Daandii Ida'amu

Daandii Ida'amu poletices

14/08/2026

ሕገ ወጡ ህወሓት የቀድሞ ጠላቶቹን ሸኔና ጽንፈኞችን አቅፎ ሻዕቢያን ደግሞ አዝሎ የትላንት ክህደቱን በአደባባይ እየደገመው ይገኛል - የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

14/08/2026

ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለመላው ኢትዮጵያዊያን የተላለፈ መልዕክት
++++++++++++

| በኢትዮጵያ አዲስ ታሪክና ባህል ሆኖ እየተከናወነ ያለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መካሄድ ከጀመረ እነሆ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም አንድ ወር አስቆጠረ፡፡

ሂደቱ በሀገራችን ሲከናወን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመሆኑ፣ ለምክክር የቀረቡ አጀንዳዎች እጅግ መሰረታዊና ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ እንደመሆናቸው፤ የሀገራችንን ብዙኃነት መሰረት ያደረጉ ፍላጎቶች በርካታ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ጉባኤው የብዙዎች መነጋጋሪያ መሆኑ ለኮሚሽኑ አስገራሚ ነገር ሆኖ አልተገኘም፡፡

በዚህ ሂደት ኢትዮጵያዊያን የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮቻቸው ላይ ለመምከር ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ በምክክሩ ሂደት እያሳዩት ያለው መከባበር፣ መደማመጥ እንዲሁም እያካበቱት ያለው ማህበራዊ ግንኙነት እጅጉን አመርቂ እና ተስፋ ሰጪም ነው፡፡

ይህ በሀገራችን አዲስ የሆነው የምክክር መድረክ ብዙዎች እንዲተዋወቁ፣ የአንተ ችግር የእኔ ነው’ እንዲባባሉ፣ ለነገ ሀገራቸው የሚጠቅም የጋራ ሃሳብ በመግባባት እንዲያፈልቁ እያስቻለ ይገኛል፡፡ ሂደቱ በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት አንዱን ምዕራፍ እየጨረሰ ወደ ሌላው ምዕራፍ ሲሸጋገር ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ወሳኙ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

በኮሚሽኑ ግምገማ መሰረት ያለፈው አንድ ወር የምክክር ሂደት ስኬታማ ሥራዎች የተሰሩበት፣ ምክክር ባህል እንዲሆን መሰረት የሚጥሉ አዳዲስ ጉዳዮች የታዩበት ነው፡፡ ይህ ግን ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ ነበረ ማለት አይደለም፡፡ አለመግባባት የሚመስሉ ነገሮች ተስተውለዋል፡፡ እነዚህ ነገሮች አለመግባባት አለ ብለን ለተቀመጥን ወገኖች እንግዳ መሆን እንደሌለባቸው የኮሚሽኑ እምነት ነው፡፡

ኮሚሽኑ ካለው አሰራርና ልምድ በመነሳት እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ሊያግጥሙ እንደሚችሉ ምክክሩን ከማስጀመሩ በፊት በውል የተረዳው ጉዳይ ነው፡፡ጉዳዩ እንግዳ የመሰለው ለተመካካሪዎችና ወክለው ለመጡት አካል ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በዚህ ስጋት ላይ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች የሚያሰራጩት ሀሰተኛ መረጃ ሲጨመርበት ደግሞ ነገሩን ምን ያክል ውስብስብ እንደሚያደርገው ኮሚሽኑ ይረዳል፡፡

ለዚህ ነበር ኮሚሽኑ ህብረተሰቡን በኮሚሽኑ ከሚወጡ መረጃዎች፤ በስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ከሚያወጡት መረጃ ውጪ ካሉ መረጃዎች ራሱን በማቀብ ከሀሰተኛ መረጃዎች እንዲጠበቅ ሲያሳስብ የቆየው፡፡ አሁንም ምክክሩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን ተከትሎ የተዛቡ መረጃዎች በስፋት መውጣታቸውን ስለሚቀጥሉ በድጋሚ መላው ኢትዮጵያዊያን ኮሚሽኑ ከሚያወጣቸው መረጃዎችና በስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ከሚያወጡት መረጃ ውጪ ያሉ መረጃዎችን ባለመከታተል ራሱን ከሀሰተኛ መረጃ እንዲጠብቅ ኮሚሽኑ በድጋሚ ያሳስባል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችም ጫፍ ያልደረሰ መረጃ በማጋራት በህዝብ ላይ ያልተገባ ብዥታና መደናገርን ከመፍጠር እንድትቆጠቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ ያሳስባል። መሰል ተግባራትን ኮሚሽኑ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ ጥሰት እየፈፀሙ ያሉ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑንም ማሳወቅ ይወዳል። ይህ ክትትልና እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ማሳሰብ ይወዳል።

ሀገራዊ ምክክር ለሀገራዊ መግባባት!

14/08/2026
14/08/2026

አሸናፊ እና ተሸናፊ የሚለይበት ሳይሆን ኢትዮጵያ የምታሸንፍበት ታሪካዊ መድረክ

ሀምሌ 8/ 2018 ዓ/ም የተጀመረው ታላቁ የምክክር ጉባኤ፣ በስምንት ወሳኝ አጀንዳዎች ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ሕዝብ በወኪሎቹ አማካይነት በግልጽ የሚወያይበት፣ በምክንያት የሚሞግቱበት እና ብሔራዊ የጋራ መግባባት ላይ የሚደርስበት ታላቅ መድረክ ነው።

ሁሉም ዜጎች ለጥያቄያቸው ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት በመመካከርና በመወያየት እንጂ በጠብመንጃ እንዳልሆነና አሸናፊው እከሌ ነው ተሸናፊው እከሌ ነው የሚባልን ታሪክ ሊቋጭ ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የተወጣጡ 4ሺህ ተመካካሪዎች ኢትዮጵያዊያንን ወክለው እየመከሩ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በታሪኳ በርካታ የፈተናና የድል ምዕራፎችን አሳልፋ ዛሬ ላይ ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞዋን እያፋጠነች በምትገኝበት በዚህ ወቅት ሁላችንም ያሉብንን ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየትና በመፍታት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ ይኖርብናል።

እየተካሄደ ያለው ታላቁ ሀገራዊ ምክክር፣ ለቀጣዩ ትውልድ የምናወርሳት ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊት እና ሰላማዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ታላቅ ታሪካዊ መድረክም ጭምርም ነው።

የሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የሀገርን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያረጋግጥ፣ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋትን የሚያስፍን ቁልፍ ምዕራፍ ነው።

ዛሬ ላይ የሚደረገው ምክክር የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን የነገዋን ኢትዮጵያ በጠንካራ መሠረት ለመገንባትና የምናልመውን ብልጽግና ለማሳካት የሚያስችል ሂደት ነው።

14/08/2026

I'm in the top 18% of Jafar Sufian fans. I earned 149 points on their weekly engagement list last week.

14/08/2026

Big shout out to my newest top fans! Daandii Ida'amu

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራዊ ምክክርን በሚመለከት የተናገሩት
02/08/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራዊ ምክክርን በሚመለከት የተናገሩት

02/08/2026

የታሪክ ቀጠሮ! በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል አንድ ቀን ብቻ ቀረን!

02/08/2026

Address

Harer

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daandii Ida'amu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Daandii Ida'amu:

Shortcuts

Share