Dagnealemu

Dagnealemu My interest to use FB is the like to transmit Gospel of Jesus to all nation for to have eternal life for who believe in Jesus

20/08/2021

ስዖል ወይም ገሃነመ እሳት አለ ወይስ የለም?

አንዳንድ ሰዎች የሃይማኖትን ሰዎችን ጨምሮ ስለ ገሃነመ እሳት ያላቸው ግንዛቤ በጣም ያነሰ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ፈፅሞ ምንም የማያወቁና ለማወቅም ምንም ፍላጎትና መነሳሳት የሌላቸው ናቸው::
ሆኖም ገሃነመ እሳት እግዚአብሔር ለሰይጣንና ለወደቁ መለኣክት በኃጢአታቸው ምክንያት የተዘጋጀ የቅጣት ቦታ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል:: እንዲሁ ሰዎችም በኋላ ላይ ሰይጣንን በመስማት ከእግዚአብሔር ዓላማ ውጭ በመሆናቸው ምክንያት በዚሁ ለሰይጣን በተዘጋጀው ስፍራ በገሃነመ እሳት በኃጢአታቸው ምክንያት እንደሚጣሉና ለዘላለም በሲቃይ እንደሚኖሩ ቃሉ ይናገራል::
የትኛውም ሰው የተማረ ያልተማረ ትንሽ ትልቅ ሳይል ሁሉም ኃጢአተኛ ነው :: በራሱ ጻድቅ ሰው የለም :: ሁሉም የእግዚአብሔር ክብር ጎድሎታል::
ስለዚህም ሰው ወደ እግዚአብሔር ክብር ለመመለስ የሚችለው ; ለኃጢአቱ ይቅርታ የሚያገኘው ; ከሲዖል አሰቃቂ ጥፋት መዳን የሚችለው; ከእግዚአብሔር ጋር በክብር በመንግሥቱ ውስጥ ከእርሱ ጋር መኖር የሚችለው; የዘላለም ሕይወት ሊኖረው የሚችለው ከዘላለም ጥፋት መዳን የሚችለው
በሚከተለው የሃይማኖት ስም ወይም ሥርአት ሳይሆን ስለ ሁሉም ወይም ስለ ኃጢአተኞች ሰለ አንተ ሰለአንቺ ሰለ እኔ ሰለ ሁላችንም ኃጢአት በመስቀል ላይ በሞተልን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ወይም እንደገና ወይም ሁለተኛ በመወለድ ነው :: ይህን ቃሉ አስረግጦ ይነግረናል ይህን በናደርግ ግን የሚጠብቀን ሲዖልና ጥፋት ይጠብቀናል:: ወንድሜና እህቴ ሆይ አስብበት ዛሬ አቅልለህ ያየኸው ጉዳይ ነገ በሕይወትህ ላይ ሲሆን ስፍራ ባለመስጠትህ ምክንያት ቁጭትንና ጥፋትን ያመጣብሃልና ነገር ግን ትክረት ብትሰጠውና ነገሩን ብትመረምረው ከጥፋት የምታመልጥበትን መሠ ረታዊ ጉዳይ ታገኛለህና ተጠቃሚ ትሆናለህ:;
ከዚህ በታች የምታየው የእሳተ ገሞራ ደንጋይ ቀልጦ ፈሳሽ እሳት ነው::ስለሆነም ሲዖል ማለት ኃጢአተኞች ወይም በጌታ በማመን ዳግም ያልተወለዱ ወይም ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው ያልተቀበሉ ሰዎች ሁሉ የሚጣሉበት የእሳት ባህር ነው :: መ.ቅዱስ ትሉ የማይሞት እሳቱ የማይጠፋ እንደተባለ የሆነው ነው:: ስለዚህ የሲዖል መኖር እውነተኛ ነው የፍርዱ ሰዓት ደርሷልና ሳታመቻምች በጊዜ አምልጥ ብየ እመክርሃለው::
ይህንን ያልከህ ስለምወድህ እንጂ በከንቱ ጉዳይ ላጠምድህ እንዳልሆነ በትክክል ተረዳ::ለዚህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን አንብብ በግብዝነት አትመልከት በየትኛውም ምክንያት አትመካ ወደዚህ ምድር በራስህ ይዘኸው የመጣህ የእኔ የምትለው ምንም ነገር የለም ይዘህም የ ምትሄደው ነገር የለም:; በራስህ ማስተዋል አትደገፍ ቃሉን ስማ እርሱንም ተከተል እንጂ የጥፋትን መንገድ አትከተል:;
እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ማሰተዋልን ይስጥህ::
እግዚአብሔር ዘመንህን ይባርክ!!!

Gospel of Jesus were preached well in Sandafa town in July 3,2021" በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግ...
07/07/2021

Gospel of Jesus were preached well in Sandafa town in July 3,2021
" በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 1:16)

ከዛሬ ጀምሮ!!!"እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።"(መዝሙረ ዳዊት 29:11)
20/06/2021

ከዛሬ ጀምሮ!!!
"እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።"
(መዝሙረ ዳዊት 29:11)

06/06/2021

" ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:14-15)

" መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።"(ወደ ቲቶ 2:14)
03/06/2021

" መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።"
(ወደ ቲቶ 2:14)

17/05/2021
06/05/2021

" አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዓይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ። "
(መጽሐፈ መክብብ 11:9)

Address

Ethiopia Dese_Welo
Addis Alem

Telephone

+251911053216

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dagnealemu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share