Omo Union

Omo Union Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Omo Union, Arba Minch'.

ገበሬው  እርሻው ላይ እያለ፣ አንዲት ሚዳቋ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠች መጣችና ሳታስተውል እዚያው እርሻ ውስጥ ከነበረ የዛፍ ጉቶ ጋር ተጋጭታ አንገቷ ተሰብሮ ሞተች።..ገበሬውም ያለምንም ድካ...
19/07/2026

ገበሬው እርሻው ላይ እያለ፣ አንዲት ሚዳቋ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠች መጣችና ሳታስተውል እዚያው እርሻ ውስጥ ከነበረ የዛፍ ጉቶ ጋር ተጋጭታ አንገቷ ተሰብሮ ሞተች።..
ገበሬውም ያለምንም ድካም ያገኛትን ሚዳቋ ወስዶ አርዶ በላት። በዚህም በጣም ተደሰተ። ከዚያን ቀን ጀምሮ ገበሬው "ታዲያ በየቀኑ በፀሐይና በብርድ እየደከምኩ ለምን እታገላለሁ? በየቀኑ እዚህ ዛፍ ሥር ቁጭ ብዬ ሚዳቋ እስክትመጣልኝ መጠበቅ እችላለሁ እኮ!" ብሎ አሰበ።..
እርሻ ማረሱንና መኮትኮቱን ትቶ፣ በየቀኑ ከዛፉ ጉቶ አጠገብ ቁጭ ብሎ ሌላ ሚዳቋ እስክትመጣና እስክትጋጭለት መጠበቅ ጀመረ። ቀናት፣ ሳምንታትና ወራት አለፉ፤ ነገር ግን ሌላ ሚዳቋ ፈጽሞ አልመጣችም። በመጨረሻም እርሻው በሳርና በአረም ተሸፈነ፤ ምንም እህል ማምረት አልቻለም። ገበሬውም በሰነፍ አስተሳሰቡና በአቋራጭ ለመክበር በመመኘቱ ምክንያት ለረሃብና ለችግር ተዳረገ። በመጨረሻም እንዲህ አለ "ነፃ ምሳ ብሎ ነገር የለም።" There is no free lunch እንደማለት። ..
እዚህ ዓለም ላይ ነፃ ብሎ ነገር የለም፤ በነፃ አትታገዝም፤ በነፃ ብር አይገኝም፤ በነፃ ጥበብ የለም። ሁሉም ነገር ልፋት እና ጥረት ይፈልጋል።

https://OmoUnion.com

ስለ እንሰት ጥቅም እና ስለ ዋናው ተግዳሮቱ (የእንሰት አጠውልግ በሽታ) በጋሞኛ Wol'aa ስለሚባለዉ ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦ እንሰት ከሥሩ እስከ ቅጠሉ ጥቅም ላይ የሚውል ድን...
13/07/2026

ስለ እንሰት ጥቅም እና ስለ ዋናው ተግዳሮቱ (የእንሰት አጠውልግ በሽታ) በጋሞኛ Wol'aa ስለሚባለዉ ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

እንሰት ከሥሩ እስከ ቅጠሉ ጥቅም ላይ የሚውል ድንቅ ተክል ነው።
ሀ. (Food Security)
የረሃብ መከላከያ፡ እንሰት ድርቅን የመቋቋም ከፍተኛ አቅም አለው። ሌሎች ሰብሎች በዝናብ እጥረት ሲጠቁ እንሰት ግን ለረጅም ጊዜ ውሃ አቆይቶ ስለሚቆይ በችግር ጊዜ ደራሽ ነው።
የተለያዩ የምግብ አይነቶች፡ ከእንሰት የሚገኙት ቆጮ፣ ቡላ እና አሚቾ (የእንሰት ስር) ከፍተኛ የኃይል ምንጭ (Carbohydrates) ናቸው።
የመቆየት አቅም፡ የተፋቀ እንሰት (ቆጮ) ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሮ ለበርካታ ዓመታት ሳይበላሽ ሊቆይ ይችላል።
ለ.
የእንሰት ቅጠል እና የግንዱ ክፍል ለከብቶች በተለይም በደረቅ ወቅት ተመራጭ መኖ ነው። የእንሰት ዝቃጭ (ቆጮ ተጨምቆ የቀረው) ለከብቶች ማድለቢያነት ያገለግላል።
ሐ.
ቃጫ (Fiber)፦ ከእንሰት የሚወጣው ቃጫ ለገመድ፣ ለጆንያ እና ለምንጣፍ ስራ ከፍተኛ ጥራት ያለው ግብዓት ነው።
ቅጠል፦ ምግብ ለማብሰል ፣ ለማሸጊያነት፣ ለቤት ክዳን ።
መ.
እንሰት ዘላቂ ተክል በመሆኑ የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል። ከፍተኛ የውሃ ይዘት ስላለውም በአካባቢው ላይ እርጥበትን የመጠበቅ እና አፈርን የማበልጸግ ባህሪ አለው።

