስ አበባ ከተማ የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር በአዋሬ አካባቢ በ2ኛ ዙር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ "በቅርስነት የተመዘገበ ይዞታ በመንግስት ኃይል ፈረሰ" የሚል መሰረተ ቢስና አሳሳች መረጃ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ይገኛል።

በሀለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት አዋሬ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ውስጥ ያለው በወራሽ በነ ኡመር ማህመድ የተመዘገበው ይዞታ የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 79/2014 መሰረት ተገቢውን ካሳ እና ምትክ አንዲያገኙ በካርታ ቁጥር የካ/172375/04 በቀን 1/6/2004 በወራሾች እነ ኡመር መሀመድ ስም የካሳ ክፍያ 2,029,854.67 / ሁለት ሚሊዮን ሃያ ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ አራት ብር ከስልሳ ሰባት ሳንቲም/ በአካውንታቸው ገቢ ተደርጎ የወሰዱ ሲሆን በተጨማሪም ምትክ ቦታ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እንደተመደበላቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በኩል በደብዳቤ ቁጥር አ.አ/መ/ል/አስ/ቢ/2.3/25907/17 በቀን 20/09/2017 ስለተገለፀ ማህደራቸው ወደ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተልኮላቸው ቦታ ተረክበዋል፡፡

በተጨማሪም በቤት ቁጥር 116/ሐ የመንግስት ቤት የሆነው ውስጥ ነዋሪ የነበሩት እነ አለማየሁ ተሾመ ተስፋዬ የጋራ መኖሪያ ቤት ተመድቦላቸው አንዲረከቡ ተደረጓል ።

በተጨማሪም ቤቱ የቅርስ ቤት መስፈርት የማያሟላ መሆኑ የኢትየጵያ ቅርስ ባለስልጣን በቁጥር 01/9-14-014 በተጻፈ ደብዳቤ ገልጾልናል፡፡

ቤቱ የግለሰብ እንጂ ከመስጂዱ ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ እያሳወቅን፣ መስጅዱ በልማቱ ያልፈረሰ ሲሆን አሁንም ይዞታው እንደተከበረ መሆኑና በዚሁ ቦታ እንደሚገኝና መንፈሳዊና መደበኛ አገልግሎቱን እየሰጠ አንደሚገኝ አንዲሁም ፈረሰ የተባለው ይዞታ እና መስጂዱ ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው እንደሆነ ልናሳውቅ አንደወዳለን።

ከበቂ ጊዜ መስጠት ጋር ተያይዞ ካዛችስ ከተነሳበት ጀምሮ እንዲያፈርሱ ተነግሮቸዉ ነገ ዛሬ እያሉ የቆዩ ሲሆን ባለቤቶቹ ሲወጡ መብት የሌላቸዉ ሰዎች በህወጥ መንገድ በመያዛቸዉ ና ለመልቀቅ ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ በግረሀይል ፈርሷል።

በተጨማሪም ዜጎች ከመሰረተ ቢስ የሀሰት ወሬዎች እንዲጠበቁ እና መረጃዎችን ከሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ብቻ እንዲያገኙ ጥሪ እያቀረብን።

እንደዚህ ያሉ መሰል የተሳሳቱ መረጃዎች በማሰራጨት ህብረተሰቡን የሚያውኩ አካላት ከድርጊታቸው አንዲቆጠቡ እና ይህ ሳይሆን ሲቀር ተግቢውን የህግ ተጠያቂነት ለማስፈን እንደሚሰራ የወረዳ 06 አስተዳደር አስታውቋል፡፡

  newsሰላም የማይወዱ አካላት አሁን ደግሞ በሀይማኖትን አጀንዳ በማድረግ ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ነው። ታሪካዊ የሆነው የሀጂ ወሌ ሙሐመድ መስጂድ ፈረሰ እያሉ የሚያሰራጩት ዘገባ ከእውነት ...
25/11/2025

news

ሰላም የማይወዱ አካላት አሁን ደግሞ በሀይማኖትን አጀንዳ በማድረግ ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ነው።

ታሪካዊ የሆነው የሀጂ ወሌ ሙሐመድ መስጂድ ፈረሰ እያሉ የሚያሰራጩት ዘገባ ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ መረጃ ነው። መስጂዱ አሁን ላይ መደበኛ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

Address

Ethiopian
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New generation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share