30/08/2026
የእግዚአብሔር ቤት ከሌሎች ቤቶች የሚለየው በምንድነው? Camon
#1. የቃል ኪዳኑ ታቦት በውስጡ በመኖሩ
#ንጉሥ ሰለሞን እንዲህ አለ፦
2 ዜና 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ፤ እግዚአብሔርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአባቴ በዳዊት ፋንታ ተነሣሁ፥ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ተቀመጥሁ፥ ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ።
¹¹ ከእስራኤልም ልጆች ጋር ያደረገው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦት በዚያው ውስጥ አኖርሁ። #ስቀጥል...
#እግዚአብሔር ለንጉሡ በህልም ተገልጦ እንዲህ አለ፦
2 ዜና 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ።
¹⁶ አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።
ከመጽሐፉ ሁለቱን ምዕራፍ እስከ መጨረሻ አንብቡት ራሳችሁን ታገኛላችሁ።
#2. ዘወትር የሚቀደስ በመሆኑ፦
👉“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።” ዘጸአት 20፥8
#ይቀጥላል! ...