ሠ . #ለመድሀኒትነት
በተለይም የእንስት አሚቾ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉትና ለክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለዩ ዝርያዎች እንዳሉ ይታመናል::

2. (Enset Bacterial Wilt)
ይህ በሽታ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የእንሰት ህልውና እየተፈታተነ ያለ ትልቁ ጠላት ነው።
መንስኤው (Cause) በሽታው የሚመጣው Xanthomonas campestris pv. musacearum በሚባል ባክቴሪያ ነው።
እንዴት ይተላለፋል?

፦ በበሽታው የተጠቃን ተክል የነካ ቢላዋ፣ ማጭድ ወይም አካፋ ሳይታጠብ ጤናማውን ተክል ሲነካ።

፦ በሽታ ካለበት አካባቢ ችግኝ አምጥቶ መትከል።

#እንስሳት፦ የታመመ ተክል የበሉ ከብቶች ወደ ጤናማው ማሳ ሲገቡ ወይም በሰገራቸው አማካኝነት።

#ሰው፦ በጫማ ወይም በልብስ አማካኝነት ባክቴሪያውን በማጓጓዝ።

ምልክቶቹ

የውስጠኛው ወጣት ቅጠል በድንገት መጠውለግ እና ቢጫ መሆን።
ተክሉ ውሃ እንደጠማው ሆኖ ዝልፍልፍ ማለት።
ግንዱ ሲቆረጥ የሚወጣው ፈሳሽ ቢጫ እና ዝልግልግ መሆን።
በመጨረሻም ተክሉ ሙሉ በሙሉ ደርቆ ይሞታል።

3. ( )
ለበሽታው እስካሁን ፍጹም መድኃኒት አልተገኘለትም፤ ዋናው መፍትሔ መከላከል ብቻ ነው።
መሣሪያዎችን ማጽዳት (Disinfection)፦ ከማንኛውም ስራ በኋላ መሳሪያዎችን በእሳት ማቃጠል ወይም በፀረ-ተባይ/ አልኮል ማጠብ።
በሽታውን ለይቶ ማጥፋት (Eradication)፦ በሽታው የታየበትን ተክል ወዲያውኑ ነቅሎ በማሳው ዳርቻ ላይ ጉድጓድ ውስጥ ቀብሮ ማቃጠል።
የንክኪ ቁጥጥር፦ የታመመ ተክል ያለበት ማሳ ውስጥ እንስሳት እንዳይገቡ መከልከል።
ጤናማ ችግኝ መጠቀም፦ ምንጩ የማይታወቅ ወይም የታመመ ችግኝ በፍጹም አለመትከል።

ትምህርት ካገኛችሁበት ፔጁን Like Share & follow በማድረግ አዳዲስ መረጃዎችን ለራስዎም ሆነ ለሌሎች እንዲደርስ ያድርጉ!!! 🙏

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አብንን በመወከል ላለፉት 5 ዓመታት የተጓዙት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፖለቲካ ተሳትፎ (የፓርቲ አባልነትን ጨምሮ) ራሳቸውን ማግለላቸውን ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም...
09/07/2026

