08/09/2025
ውድ ተመራቂዎች፣
ዛሬ የምርቃታችሁ ቀን ብቻ አይደለም።
ህልሞቻችሁ በትዕግስት፣ ትጋታችሁ በድፍረት ፤ ያሰቡበት ሊደረስ እንደሚቻል ማስረጃ የምትሆናችሁ ውድ እና ልዩ ቀን ናት ።
በሄዋን ፋሽን ሁሌም የምናምነው ፋሽን ልብስ መስፋት ፣ ጸጉር መተኮስ ፣ ወይም በጥፍር መሞረድ ፤ ብቻ አይደለም - ፋሽን የማንነታችን ማሳያ ፣ የክብራችን መገለጫ ነው ፡፡ ደግሞም ለእኛ በእጃችን ህልማችንን የምንገንባበት መሳሪያችን ነው።
ወደዚህ ትምህርት ቤት የመጣችሁት ያልተነካ መክሊት ፣ ጉጉት እና ፍላጎት ይዛችሁ ነው ። አሁን፣ በችሎታ፣ በእውቀት ተመርቃችሁዋል ፤
መልእክቴ ቀላል ነው፡ እድሎችን ሌሎች እስኪሰጡዋችሁ አትጠብቁ
-የራሳችን እድል ፈጣሪዎች እኛ ነን ፟- ፍጠሩዋቸው ። ኢትዮጵያ የአንተን እና ያንቺን ሀሳብ እና የጥበብ ትፈልጋለች እጆች ትፈልጋለች ፣ የሃገራችንን ሰዎች ለማስዋብ እዚህ የተማራችሁትን ሁሉ ተጠቀሙ ።
እና ፈጽሞ አትርሱ : ፋሽን ኃይል ነው. በእያንዳንዱ ስፌት ፣ በእያንዳንዱ ንድፍ ፣እራሳችንን እንዴት እንደምንመለከት ብሎም ዓለም እኛን እንዴት እንደሚመለከተን የመቀየር ችሎታ አለው።
ውድ ተመራቂዎቼ፣ እንኳን ደስ አላችሁ ።
አሁን ትንሽ ቀልድ ፍቀዱልኝ፡ እስከ አሁን የተጠቀሟቸው መቀሶች፣ ማበጠሪያዎች እና መርፌዎች የእናንተ የመለማመጃ መሳሪያ ብቻ ነበሩ። ከዛሬ ጀምሮ ፣ ደግሞ እውነተኛ የለውጥ መሣሪያዎቻችሁ ይሆናሉ። በጥንቃቄ ተጠቀሙባቸው - ከአሁን በኋላ ተማሪዎች አይደላችሁም፣ የውበት - ወታደሮች ናችሁ።
እያንዳንዱ ቀሚስ እና ሱሪ ፣ እያንዳንዱ የፀጉር አሠራር፣ እያንዳንዱ ንድፍ፣ እያንዳንዱ የጥበብ ሥራ የምትፈጥሩት እናንተ የፋሽን - አምባሳደር ናችሁ ።
ስለዚህ ለእናንተ ያለኝ ምርቃቴ - ይህ ነው:
⦁ የምትወስዷቸው እርምጃዎች በሙሉ እንደ ተሰራ ጥፍር በልበ ሙሉነት ያንጸባርቁ።
⦁ በራስ መተማመናችሁ ሁል ጊዜ ከመጨማደድ የፀዱ ፟ የተተኮሰ ይሁን
⦁ መቀሳችሁ ጨርቅን እና ጸጉር ይቆርጡ እንጂ ህልሞቻችሁን በጭራሽ አይቁረጡ።
⦁ የስዕል ደብተሮቻችሁ ገፆች መቼም አይለቁ ፣ የመሳያ ቀለም አይደርቅባችሁ
⦁ ጉዞዋችሁ ልክ እንደ የሰርግ ልብስ በጥንቃቄ የተሰፋ፣ ይሁን። መድረሻችሁም እንደሰርግ መድረክ የተዋበ ይሁን
⦁ ስኬታችሁ እንደ ተተኮሶ ነፋስ ላይ እንደውጣ ረጅም ጸጉር ይውለብለብ
እንኳን ደስ አላችሁ ውድ ተመራቂዎቼ።
ኢትዮጵያ ትኮራባችሁዋለች ፤ እኔም እኮራባችሁዋለሁ።
አመሰግናለሁ።ሉሲዬ እህቴ ፣ሸዬ የኔ ውድ እህት ይግዬ ወንድምነት አመሰግናለሁ በጣም ሑልግዜ ድምቀቶቻችን ናችሁ ክበሩልኝ።