Urjii alii

Urjii alii Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Urjii alii, Women's clothes shop, Dire, Harer.

11/08/2026
11/08/2026
11/08/2026
11/08/2026

በሀረሪ ክልል በየዘርፉ የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለፀ።

የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ የክልሉ መንግሥት በያዝነው የበጀት ዓመት ትኩረት በሚያደርግባቸው ጉዳዮች በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው እንዳሉት በ2019 የበጀት አመት በተለይ ገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት መከተል፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችንና ቱሪዝምን ማስፋፋት፣ አረንጓዴና ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው ለስራ እድል ፈጠራ ለማጎልበትም በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ነው የገለፁት።

የድሀውን ማህበረሰብ የኑሮ ደረጃ ያገናዘበ የዋጋ መረጋጋት ስራ ላይም ርብርብ እንደሚደረግ የገለፁት ኃላፊው የግል ኢንቨስትመንቶችን ይበልጥ እንዲጠናክር ይደረጋል ብለዋል።

የክልሉን መንግሥት የበጀት ፍላጎትን ለማሳካት የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በማጠናከር የክልሉን የገቢ መሰረቶች ለማሳደግ እንደሚሰራ ነው የተናገሩት።

የምግብ ዋሰትናን ለማረጋገጥ የግብርና ምርታማነትንና የሌማት ትሩፋትን የማሳደግና የማስፋፋት ስራዎች እንደሚከናወኑ ጠቅሰው ተረጂነትን ዜሮ ለማድረግም የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በክልሉ ያለው የሰላምና አብሮ የመኖር እሴት የበለጠ ለማጽናትና የክልሉን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እንደሚሰራ ነው አቶ ሄኖክ የገለፁት።

በክልሉ በትምህርትና በጤና ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች የበለጠ ማጠናከር የ2019 የበጀት አመት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም የዲጂታል መሰረተ ልማት የማስፋፋ እንደሚከናወን አብራርተዋል።

ከዚህ ባሻገርም የማኅበረሰብ ጤና መድንን ማጠናከር እንዲሁም የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን እና በሴፍቲኔት የታቀፉ ወገኖችን የማብቃት ስራ ትኩረት እንደሚሰራ ነው የጠቆሙት።

የመኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት፣ የቤት ኪራይን በሕግና መመሪያ መቆጣጠር እንዲሁም የከተማ ግብርናን የማስፋፋት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የመንገድ ተደራሽነት ለማሻሻልና የንግድና የቱሪዝም ፍሰትን ለማሳደግ አዳዲስ የከተማና የገጠር መንገዶች ስራ ይከናወናል ብለዋል።

የኮሪደር ልማትና መሰረተ ልማት ዝርጋታ የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከር ሌላው ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው በገጠር ኮሪደር የሶፊ ወረዳ ሞዴል የገጠር መንደር ግንባታ በጥራት፤ በፍጥነት እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ እንደሚከናወን ተናግረዋል።

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችና ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች በተለይም የኢ-አስተዳደር (e-governance) አሰራርን እና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን የማጠናከር ስራ በትኩረት ይከናወናል ብለዋል።

ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘም መሶብ የአንድ ማዕከል በማስፋት የህዝብ አገልግሎትን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

ከዚህ በተጨማሪም የፀረ-ሙስና ዘመቻዎችን የማጠናከር፦ ለሙስና የሚያጋልጡ አሰራሮች በመለየት ማሻሻል እንዲሁም ሙስና የፈጸሙ አካላትን ተጠያቂነት የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

10/08/2026

Address

Dire
Harer

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Urjii alii posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share