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አብንን በመወከል ላለፉት 5 ዓመታት የተጓዙት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፖለቲካ ተሳትፎ (የፓርቲ አባልነትን ጨምሮ) ራሳቸውን ማግለላቸውን ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ አደረጉ።
(መግለጫቸው እነኾ)
ላለፉት 5 አስቸጋሪና ፈታኝ ዓመታት (ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውድ ሕዝባችንን በመወከል ያደረግሁትን የፓርላማ ቆይታ ትናንት በይፋ አጠናቅቂያለሁ። ይህ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ፣ ወደዚህ የሕዝብ አገልጋይነት ያመጣኝንና ያለፍኩበትን የ10 ዓመታት የማኅበረሰብ አገልግሎት እና የትግል ጉዞዬን መለስ ብዬ የምመለከትበት አጋጣሚ ሆኖልኛል።
ወደ ፖለቲካ ሕይወት ከመግባቴ በፊት፣ በዩኒቨርሲቲ ከነበረኝ ማስተማርና ኃላፊነት ጎን ለጎን ለ2 ዓመታት በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ትኩረት እንዲያገኝ በአክቲቪዝም እና ሀገር በቀል የሲቪክ ማኅበረሰብ በመመስረት በግንባር ቀደምትነት መርቻለሁ። ባለፉት 8 ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፓርቲ ምስረታ እስከ ከፍተኛ አመራርነት፣ በተለይም ደግሞ ባለፉት 5 ዓመታት በፓርላማ አባልነት ድምፅ ለሌላቸው ወገኖቼ እውነተኛ ድምፅ መሆን በመቻሌ የተሰማኝ ክብርና ኩራት የላቀ ነው።
በነዚህ እጅግ አስቸጋሪ ዓመታት፣ በፈተና እና በጭንቅ ሰዓት ለህዝቤ የገባሁትን ቃል እንድጠብቅ፣ እንዳልናወጥ፣ በቅንነትና በድፍረት የሕዝቤን ችግር እና ስቃይ በታሪክ ፊት እንድመሰክር ፍርሃትን አርቆልኝ ማስተዋልንና ጽናትን ላደለኝ፤ እስከዚች ሰዓትም በሰላም ላደረሰኝ ለቸሩ አምላክ ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይድረሰው። ያለ እሱ መለኮታዊ ጥበቃና መሪነት፣ ያለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅርና እናታዊ ምልጃ ይህንን ከባድ የሕዝብ አደራ መወጣት ፈጽሞ አይቻልም ነበር።
የባሕር ዳር ከተማ መራጮቼን ጨምሮ፣ ላለፉት ዓመታት እያንዳንዱን የፓርላማ ውሎዬን እየተከታተላችሁ አስተያየት እና ምስጋና የቸራችሁኝ፣ በተለይም ደግሞ ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት ለ45 ቀናት በታሰርሁበት ወቅት በጸሎትና በሐሳብ ያገዛችሁኝ ውድ ወገኖቼ፣ በየአጋጣሚው የለገሳችሁኝ ፍቅር ጉልበት ሆኖኝ ዛሬ በኩራትና በነጻ ሕሊና የሕዝብ አገልግሎቴን እንድፈጽም አድርጎኛል። የሕዝብ አገልጋይ መሆን ምንኛ መታደል እና ታላቅ ክብር እንደሆነ በተግባር ያየሁበት አጋጣሚ ነው።
በምክር ቤቱ ቆይታዬ በሀሳብ ለደገፋችሁኝ፣ በሰለጠነ መንገድ አክብሮታችሁን ለገለጻችሁልኝ የተለያዩ ፓርቲዎች የምክር ቤት አባላት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮች፣ ለምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች፣ የምክር ቤቱን ውሎዎች በታማኝነት ለዘገባችሁ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ተቋማት፣ እንዲሁም ለቅርብ የትግል አጋሮቼ በሙሉ ያለኝ ምስጋና የላቀ ነው።
በትናንትናው የምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ «አብረን እንስራ» በማለት ላቀረቡልን ጥሪና ላሳዩን አክብሮት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከጉባዔው መጠናቀቅ በኋላ ጥያቄ ያቀረብን የተቃዋሚ የምክር ቤት አባላት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረን የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ላይም በ7ኛው ዙር ምርጫ በባሕር ዳር ከተማ ለመወዳደር ተመዝግቤ ቢሆን ኑሮ እጩ ላለማቅረብ ወስነው እንደነበር ገልጸውልኛል። በምክር ቤቱ ሳነሳቸው የነበሩ ሀሳቦች ጠቃሚ እንደነበሩ፣ በትኩረት እንደሚወስዷቸው እና በምክር ቤቱ ብቀጥል ፍላጎታቸው እንደነበር የገለጹልኝን ሀሳብም በበጎ ጎኑ እና በቅንነት ተመልክቼዋለሁ።
ይሁን እንጂ፣ ላለፉት 10 ዓመታት የሕዝብን አደራ ለመወጣት ካደረግሁት ከፍተኛ ጥረትና ድካም በኋላ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ውሳኔዬ በሙያዬ ሀገሬን ለማገልገልና ጎን ለጎን ደግሞ

