Kidist Yalewle ET

Kidist Yalewle ET Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kidist Yalewle ET, Men's clothes shop, Gondar.

ማነጻጸር አይቻልም- - -እርግጥ ነው በውትድርና ቤት ጥቅምን የተገነ፣መጠቀምን ያለመ አስተሳሰብና ዕምነት የለም።የውትድርና ቤት ለሌሎች በመኖር በነፍስ ክፍያ በሚደመደም ከራስ ግላዊ ፍላጎት ...
28/07/2023

ማነጻጸር አይቻልም- - -

እርግጥ ነው በውትድርና ቤት ጥቅምን የተገነ፣መጠቀምን ያለመ አስተሳሰብና ዕምነት የለም።

የውትድርና ቤት ለሌሎች በመኖር በነፍስ ክፍያ በሚደመደም ከራስ ግላዊ ፍላጎት የተቆራረጡ ቆራጦች መኖሪያ ነውና ከሌላው ጋር ለማናፃጸር ከበድ ቢል አይገርምም።

ክብር ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት!!

02/06/2023

ዳገትን ለመውጣት ፈተናዎች ያጋጥማሉ፤ ዳገቱ ግን ያበረታል፤ የበለጠ ያጠነክራል እንጂ ፈፅሞ ሊመልሰን አይችልም!

በላብ የተፈተነ፣ በደም የተገነባ፣ በህይወት መስዋዕትነትና በዓለት ላይ የቆመን የዓላማ ፅናት እዚያም እዚህም የሚታዩ የጊዜያዊነት የዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች አይበግሩትም ።

ህዝብ ሁሉን ያያል፤ ህዝብ ያመዛዝናል፤ ህዝብ ፍርድም ይሰጣል፡፡ ህዝብ በሁሉም ነገሮች ምላሽ አለመስጠቱ አለማወቁን፣ አለመቻሉን ወይም ደካማ መሆኑንም አያመለከትም ፤ ይልቁንም ታጋሽነቱን አርቆ አሳቢነቱን እና የነገ ብሩህ ተስፋውን በማሰብ የፅንፈኝነት እና የጎሰኝነት አጀንዳ አራማጆችን በዝምታ እየተመለከተ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የህዝቡ አላስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን አይቶ እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ መሆኑ ከአባቶቻችን ድንቅ ጥበቦች አንዱ የሆነው ስክነት ባለቤት መሆኑን ማረጋገጫ ነው።

እውነታው ለማንም ከእውነት ጎን ለቆመ ሁሉ ግልፅ ሆኖ ሳለ በህዝብ ላይ ለመፍረድ የምትሞክሩ አካላት ከድርጊታችሁ መታቀብ ብትችሉ ትርፉ ለእናንተው ነው፤ ይህንን አልፋችሁና በህዝበኝነት ካባ ተጀቡናችሁ ክልላችንን የብጥብጥ ቀጠና ለማድረግ በመሞከራችሁ ህግን ለማስከበር ሲባል የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

ሲዞሩ በመኖር ፅድቅ፤ ሲመኙ በመኖር ወርቅ አይገኝምና በማይጠቅምና ለወቅታዊ ሁኔታው በማይዋጅ መንገድ ተጉዛችሁ በህዝብ ደም ኪሳችሁን ለማድለብ ቀን ከሌሊት በሴራ ፖለቲካ የምትናውዙ ግለኞች ከቀን ህልማችሁ ነቅታችሁ ወደ ቀልባችሁ ብትመለሱ መልካም ይሆናል፡፡

ለፖለቲካዊ ሴራችሁ ማስፈፀሚያነት ልዩ ልዩ የጽንፈኝነት አጀንዳዎችን በመምዘዝ መንግስትና ህዝብ ሆድና ጀርባ እንዲሆን እንደምትሰሩ ህዝባችን በሚገባ ይረዳል።

በመሆኑም አጀንዳ ሰጭም ጥፋት አድራሽና ነጠላ ዘቅዝቆ አልቃሽ በመሆን ህዝባችንን ለእልቂት ለመዳረግ የሚካሄደውን የጥፋት ሴራ ለማክሸፍ አስፈላጊውና ህጋዊ እርምጃ ተወስዶ የህዝባችን ሰላም መረጋገጡ ይቀጥላል፡፡
•~•~•

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/

02/06/2023
ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት የተላለፈ መልዕክት***በምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው ደብረ ኤልያስ ወረዳ ለኑሮ ምቹ የአየሩ ፀባይ ተስማሚ ምርታማ የሰጡትን አብቃይ ብዙ ማዕድናት...
01/06/2023

ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት የተላለፈ መልዕክት
***
በምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው ደብረ ኤልያስ ወረዳ ለኑሮ ምቹ የአየሩ ፀባይ ተስማሚ ምርታማ የሰጡትን አብቃይ ብዙ ማዕድናት ያሉበት ሰርቶ መለወጥ ለሚፈልግ ተስማሚ ወረዳ ናት።

በወረዳው የሚኖረው የህ/ሰብ ሠላም ወዳድ ሰው አክባሪ እና አምራች ዜጋ ነው ። ሆኖም ግን በደጎልማ ቀበሌ የሚገኘው የስላሴ አንድነት ገዳም ውስጥ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ እና ገዳሙን መሸሸጊያ እያደረጉ የሀይማኖት አባቶችን ፣ታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎችን የመንግስት አመራሮችን እየገደሉ በህግ ላለመጠየቅ የሚጥሩ የታጠቁ ሰዎች የሚኖሩበት ገዳም ሆኗል ።

የገዳሙን አባቶችም ትክክል አይደላችሁም የወንጀለኛ መደበቂያ እሆናለሁ ነው ለገዳሙም ጥሩ አይደለም በማለት በሀይማኖት አባቶች ፣በሀገር ሽማግሌዎች ፣ በመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እና በዞን ሀገረ ስብከት የሀይማኖት አባቶች ቢጠየቁም ከማስተካከል ይልቅ ይባስ ብለው በገዳሙ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና እየጡ ምሽግ በመስራት መሳሪያ በመግዛት እንዲሁም ከመንግስት ያፈነገጡ ሰዎችን በማሰባሰብ አጠናክረው በመቀጠላቸው ችግሩን ሲከታተል የቆየው መንግስት ችግሩን ለመፍታት መከላከያ አስገብቶ በእምነት ተቋሙ ላይ ምንም አይነት ውድመት ሳያደርስ አስፈላጊውን ስራ ሰርቷል ።

በመሆኑም አንዳንድ ሚዲያዎች ወረዳውን ለማጠልሸት እና ህዝብን ከመንግሥት ለማጋጨት የሀሰት አሉባልታ በማሰራጨት ህ/ሰቡን እያደናገሩት ይገኛሉ።
ስለዚህ ህ/ሰቡ በሀሰት አሉባልታዎች ሳይረበሽ ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመቆም አካባቢውን ተደራጅቶ በመጠበቅ የወረዳውን ሰላም በጋራ እየጠበቀ የግል ስራውን ተረጋግቶ እንዲሰራ እናሳስባለን።

# # # #መረጃው የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ነው።

25/05/2023
25/05/2023

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kidist Yalewle ET posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share