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ስላስተማረበት ቋንቋ እና የተጠቀመባቸውን ሌሎች ቋንቋዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከተለው ማየት ይቻላል፡አራማይክ (Aramaic)፡ አብዛኞቹ የታሪክ አዋቂዎችና ሊቃው...
04/07/2026

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ስላስተማረበት ቋንቋ እና የተጠቀመባቸውን ሌሎች ቋንቋዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከተለው ማየት ይቻላል፡
አራማይክ (Aramaic)፡ አብዛኞቹ የታሪክ አዋቂዎችና ሊቃውንት እንደሚስማሙት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለት ተዕለት ኑሮውና ሕዝቡን በማስተማር ወቅት በብዛት የተናገረውና የተጠቀመው የአራማይክ ቋንቋን (በተለይም የገሊላ ቀበሌኛ) ነበር። ይህ ቋንቋ በወቅቱ በመካከለኛው ምስራቅ በስፋት ይነገር የነበረ የንግድና የሕዝብ ቋንቋ (lingua franca) ነበር። እንደ 'አባ' (አባት)፣ 'ታልታ ኩሚ' እና 'ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ' ያሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገቡት የኢየሱስ ቀጥተኛ ቃላት የአራማይክ ቋንቋ ናቸው።
ዕብራይስጥ (Hebrew)፡ ኢየሱስ በይፋዊ የሃይማኖት ሥርዓቶች ላይ ማለትም በምኩራብ (Synagogue) ውስጥ ብሉይ ኪዳንን ሲያነብና ሲተረጉም ዕብራይስጥን ይጠቀም ነበር። እንዲሁም ከፈሪሳውያንና ከሕግ አዋቂዎች ጋር በሚያደርጋቸው ክርክሮች ይህንን ቋንቋ ተጠቅሟል።
ግሪክኛ (Greek)፡ በወቅቱ የሮም ግዛት ተደማጭነት ያለው ቋንቋ ስለነበር፣ ኢየሱስ ከአይሁድ ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር (ለምሳሌ ከሮማዊው መቶ አለቃ ጋር) ሲነጋገር የግሪክኛ ቋንቋን ተጠቅሞ ሊሆን እንደሚችል ምሁራን ይስማማሉ።
ኢየሱስ የመጣበትን አላማ ዕወቁ ዮሐ 1 ፥ 4-5"በእርሱ ሕይወት ነበረች
ኢየሱስ የመጣበትን አላማ ዕወቁ ዮሐ 1 ፥ 4-5"በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም። ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣበትን አላማ አያውቅም ፥እርሱ የመጣው ...
ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ወይስ የአምላክ ልጅ?
ስለ ኢየሱስ እውነቱን ማወቅህ አስፈላጊ ነው። ለምን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተንና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ አለባቸው።” (ዮሐንስ 17:3) ስለ ይሖዋና ስለ ...
ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישו ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት (በግሪክ ቋንቋ ሲጻፍ Χριστός ፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው)፤ (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ...
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው · ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ የምትመሰክራቸው እውነቶች · በኒቅያ የተሰበሰቡት አባቶቻችን በአርዮስ የቀረበላቸውን የስህተት ትምህርት ፊት ለፊት በእግዚአብሔር ቃል ሲቃወሙት በሌላ በኩል ደግሞ ...
ቤተ ጎለጎታ ከቤተ ደብረሲና በስተ ሰሜን የሚገኝ የላሊበላ አለት ፍልፍል ቤተ ክርስቲያ ነው። ቤተ ጎልገጎታ አንድ ውጫዊ የግድግዳ ገጽታ ብቻ ሲኖረው ውስጡ ሶስት ታቦታትን ይዟል። ቤተ ጎለጎታ ውስጥ እየሱስ ቤትና የኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር በሚባሉ ...
ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? - የሕይወት እንጀራ
ኢየሱስ ሰብአዊ አካል ነበረው። ኢየሱስ ፍጹም ሰው እንደነበረ እንዴት ልናውቅ እንችላለን? በመጀመሪያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን ኢየሱስ ሰብአዊ አካል ነበረው። ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡1 አንብቡ።
በኢየሱስ ስም ተጠመቁ ማለት ምን ማለት ነው ??
1ኛ ዮሐ 5:6! ኢየሱስ በስጋዉ ወራት በምድሩ ቆይታዉ፤ በአይሁድ ጎኑን ስወጋ የወጣው ዉኃ እና ደም ነበር። ይህ ዉሃ በእግዚአብሔር አሠራር ከአዳም የተወረሰዉን የኃጢአት ሥር ልቆርጥ በምችል ብቃት ለስርዬታችን ሆነ።
በግሪክ ክርስቶስ፣ በግእዝ ቅቡዕ ማለት ነው። ቅቡዕ ማለትም የተቀባ

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል‼የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የክልል ምክር ቤቶች ውጤት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ የክልል ምክ...
21/06/2026

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል‼

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የክልል ምክር ቤቶች ውጤት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ውጤት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

📌ኦሮሚያ ክልል፦ ከጠቅላላው 528 ወንበሮች ውስጥ **ብልጽግና ፓርቲ 523 ወንበሮችን** በማሸነፍ አብላጫነቱን ይዟል። ቀሪዎቹን ወንበሮች የግል ተወዳዳሪዎች (4) እና ኢዜማ (1) አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 97%)

📌አማራ ክልል፦ከጠቅላላው 277 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 257 ወንበሮችን አሸንፏል። ቀሪዎቹ ወንበሮች ለአዴኃን (4)፣ ለኢዜማ (3) እና ለአብን (2) ደርሰዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 95%)

📌ሶማሌ ክልል፦ከጠቅላላው 252 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 214 ወንበሮችን ሲያሸንፍ፣ ኦብነግ 20 እንዲሁም ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ 13 ወንበሮችን አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 94%)

📌ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፦ ከጠቅላላው 171 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 144 ወንበሮችን አግኝቷል። ሰላም ለኢትዮጵያ 12 እንዲሁም ኢዜማ 10 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 97%)

📌ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፦ ከጠቅላላው 170 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 143 ወንበሮችን ሲወስድ፣ ኢዜማ 12 እንዲሁም ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ 7 ወንበሮችን አሸንፈዋል። *(የመራጮች ተሳትፎ፦ 96%)

📌ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፦ከጠቅላላው 165 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 143 ወንበሮችን አግኝቷል። ጉህዲን 16 እንዲሁም ቤህነን 5 ወንበሮችን ይዘዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 97%)

📌አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፦ከጠቅላላው 158 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 134 ወንበሮችን ሲያሸንፍ፣ ኢዜማ 8 እንዲሁም አንድ ኢትዮጵያ ፓርቲ 4 ወንበሮችን አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 96%)

📌አፋር ክልል፦ ከጠቅላላው 135 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 124 ወንበሮችን አሸንፏል። አኔግ 6 እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ 3 ወንበሮችን አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 94%)

📌ሐረሪ ክልል፦ከጠቅላላው 36 ወንበሮች ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ 32 ወንበሮችን ሲያሸንፍ፣ ነፃነትና እኩልነት (1) እና ሐዴድር (1) ወንበር አግኝተዋል። (የመራጮች ተሳትፎ፦ 99%)
ተጨማሪ መረጃዎች በፍጥነት እንድደርስዎ Omo Unionን like, share & follow አድርጉት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ዛሬ እሁድ ዕለት ይፋ ባደረገው የምርጫ ውጤት መሠረት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸንፏል።የብሔራዊ ም...
21/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እሁድ ዕለት ይፋ ባደረገው የምርጫ ውጤት መሠረት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸንፏል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳስታወቁት "ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውድድር ከተካሄደባቸው 486 መቀመጫዎች ውስጥ 438ቱን አሸንፏል"።

ሰኔ አንድ ቀን የተካሄደው ይኸው የፓርላማ ምርጫ፣ በትግራይ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎችን ጨምሮ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ሳይካሄድ ቢቀርም፣ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ግን በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት ተከናውኗል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የብልጽግና ፓርቲ ጋር ከ40 በላይ ፓርቲዎች የተወዳደሩ ቢሆንም፣ አብዛኛዎቹ የፋይናንስ እጥረት የነበረባቸው በመሆኑ ገዥው ፓርቲ በ64 የምርጫ ክልሎች ውስጥ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ለብቻው ተወዳድሯል። ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በተሻለ ከፍተኛ የዕጩዎች ውክልና የነበረው ኢዜማ 293 ዕጩዎችን ሲያቀርብ፣ ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ 461 ዕጩዎችን ለውድድር አቅርቦ ነበር።
"የብልጽግና ፓርቲ ድል ውድድር ከተካሄደባቸው መቀመጫዎች ውስጥ ወደ 90 በመቶ የሚጠጋውን ይሸፍናል" ሲል የምርጫ ቦርድ በመግለጫው አብራርቷል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማው) ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚሰይም በመሆኑ፣ ይህ አብላጫ የምርጫ ውጤት እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምሮ በስልጣን ላይ ላሉት አብይ አህመድ ሀገሪቱን ለተጨማሪ አምስት ዓመታት በቢሮ ሆነው እንዲመሩ ሰፊ ዕድል የሚሰጣቸው ይሆናል።
ይሁን እንጂ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ የተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው ሳይካሄድ መታገዱ፣ እስካሁን እልባት ያላገኙ የውስጥ ግጭቶች በሀገሪቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ እያሳደሩ ያለውን ከፍተኛ ጫና በጉልህ የሚያሳይ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሰበር ዜና‼️የአየር ኃይሉ ከባድ የአጸፋ እርምጃ ወስዷል ተባለ‼ ከትናንት በስቲያ አርብ በሱዳን በኩል ተነስተው በኢትዮ-ሱዳን የሸረሪና የድንበር መስመር ላይ ትንኮሳ የፈጸሙት ‘አርሚ 70’ ...
21/06/2026

ሰበር ዜና‼️
የአየር ኃይሉ ከባድ የአጸፋ እርምጃ ወስዷል ተባለ‼

ከትናንት በስቲያ አርብ በሱዳን በኩል ተነስተው በኢትዮ-ሱዳን የሸረሪና የድንበር መስመር ላይ ትንኮሳ የፈጸሙት ‘አርሚ 70’ የተባሉ የህወሓት ታጣቂዎች፣ ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ጥቃታቸው ከሽፎ ወደ ኋላ መመለሳቸው ተዘግቧል።

ከትንኮሳው በኋላ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በድንበር አካባቢ በሚገኝ ወታደራዊ ጣቢያ እና የጦር መሣሪያ ማከማቻ ላይ በወሰደው የአየር ጥቃት መጋዘኑን ማውደሙ ተገልጿል።ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።
v👇Like + Follow👇
Omo Unio

📍አስቸኳይ ሰበር - መረጃ -🔴​ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በሰላም ይጓዙ የነበሩ 5 የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ራያ ሞሆኒ መግቢያ ላይ በህወሓት ሰራዊት መታገቱ ተገለፀ! ​የሚያሳዝነው እና አ...
21/06/2026

📍አስቸኳይ ሰበር - መረጃ -🔴

​ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በሰላም ይጓዙ የነበሩ 5 የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ራያ ሞሆኒ መግቢያ ላይ በህወሓት ሰራዊት መታገቱ ተገለፀ!

​የሚያሳዝነው እና አሳሳቢው ነገር፣ የታጋቾቹ 96% የሚሆኑት ወጣቶች መሆናቸው ተገልጿል ። በትግራይ ክልል ከጦርነት በመሸሽ ወደ አዲስ አበባ የሚሸሸው የወጣቶች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ህወሃት በኬላዎች ላይ ያለው ቀጥጥር ከፍ በማድረግ የ ወጣቶችን አፈሳ ከጀመረ ሰንብቷል።

በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፀም የዓድዋ ገዢ ቡድን ግፍና ድርጊት ማንም ሊታገሰው አይገባም ንፁሃን ዜጎች እና ወጣቶች በሰላም የመንቀሳቀስ መብታቸው ሊከበር ይገባል! ድርጊቱን በፅኑ እናውግዛለን

👉 እውነት ይውጣ፣ ለወጣቶቹ ድምፅ እንሁን -ሁላችንም ሼር በማድረግ ድምፅ እንሁን! በማድረግ ለሁሉም አድርሱ!

✍️ Tigray Press




#ሼር

21/06/2026
ምድረ ገነት፥ምድረ ቀደምት፥የጥበብ ምድር፥የደጋጎች መኖሪያ፤የአረንጓዴ መገኛ፥የጀግኖች መፍለቂያ።Visit Gamo, Visit Arba Minch! http://omounion.com/ follow አድ...
13/06/2026

ምድረ ገነት፥
ምድረ ቀደምት፥
የጥበብ ምድር፥
የደጋጎች መኖሪያ፤
የአረንጓዴ መገኛ፥
የጀግኖች መፍለቂያ።
Visit Gamo, Visit Arba Minch! http://omounion.com/ follow አድርጉ!

Address

Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Omo Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share